ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ለፍጆታ ክፍያዎች

በቤትዎ ውስጥ ላሉ አገልግሎቶም ማለት እንደ ኤሌትሪክ፣ ጋዝ፣ ዘይት፣ ውሀና ቆሻሻ ማስወገጃ ያሉት ‘ለመጠቀሚያ’ አገልግሎቶች በሚል ይጠራል። እነዚህን መገልገያ አገልግሎቶች ለማስቀጠል ወይም ለማስቆረጥ ያለዎት ሃላፊነቶች በዚህ ጽሁፍ ወረቀት ላይ ይገልጻል። እንዲሁም የትኛው ክፍያ የርስዎ ሃላፊነት እና የትኛው የባለንብረቱ ሃላፊነት እንደሆነ ያብራራል።

ይህ ገጽ

በመጀመሪያ ለማስቀጠያ ክፍያዎች
የተለያዩ ቆጣሪዎች
የራሱ የተለየ ቆጣሪ ያለው ንብረት
ለራሱ የተለየ ቆጣሪ የሌለው ንብረት
ያወጣውን ገንዘብ መመለስ
ወደ ኪራይ ቤት ሲገቡ
የተከራዩትን ቤት ሲለቁ
ጥገናዎች
ተለፎን

ከመገልገያ አገልግሎት ጋር በተዛመደ ችግር ካለብዎ ለአገልግሎት አቅራቢዎች ማነጋገር አለብዎ። የአገልግሎት አቅራቢዎች ችግሩን ካላስተካከሉት በቪክቶሪያ ለኤሌትሪክ ሀይልና ውሀ አቤቱታ ሰሚ (Energy and Water Ombudsman of Victoria (EWOV)) በስልክ 1800 500 509 ማነጋገር ይችላሉ።

በመጀመሪያ ለማስቀጠያ ክፍያዎች

እነዚህ የማስቀጠያ ክፍያዎች በንብረት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የመገልገያ አገልግሎት ሲቀጠል ይሆናል። ለመጀመሪያ ማስቀጠያ ክፍያዎች ማለት ለኤሌትሪክ፣ ውሀ፣ ጋዝ ወይም ዘይት አገልግሎቶች የተከራዮች ሀላፊነት አይደለም። እነዚህ የርስዎ ባለንብረት ሃላፊነቶች ይሆናሉ። ባለንብረቱ ሊያስከፍልዎ ከሞከረ ለነሱ መክፈል የለብዎም። (ይህ ለተለፎ ማስቀጠያ አይጨምርም። በዚህ እውነታ ጽሁፍ ወረቀት ጀርባ ላይ ‘ተለፎን/Telephone’ የሚለውን ይመልከቱ።)

የመጀመሪያ ማስቀጠያ ክፍያዎችን አጠናቀው ከሆነ፤ ባለንብረቱ የከፈሉትን ገንዘብ መመለስ አለበት። ገንዘቡን እንዲመለስልዎ በ28 ቀናት ውስጥ በደብዳቤ ለባለንብረቱ መጠየቅ። የክፍያ መጠየቂያውንና የከፈሉበትን ደረሰኝ ከደብዳቤው ጋር መላክና ቅጂውን ማስቀመጥ። ባለንብረቱ ገንዘቡን ካልመለሰልዎት በቪክቶሪያ ሲቪል አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) በኩል ባለንብረቱ እንዲመልስልዎ ትእዛዝ እንዲሰጥ ማመልከት አለብዎ።

የተለያዩ ቆጣሪዎች

ለርስዎ መገልገያ የተለያየ ቆጣሪ ስለመኖሩ ማወቅ አስፈላጊ ነው። የመገልገያ አቅርቦት በርስዎ ቤት ብቻ እንዲሆን የተለያየ መቁጠሪያ አንደኛው እርምጃ ይሆናል። ለምሳሌ፡ በአንዳንድ ህንጻ ውስጥ ያሉ ፍላቶች ለየብቻ የራሳቸው ውሀ መቁጠሪያ ሲኖራቸው፤ በሌሎች ህንጻ ውስጥ ያሉ ፍላቶች ደግሞ የውሀ ፍጆታ መጠን ለማወቅ በአንድ መቁጠሪያ ብቻይ ይሆናል። የተለያየ መቁጠሪያ ስለመኖሩ ለማወቅ በቀጥታ የአቅራቢ ኩባንያውን ማነጋገር ነው።

የራሱ የተለየ ቆጣሪ ያለው ንብረት

በርስዎ ቤት የራሱ መቁጠሪያ ካለው፣ ለሚከተሉት ክፍያዎች ለማካሄድ የራስዎ ሀላፊነት ይሆናል:

 

  • ለአቀርቦት ክፍያዎች ወይም ለኤሌትሪክ፣ ጋዝ ወይም ዘይት ፍጆታ (ለፍጆታና የመቀጠያ ክፍያን ያካተተ)
  • ለኤሌትሪክ ወይም ጋዝ ቆጣሪ ማሻሻያ ክፍያ
  • ሁሉም ክፍያ የሚወሰነው እንደ ውሀ ፍጆታህ ሲሆን (ግን የአገልግሎት ክፍያንና የማስቀጠያ ክፍያን አይደለም)
  • ለሁሉም ቆሻሻ ማስወገጃ ክፍያዎች
  • የታሸገን ጋዝ ለመጠቀም ክፍያዎች (ነገር ግን ለሚቀርብ ወይም ለሚከራይ የታሸገ ጋዝ አይደለም)

 

እነዚህን ክፍያዎች እንዲከፍሉ ከርስዎ ባለንብረት ጋር የስምምነት ድርድር ማካሄድ ይችላሉ። ለምሳሌ፡ በንብረቱ ላይ ትልቅ የአትክልት ቦታ ካለና እርስዎ እንዲንከባከቡለት ከፈለገ ታዲያ በየጊዜው ለአትክልት ማጠጣት የወጣው ክፍያ እንዲመለስልዎ መደራደር አለብዎ። የተደረገው ስምምነት በጽሁፍና በባለንብረቱና በርስዎ የተፈረመበት መሆኑን ያረጋግጡ።

የፍጆታ መጠየቂያው በርስዎ ባለንብረት በኩል የሚከፈል ከሆነ ታዲያ የእርስዎን ድርሻን ለእነሱ መልሶ ለባለንብረቱ መክፈል ይኖርብዎታል። በመገልገያ አቅራቢ በኩል ከተጠቀቀው ክፍያ በላይ የርስዎ ባለንብረት ሊያስከፍልዎ አይችልም።

ለራሱ የተለየ ቆጣሪ የሌለው ንብረት

ለርስዎ ኤሌትሪክ፣ ጋዝ፣ ዘይት ወይም ውሀ አገልግሎት የተለየ ቆጣሪ ከሌለዎች በስተቀር በዚያ አቅርቦት ወይም አገልግሎት ስለሚኖር ማንኛውም ወጪ የርስዎ ሃላፊነት አይሆንም። እነዚህ ወጪዎች የባለንብረቱ ሀላፊነት ይሆናሉ። በቤትዎ ውስጥ በማያዣ ጠርሙስ የታሸገ ጋዝ የሚጠቀሙ ከሆነ ለጋዙ ብቻ ተጠያቂ ሲሆኑ፣ ነገር ግን ለአቅርቦት ወይም ለመያዣ ጠርሙስ ኪራይ ሀላፊነት የለብዎም።

በመንግሥት ወይም በማህበረሰብ መኖሪያ ቤት ተከራይ ከሆኑ ታዲያ በተናጠል መቁጠሪያዎች ማስገባት አልተለመደም (ለምሳሌ፡ በትላልቅ ፎቅ ላይ ያሉ ፍላቶች)፤ ስለዚህ ለርስዎ ጋዝ፣ ኤሌትሪክ፣ ውሀ፣ ማሞቂያ ወይም የልብስ ማጠቢያ አገልግሎት ፍጆታ በመኖሪያ ቤት ጽህፈት ቤት (Office of Housing) በኩል ‘የአገልግሎት ክፍያ’ ሊያስከፍልዎት ይችላል።

ያወጣውን ገንዘብ መመለስ

የባለንብረቱ ሀላፊነት ሆኖ እርስዎ ለፍጆታ ሂሳብ ከፍለው ከሆነ ያወቱትን ያህል ባለንብረቱ ለርስዎ መመለስ አለበት። በ28 ቀናት ገንዘቡ እንዲመለስልዎ፤ ለባለንብረቱ ደብዳቤ ከክፍያ ጥያቄና ከተከፈለበት ደረሰኝ ቅጂ ጋር አያይዞ መላክ።

ባለንብረቱ በ28 ቀናት ውስጥ ካልከፈልዎ ባለንብረቱ እንዲከፍልዎ ትእዛዝ በቪክቶሪያ ሲቪል አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) በኩል እንዲሰጥ ማመልከት ይችላሉ።

ክፍያ ማካሄድ የባለንብረቱ ሃላፊነት ከሆነና አልከፍልም ካለ የፍጆታ አቅራቢ ድርጅቶች አገልግሎቱን ለመቁረጥ ሊያስፈራርዎ ይችላሉ። ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ በአስቸኳይ ለልዩ ፍርድ ቤት በማመልከት የፍጆታ ክፍያ ጥያቄ በባለንብረቱ እንዲከፈል ትእዛዝ ይሰጥ ዘንድ መጠየቅ። ለልዩ ፍርድ ቤት ሲያመለክቱ በተከራይ ማሕበር (Tenants Union/Tenants Victoria) እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም ከፍጆታ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ክርክር እንደነበረና ስለርስዎ ፍጆታ አቅርቦት መቆረጥ ድርድር እንደተደረገ መንገር ይኖርብዎታል። የፍጆታ አቅራቢ ድርጅቶች በዚህ ላይ ካልተስማሙ ለ EWOV ማነጋገር ያስፈልግዎታል።

ወደ ኪራይ ቤት ሲገቡ

ወደ ኪራይ ቤት ሲገቡ የፍጆታ አገልግሎቶች በስምዎ እንደገና ማስቀጠል የርስዎ ሃላፊነት ነው። አገልግሎቱን ለመቀጠልና ያለውን ቆጣሪ ለማንበብ የ48 ሰዓታት ማሳሰቢያ ለአገልግሎት አቅራቢዎች መስጠት አለብዎ። ወደ ኪራይ ቤት በሚገቡበት ጊዜ በአካባቢዎ ላለ የውሀ አቅራቢ በማሳወቅ፤ ስለዚህ ቀደም ሲል ለነበረ ተከራይ የውሀ ፍጆታ እርስዎ አይከፍሉም ማለት ነው።

ኤሌትሪክ ወይም ውሀ ሊቆጥብ የሚችል መሳሪያ ማስገባት ከፈለጉ (ለምሳሌ፡ ለውሀ ፍሳሽ ቆጣቢ ገላ መታጠቢያ ጫፍ) መጀመሪያ ከባለንብረቱ ጋር በመደራደር ወጪውን ሊሸፍኑ ወይም በከፊሉ መክፈል ከቻሉ ማቀናጀት። እንዲሁም ቤቱን በሚለቁበት ጊዜ ይህን መሳሪያ ባለንብረቱ እንዲያወጡት ስለመፈለግ ማወቅ አለብዎ። በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ (Residential Tenancies Act 1997) መሰረት ተከራዮች ሲለቁ በንብረቱ ግድግዳ ላይ የተለጠፈና የተገጠመ ካለ ማስወገድና የቤቱን ሁኔታ እንደነበረው አድርጎ መልቀቅ ይሆናል።

የጤና እንክብካቤ ካርድ ካለዎትና የፍጆታ ሂሳብ ለመክፈል ችግር ካለብዎ ወይም ለርስዎ የሚያስፈልግ መገልገያ ማለት እንደ ፍሪጅ ማቀዝቀዣ ወይም የልብስ ማጠቢያ መሳሪያ ለችግር ማቃለያ ጠቀሜታ የገንዘብ እርዳታ (Utility Relief Grant) ወይም ለመሳሪያዎችና መሰረታዊ ፍላጎት የገንዘብ እርዳታ (Appliance and Infrastructure Grant) ለማግኘት ይፈቀድልዎታል። በበለጠ መረጃ ለማግኘት በሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ፣ የዋጋ መቀነሻ ክፍልን (Department of Human Services Concessions Unit) በስልክ 1800 658 521 ደውሎ ማነጋገር።

የተከራዩትን ቤት ሲለቁ

ቤቱን ሲለቁ ለአገልግሎት መስጫ የማስቆረጫ ክፍያ አይኖርም። ይሁን እንጂ ቤቱን መቸ እንደሚለቁ ለአገልግሎት አቅራቢዎች መናገር አለብዎ፤ ከዚያም የተሌፎንን ያካተተ የመጨረሻ ቆጣሪ ንባብ ይደረግና መገልገያው ይቆረጣል። የ48 ሰዓታት ማሳሰቢያ መስጠት አለብዎ። አገልግሎቱን ካላስቆረጡት፤ ታዲያ የቀጣዩን ተከራይ ፍጆታ ሂሳብ መክፈል እንዳለብዎት ነው።

ጥገናዎች

በባለንብረቱ የተገጠመ የውሀ ቧንቧ እቃዎችን (ቱቦ፣ መክፈቻና መዝጊያ እንዲሁም የሙቅ ውሀ መገልገያ ወዘተ.) ለመቀየር ከተፈለገ የጥራት ደረጃው ‘A’ በሆነ እቃ መቀየር አለበት። ይህም ውሀን በብቃት ለመጠቀም የሚስማማ ጥራት ‘A’ መለኪያ በአውስትራሊያ ደረጃ (Standards Australia) እንደተሰጠ ነው። ባለንብረቱ እቃውን በጥራት ‘A’ ደረጃ ባለው ካለወጠ፤ ስለዚህ ለውሀ ፍጆታ ክፍያዎች የርስዎ ሃላፊነት አይሆንም። ባለንብረቱ በጥራት ‘A’ ደረጃ ባለው እቃዎች እስካስቀየሩ ድረስ ክፍያዎቹ የራሳቸው ሀላፊነት ይሆናል። ይህ በርስዎ ላይ ከደረሰ የመገልገያ እቃዎች እስከሚቀየሩ ድረስ ለውሀ ፍጆታ ክፍያዎች የባለንብረቱ ሀላፊነት እንደሆነ መንገር አለብዎ። ባለንብረቱ እምቢ ካለ ክፍያውን ባለንብረቱ እንዲከፍል ትእዛዝ በልዩ ፍርድ ቤት ለመጠየቅ ማመልከት ይችላሉ።

በባለንብረቱ በኩል በቀረበ መሳሪያዎች ወይም የተገጠመ እቃ ላይ ለጥገና ችግር ካለብዎና ምን ማድረግ እንዳለብዎ በበለጠ መረጃ ለማግኘት Repairs (ጥገናዎች) የሚለውን እውነታ ጽሁፍ ወረቀት ማየት።

ተለፎን

ከኪራይ ቤት ውስጥ ባለ የተለፎን አቅርቦትና መጠቀም በተዛመደ ማንኛውም ክፍያዎች የተከራዮች ሀላፊነት ይሆናል። በዚህ ውስጥ የሚካተት ለሁሉም የአገልግሎት ክፍያ፣ ለስልክ ጥሪ ክፍያ፣ ለመሳሪያ ኪራይ ክፍያና ለማስቀጠያ ክፍያዎች ናቸው። በተጨማሪም ለተለፎን መስመር የመጀመሪያ ማስቀጠያ ክፍያ ወጪን ያካትታል።

አዲስ በተገነባ ንብረት ላይ ከገቡ ወይም ለተወሰነ ጊዜ በንብረቱ ላይ ስልክ ካልተቀጠለበት ታዲያ የስልክ መስመሩን እንደገና ማስገባት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ይህም በጣም ውድ ሊሆን እንደሚችልና ወጪውን ከባለንብረቱ ላይ ማካካስ አይቻልም። በኮንትራት ስምምነት ውል ላይ ከመፈረምዎ በፊት የስልክ መስመር ማስገባት ስለማስፈለጉ ለማወቅ ከተለፎን አገልግሎት አቅራቢ ጋር ማጣራት እንዳለብዎ እንመክራለን። እንደዚያ ከሆነ ስለመጀመሪያ ማስቀጠያ ወጪ ክፍያ በተመለከተ ከባለንብረቱ ጋር መደራደር አለብዎ። የሚሰጥዎ ማንኛውም ስምምነት በጽሁፍና በእርስዎና በባለንብረቱ የተፈረመበት ስለመሆኑ ያረጋግጡ።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

ጥገናዎች
በቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Utility charges | Amharic | May 2010

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept