ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

በቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት

የቪክቶሪያ ሲቪል እና ኣስተዳደር ሸንጎ(የመኖሪያ  ቤቶች የክራይ ዝርዝር) The Victorian Civil and Administrative Tribunal (Residential Tenancies List) በኣከራዮች እና ተከራዮች መካከል ያሉ ኣለመስማማቶችን ይሰማል። ይህ ፍርድ ቤት ኣይደለም፣ ግን በህግ ሊተገበሩ የሚችሉ ውሳኔዎችን ሊያደርግ ይችላል። ኣላማው መደበኛ ያልሆነ እና ርካሽ ለመሆን፣ እና ኣለመስማማቶችን በፍጥነትና ተጋቢ በሆነ ሁኔታ መፍታት ነው።

ማመልከቻዎች

ከኣከራይዎ ወይም ከወኪሉ ጋር በመነጋገር ችግሮችዎን ለመፍታት መሞከር የተሻለ ነው።  ነገር ግን ከኣከራይዎ ጋር ሊፈቱት ያልቻሉት ችግር ካለዎት፣ ለሸንጎው (ቪሲኤቲ)ማመልከት ይችላሉ። ለማመልከት ከወሰኑ፣ ለምክር እኛን ለመገናኘት ይችላሉ። ለማመልከት፣ የቪክቶሪያ ሲቪል እና ኣስተዳደር ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከቻ ቅጽመሙላት ያስፈልግዎታል። በቅጹ ላይ ያሉትን መመርያዎች ይከተሉ። ፎርሙ የኣከራዩን ስም የሚጠይቅበት ላይ፣ የወኪሉን ሳይሆን የኣከራዩን ስም ማስቀመጥዎን ያረጋግጡ።  ያከራይዎ ኩባንያ (ካምፓኒ)ከሆነ፣ ACN ያካትቱ።     የህዝብ ተከራይ ከሆኑ፣ ኣከራይዎ የቤቶች ጉዳይ ሃላፊ (Director of Housing) ይሆናል። ለኣከራዩ  የማመልከቻዎን ቅጂ መላክ ኣለብዎት፣ በተመዘገበ ደብዳቤ ቢሆን ይመረጣል። የደብዳቤውን ደረሰኝ እና የማመልከቻዎን ቅጂ ያስቀምጡ።

የማመልከቻ ክፍያዎች

የጤና እንክብካቤ ካርድ (Health Care Card) ካለዎለዎት ወይም የመያዣ ገንዘብዎን ለማስመለስ ከሆነ የሚያመለክቱት ስለተከራዩት ቤት ጉዳይ ቪሲኤቲ ችሎት የማከልከቻ ዋጋ መክፈል ኣያስፈልግዎትም።

የማመልከቻ ክፍያው ከ 1 ጁላይ 2019 ጀምሮ $65.30 ነው፣ ነገር ግን ሊቀየር ይችላል። ወቅታዊ ክፍያዎችን (ቪሲኤቲ ድረገጽ)(VCAT website)ይመልከቱ። የጤና እንክብካቤ ካርድ ከሌለዎት ወይም ክፍያውን ለመክፈል ኣቅም ከሌለዎት፣   የክፍያ ምህረት (ቪሲኤቲ ድረገጽ) (VCAT website)መጠየቅ ይችላሉ። ክፍያውን በጥሬ ገንዘብ መክፈል ከፈለጉ፣ ማመልከቻዎን ለ ቪሲኤቲ እራስዎ መውሰድ ያስፈልግዎታል።

የሸንጎው ችሎት (Notice of Tribunal) ማስታወቂያ

ከሸንጎው ችሎቱ መቼና የት እንደሆነ የሚነግሮት ማስታወቂያ ይደርስዎታል ለ ችሎቱ የሚጠብቁት ጊዜ በማመልከቻው ኣይነት እና ሸንጎው ምን ያህል በስራ የተጠመደ መሆኑ ይወሰናል።  በችሎቱ ቀን ወደሽንጎው መሄድ ካልቻሉ፣ ስለ ቀነ ቀጠሮ ማስቀየር ምክር ለመቀበል ሊደውሉልን ይችላሉ።  የቀነ ቀጠሮ ማስቀየር ጥያቄ ከችሎቱ ቢያንስ ሁለት የስራ ቀናት በፊት መደረግ ኣለበት እንዲሁም በማስረጃ (እንደ የህክምና ሰርተፍኬት)መደገፍ ኣለበት። የቀጠሮ መቀየር ፈቃድ ማግኘት ማስተማመኛ የለም፣ ነገር ግን ኣከራይዎ  ከተስማማ ጥሩ እድል ይኖረዋል።

ኣስተርጓሚ ካስፈለግዎ፣ ከችሎቱ ቀን በፊት ለሸንጎው ለመንገር ሊገናኝዋቸው ይገባል።  ሸንጎው ኣስተርጓሚ ሊያመቻች ይገባዋል፣ ካልሆነ ቀኑ እንዲቀየር ይጠይቁ።

ጉዳይዎን ማዘጋጀት

ለሸንጎው ማመልከቻ ሲያደርጉ፣ ጉዳይዎን ማረጋገጥ ሃላፊነት የርስዎ ነው። ይህ ማለትም ጥያቄዎን ለመደገፍ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርቦታል። የሚያስፈልግዎ ማስረጃ ኣይነት በሁኔታው ይወሰናል። ከችሎቱ በፊት፣ ሸንጎው እንዲያይልዎ የሚፈልጉዋቸውን ማንኛውም ደበዳቤዎች እና ሰነዶች ፎቶኮፒ ማድረግ፣ እንዲሁም ማንኛውም ምስክሮች በችሎቱ ቀን እንዲገኙ ማመቻቸት ኣለብዎት። ምስክሮችዎ ወይም ሰነዶችዎን ከርስዎ ጋር ባለመያዝዎ ሸንጎው ጉዳይዎን ቀን ኣይቀይርም፣ እንዲሁም ጥያቄዎን ለማረጋገጥ ስልክ ኣይደውሉም። በደብዳቤ ወይም በየምስክር ሰነድ ከመተማመን ይልቅ ኣንድሰው በኣካል ማስረጃ እንዲሰጥ ማድረግ የተሻለ ነው።  ኣንድ ምስክር በችሎቱ ለመቅረብ እምቢ ካለ እናም የነሱ ማስረጃ ኣስፈላጊ ነው ብለው ካመኑ፣ ሸንጎውን የምስክር መጥሪያ  እንዲሰጥ መጠየቅ ይችላሉ።  ሸንጎው የምስክሩን የመጓጓዣ ወጪ እና/ወይም ሌላ ኣበሎች እንዲከፍሉ ሊያዝ እንደሚችል ይወቁ። ለመጥሪያው ከችሎቱ ቀን በፊት ማመልከት ኣለብዎት።  ይህ ኣንድ ሰው የሸንጎውን ችሎት እንዲካፈል እና ማስረጃ እንዲሰጥ ትእዛዝ ነው።  ኣለበለዚያም፣ ኣንድ ምስክር ማስረጃቸውን በምስክር ሰነድ (በኣብዛኞች ጋዜጣ መሸጫዎች ይገኛል)ሊሰጥ ይችላል።

ለችሎቱ ለመዘጋጀት፣ ለማለት የሚፈልጉትን የሚዘረዝር ኣጭር ማስታወሻ ያድርጉ፣ ለሸንጎው ሊያሳዩ የሚፈልጉዋቸውን ሰነዶች ዝርዝር ጨምሮ። ዝግጁ መሆን ጥሩ ጉዳይ ለማቅረብ ቁልፍ ነው።

መወከል

ባጠቃላይ፣ እያንዳንዱ ወገን የየራሱን ጉዳይ ለሸንጎው እንዲያቀርብ ይጠየቃል።  ነገር ግን በባለዎያ ጠበቃ ሊወከሉ ይችላሉ (እንደ የኪራይ ጉዳይ ሰራተኛ)፣ [list type=square_list]

  • ኣከራዩ ሊያስወጣዎት እየሞከረ ያለ እንደሆነ
  • ኣከያዩ  ባለሞያ ጠበቃ የሆነ እንደሆነ
  • ኣከራዩ  በባለሞያ ጠበቃ የተወከለ እንደሆነ
  • ሸንጎው በህጋዊ እንዲወከሉ የፈቀደልዎት እንደሆነ

[/list] ውክልና የሚያስፈልግዎት መሆኑን ካመኑ፣ የችሎት ማስታወቂያ (Notice of Hearing) እንደደረስዎ ሊገናኙን ይገባል።  በሸንጎው ከተረኛ ጠበቃ (duty lawyer) ምክር እና ከተቻለም ውክልና ሊሹም ይችላሉ። 

ችሎቱ

ለሸንጎው በጊዜ መድረስዎን ያረጋግጡ።  የዘገዩ እንደሆነ፣ ችሎቱ ያለእርስዎ ይካሄዳል ስለዚህ ከችሎቱ ጊዜ 15 ደቂቃዎች ኣስቀድመው እዚያ ለመድረስ ያቅዱ። መድረስዎን ለጠረፔዛ ሰራተኛው ከነገሩ በኋላ፣ ወደችሎቱ ክፍል ይጠራሉ።  ‘ሜምበሩ’ (Member) (በጉዳይዎ ላይ የሚወስነው ግለሰብ)እርስዎን እና ኣከራዩን ወይም ተወካዩን በመጽሃፍ ቅዱስ ወይም በቃል እውነቱን እንዲናገሩ መሃላ እንዲምሉ ይጠይቃል። ጉዳይዎ የሚሰማበት መንገድ በዚያ ልዩ ሜምበር (Member) ይወሰናል፣ ነገር ግን በኣብዛኛው ማመልከቻውን ያደረገው ሰው መጀመርያ ጉዳዩን እንዲያቀርብ ይጠየቃል።

በፍጹም ጠባይዎን እንዳያጡ። ክርክርዎን ግልጽ እና ነጥቡ ላይ ያድርጉ እናም በ ኣከራዩ፣ ተወካዩ ወይም በሸንጎው ሜምበር ፍራቻ እንዳይዝዎ ይሞክሩ። ሜምበሩ ውሳኔውን ከማድረጉ በፊት ለጉዳይዎ ግንኙነት ኣላቸው ብለው የሚያምኑትን ነገሮች ሁሉ እንዲጠቅሱ እድሉ እንደተሰጥዎት ያረጋግጡ።

ትእዛዛት

ሁለታችሁንም እርስዎን ኣና ኣከራዩን ወይም ተወካዩን ካዳመጠ በኋላ፣ የሸንጎው ሜምበር (Tribunal Member) ዝእዛዝ ይሰጣል ይህም በጉዳይዎ ላይ ውሳኔ ነው። ትእዛዙ ያልተረዳዎት እንደሆነ፣ በዝግታ እንዲያብራራው ሜምበሩን ይጠይቁ።  የትእዛዙ የጽሁፍ ግልባጭ ከችሎቱ ሁለት ሳምንት ያህል በኋላ ይላክሎታል።  ሜምበሩን የውሳኔያቸውን ምክንያት በጽሁፍ እንዲያቀርቡልዎት መጠየቅ ይችላሉ፣ ነገር ግን የጽሁፍ ምክንያቱን ከችሎቱ ፍጻሜ በፊት መጠየቅ ኣለብዎት።  ሸንጎው ምክንያቶቹን ትእዛዙ በተደረገ በ 60 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ኣለበት። እርስዎ ሸንጎው ባደረገው ውሳኔ ደስተኛ ካልሆኑ፣ ይግባኝ ማለት ይችላሉ ግን በጣም በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ ነው። ይግባኞች ለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት (Supreme Court) መደረግ ኣለባቸው እንዲሁም ይህ በጣም ውድ ሊሆን ይችላል። ይግባኝዎን ከትእዛዙ እለት በ 28 ቀናት ውስጥ ማስገባት ኣለብዎት።  ይግባኝ ማለት ከፈለጉ፣ በተቻለ ፍጥነት እኛን ይገናኙን።

  የቪክቶሪያ ሲቪል እና ኣስተዳደር ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) 55 King Street Melbourne 3000 1300 01 VCAT (ነጻ መደወያ) ፋክስ (03) 9628 9822 ክፍት 9.00 ጠዋት እስከ 4.30 ከሰኣት በኋላ ከሰኞ እስከ ዓርብ

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የታተመ: ዲሴምበር 2011

The Victorian Civil and Administrative Tribunal | Amharic | December 2011


Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept