ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ለተከራይ መብቶች ትንሽ መጽሐፍ (አጭር መግለጫ)

በቪክቶሪያ ተከራዮች ሁሉም ህጋዊ መብት አላቸው። እነዚህን መብቶች በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ (RTA) 1997 መሰረት የተረጋገጡ ናቸው። ባለንብረቶች ተከራዮችን በመብታቸው እንዳይጠቀሙ ካደረጉ ወይም በደል ችግር ካደረሱ ህገወጥነት አሰራር ነው።

የነዋሪዎች ተከራይ አንቀጽ ህግ (RTA) የአሰራር ዘዴ ዝርዝሩ በዚህ ትንሽ መጽሀፍ ውስጥ ሲቀርብ፤ በተከራይና አከራይ ለሚቀርቡ መሰረታዊ የሆኑ ጥያቄዎችን መልስ ይሰጣል። በዚህ መጽሀፍ ላይ ላለዎት ጥያቄ መልስ ማግኘት ካልተቻለ ወይም በበለጠ ማብራሪያ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት የተከራይ አማካሪ አገልግሎቶችን ማነጋገር ነው።

በሞላው የቪክቶሪያ ግዛት ውስጥ የተከራይ አማካሪ አገልግሎቶች ይገኛሉ። እነዚህ አገልግሎቶች በነጻና ሚስጢራዊ በሆነ ሁኔታ ስለሚጠበቅ ታዲያ ተከራዮች መብታቸውን እንዲያስጠብቁ ይረዳቸዋል። ከነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ የተከራዮች ማሕበር አንዱ ነው። እኛን ለማነጋገር በስልክ 1800 068 860 መደወል ወይም በድህረገጽ www.tuv.org.au ላይ ገብቶ ማየትና በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የተከራይ አማካሪ አገልግሎት በመሄድ መረጃ ማግኘት ይቻላል። አስተርጓሚ ካስፈለግዎ በስልክ አስተርጓሚ አገልግሎት በኩል ሰልክ 131 450 በመደወል ያነጋግሩን።

የተከራዮች ማሕበር ብዙ አገልግሎቶችን ለተከራዮች ያቀርባል። በተከራዮች ማሕበር የሚያቀርቡ አገልግሎቶች፡

 • ቅጾችን በመሙላት ወይም በምታደርጉት የተከራይና አከራይ ስምምነት በተዛመደ ጉዳይ መርዳት
 • ችግር ሲደርስባችሁ እናንተን መርዳት፤ ለምሳሌ፡ ጥገና፤ ኪራይ ሲጨምር
 • እናንተን በመወከል ከባለንብረቱ እና ከንብረት ተወካይ ጋር መደራደርና ምክር መስጠት
 • በቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት እናንተን መርዳት ወይም መወከል
 • ስለ ተከራይ መብቶች ጉዳይ ከእናንተ ማህበረሰብ ቡድኖች ጋር መነጋገር
 • በአቅራቢያችሁ ወደሚገኘው የተከራይ አማካሪ አገልግሎት ቢሮ መላክ

 

የተከራዮች ማሕበር እንግሊዝኛ ለማይናገሩ ተከራዮች የመረጃ መገልገያ ለማቅረብ ዝግጁ ነው።

ለአዲስ ተከራዮች ጠቃሚ ምክር

የሚከተሉት ጠቃሚ ምክሮች በአብዛኛው የተከራይና አከራይ ጉዳይ ተግባራዊ ይሆናል።

 1. አንብባችሁ መረዳእት የማትችሉ ከሆነ በባለንብረትና በንብረት ተወካዮች በኩል በግዴታ ቅጾችንና የስምምነት ውሎችን በመፍራት አትፈርሙ (የተከራዮች ማሕበር የአካባቢዎ የተከራይ ምክር ሰጪ አገልግሎት ስለ ቅጹና ስምምነቱ ማብራሪያ ሊሰጥዎ ይችላል)።
 2. ከባለንብረት ወይም የንብረት ተወካዮች ጋር ስምምነት ካደረጉ በጽሁፍ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም በርስዎና በባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ መፈረሙን ማረጋገጥ (በሌላ አገር እንደሚደረገው አውስትራሊያ ውስጥም የቃል ስምምነቶች ተቀባይነት የላቸውም)።
 3. ለባለንብረት ወይም ለንብረት ተወካይ የሆነ ገንዘብ ከከፈሉ ፌርማና ቀን ያለበት በተለይ በጥሬ ገንዘብ መክፈልዎን የሚያረጋግጥ ደረሰን መውሰድ።
 4. የተከራይና ኪራይ ጊዜ እስካለቀ ድረስ የሚሰጣችሁን ደረሰኝ፤ ሰነዶች፤ ቅጽና የተከራይና አከራይን በተመለከተ የተደረጉትን ስምምነቶች በጥሩ ቦታ ማስቀመጥ።
 5. የሚያከራክር ጉዳይ ካለዎት ለተከራይ ምክር ሰጪ አገልግሎት ወይም ለቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ/ Consumer Affairs Victoria በማቅረብ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ለማግኘት ድርድር ይካሄዳል።
 6. ክርክሩ ከባለንብረቱ ወይም ከንብረት ተወካዩ ጋር ሆኖ ሊፈታ ካልቻለ ለቪክቶሪያ ህዝባዊና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት/Victoria Civil and Administrative Tribunal ማመልከት ይሆናል። ልዩ ፍርድ ቤት መደበኛ ፍርድ ቤት አይደለም። ለልዩ ፍርድ ቤት ማመልከቻ ካቀረቡ በኋላ በክርክሩ ካልረቱ ቅጣት አይደርስብዎትም። ለሚፈጠር ክርክር መፍትሄ ለማግኘት መደበኛ ያልሆነና ውድ ያልሆነ መድረክ ሲሆን መብታቸውን ለማይጠብቁላቸው ባለንብረት ወይም የንብረት ተወካዮች ላይ ለማመልከት ተከራዮች ይህንን አጋጣሚ መጠቀም ይችላሉ።

የቤት ኪራይ አጀማመር

የሚከራይ ቤት/ንብረት ማመልከቻዎች

የሚከራይ ቤት ስታመለክቱ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ግላዊ የሆኑ ጥያቄዎችን ሊያቀርብ ይችላል። አከራዮች ስለሚከተለው መረጃ ለተከራዮች መጠየቅ ህገወጥነት ነው፡

 • የርስዎን ጎሳ ብሄር
 • የርስዎን ሃይማኖት
 • የርስዎን የጋብቻ ሁኔታ
 • የርስዎን ጤና በተመለከተ
 • የርስዎን ጾታ
 • የርስዎን ወሲባዊ ግንኙነት ፍላጎት/አቀራረብ

 

ከዚህ በላይ የተገለጹት ሁኔታዎች የእርስዎን ለተከራይነት አመቺ ሁኔታ ከመፍጠር ጋር የተዛመደ አይደለም። ለሚቀርቡት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ካልፈለጉ አለመመለስ ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄዎች ባለመመለስዎ ምክንያት ያቀረቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ያጣል ብለው ካመኑበት ለተከራይ ማሕበር በማነጋገር ምክር ማግኘት ነው።

በአንዳንድ ሁኔታ ልጆች ስላለዎት ምክንያት በማድረግ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ያቀረቡትን ማመልከቻ ውድቅ ካደረገ ህገወጥነት ነው። ልጆች ስላለዎት ምክንያት ሆኖ ያቀረቡት ማመልከርቻ ተቀባይነት ካላገኘ ለተከራይ ማሕበር በማነጋገር ምክር ማግኘት።

ለረጅም ጊዜ የኪራይ ኮንትራት ውል

ያቀረቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ካገኘ ለረጅም ጊዜ የኪራይ ኮንትራት ውል ያደርጋሉ። አብዛኞቹ የኪራይ ስምምነት ውሎች በጽሁፍ ይካሄዳሉ። ሆኖም አንዳንድ የኮንትራት ስምምነት ውሎች በቃል ይደረጋሉ። ሁለት ዓይነት የኪራይ ኮንትራት ውሎች አሉ፤ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ//Fixed-term እና ጊዜያዊ/Periodic ናቸው።

ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ/Fixed-term የኪራይ ውል የሚፈቀደው ለተወሰነ የጊዜ ገደብ ቤቱን ለመከራየት ፤ ብዙጊዜ ለ6 ወይም ለ12 ወራት የሚቆይ ውል ነው። የጊዜያዊ/Periodic የኪራይ ኮንትራት ውል ደግሞ ብዙውን ጊዜ በየወሩ የሚደረግ ውል ነው። ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ/Fixed-term የኪራይ ውል ካለቀ በኋላ አዲስ ኮንትራት ውል ካልተፈራረሙ የርስዎ ኮንትራት ውል ወደ የጊዜያዊ/Periodi ኮንትራት ውል ይቀየር ይሆናል። ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ/Fixed-term የኪራይ ውል ካለቀ በኋላ እርስዎ ከፈለጉ ወይም ቤቱን እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ ካልደረስዎ በስተቀር ከቤቱ መውጣት የለብዎትም (ለመልቀቅ ማስጠንቀቂያ የሚለውን ይመልከቱ)።

ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ/Fixed-term የኪራይ ውል በጽሁፍ ከሆነ በሚፈጠር የአከራይና ተከራይ ክርክር እርስዎ እንዲረቱ ይረዳል፤ እንዲሁም የጊዜያዊ/Periodic የኪራይ ኮንትራት ውል ከሆነም ለመርዳት በነዋሪዎች የተከራይ አንቀጽ ህግ (RTA) ውስጥ የተካተተ ነው።

ከሌላ ጓደኛ ጋር ተዳብለው የሚኖሩ ከሆነ ስማቸው በኪራይ ስምምነት ውል ውስጥ መግባቱን ማረጋገጥ። እርስዎ ከለቀቁና ጓደኛዎ የሚኖር ከሆነ ስምዎ ከኪራይ ስምምነት ውሉ ውስጥ እንዲሰረዝ ለባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ መጠየቅ። ቤቱን ከለቀቁ በኋላ ስምዎ ካልተሰረዘ በጓደኛዎ በኩል ለሚደርሰው ጉዳት ብልሽትና ላልተከፈለ የቤት ኪራይ በሃላፊነት ሊያስጠይቅዎ ይችላል።

ለቤት ኪራይና ማስያዣ

የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ሲጀመር ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ የአንድ ወር የቤት ኪራይ በቅድሚያ እንዲከፍሉ ይጠይቃል። በአብዛኛው ከአንድ ወር በላይ የቤት ኪራይ በቅድሚያ እንዲከፍሉ ሊጠይቁ አይችሉም።

እንዲሁም የቤት ኪራይ በወቅቱ ካልከፈሉ ወይም በንብረቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ የማስያዣ ገንዘብ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። በአብዛኛው የማስያዣው ገንዘብ ከአንድ ወር የቤት ኪራይ መብለጥ የለበትም።

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ የማስያዣ መጠየቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት። ቅጹን ሞልተው ከፈረሙ በኋላ ለባለንብረቱ ወይም ለንብረት ተወካዩ መመለስ። አንድ ቅጂ ኮፒ ለእርስዎ ሪኮርድ መዝገብ ይረዳ ዘንድ መስጠት፤ እንዲሁም የርስዎን የማስያዣ ገንዘብ ወደ የነዋሪዎች ተከራይና አከራይ የገንዘብ ማስያዣ ባለሥልጣን (RTBA) መላክ አለባቸው። ባለሥልጣኑ በ14 ቀናት ውስጥ ለመድረሱ ማረጋገጫ ይልክልዎታል። የእርስዎ ተከራይና አከራይ ስምምነት ውል እስኪያልቅ ድረስ የማስያዣ ገንዘቡ በባለሥልጣኑ እጅ ይቆያል።

የአውስትራሊያ ቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ካለዎ እና ለማስያዣ ገንዘብ አቅም ከሌለዎት የመኖሪያ ቤት ቢሮ ሊረዳዎ ይችል ይሆናል። በአካባቢዎ ለሚገኝ የመኖሪያ ቤት ቢሮ የማስያዣ ገንዘብ ብድር እንዲሰጥዎ የማመልከቻ ቅጽ መጠየቅ (ሰብአዊ አገልግሎት ውስጥ ከA-K ያለውን የዋይት ፔጅስ የስልክ ማውጫ መመልከት።

የተከራዩትን ቤት ለቀው ሲወጡ እና የእርስዎን የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ለሌለው ሰው ሲያስተላልፉ፤ የማስያዣ ገንዘብ ማስተላለፊያ ቅጽ መሙላት አለብዎ (ይህ ቅጽ በንብረት ተወካይ፤ በተከራይ ማሕበር ወይም በቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ ይገኛል)።

የንብረት ይዘት መግለጫ ሪፖርት

የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ከመጀመሩ በፊት ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካይ የሚከራየውን ቤት መፈተሽ ማየት አለበት። ስለ ንብረቱ ይዘት የሚገልጽ ወቅታዊ ሪፖርት በማቅረብ የተጠናቀቀውን ሁለት ቅጂ ለርስዎ ይሰጣሉ።

ባደረጉት ፍተሻና ባቀረቡት የንብረት የንብረት ይዘት ሪፖርት ላይ ካልተስማሙ ለእያንዳንዱ ጉድለት ብልሽት ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። ማንኛውም የተሰበረ ወይም ቆሻሻ ካለ ማሳወቅ አለብዎ ወይም የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል በሚያልቅበት ጊዜ ሊያስጠይቅዎ ይችላል። የቀረበውን ሪፖርት አሟልተው ሲፈጽሙ አንዱን ቅጂ ለባለንብረቱ ወይም ለንብረት ተወካዩ መመለስ እና ሌላው ቅጂ ለርስዎ ሪኮርድ መዝገብ ማስቀመጥ።

ሌሎች ሰነዶችና መረጃዎች

ምናልባት አስቸኳይ የጥገና አገልግሎት ካስፈለገር ለማነጋገር የቤቱ ባለንብረት ወይም የንብረቱ ተወካይ አድራሻ ለርስዎ መላክ አለባቸው። እንዲሁም ስለ ባለንብረትና ተከራይ ግዲታና መብት የሚገልጽ ጽሁፋዊ ጥራዝ ወረቀት መስጠት አለባቸው።

አገልግሎት መስጫን ማስቀጠል

ከመግባትዎ በፊት የኤሌትሪክ፣ ጋዝ፤፣ ውሃና የስልክ መገልገያዎችን በራስዎ ስም ማስቀጠል ወይም ቀደም ብሎ በነበረው ተከራይ አጠቃላይ ሂሳብን ይከፍላሉ። በአካባቢዎ ያሉ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ለማነጋገር ዝርዝር ሁኔታ በባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ሊሰጥዎ ይችላል።

የኤሌትሪክና የስልክ መገልገያዎችን እንደገና ለማስቀጠል ይከፍላሉ።

ንብረት በተከራዩበት ጊዜ ጥገና

የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ሲጀምር የሚከራየው ቤት ንጽህናው የተጠበቀና መለቀቁን በባለንብረት ወይም በንብረት ተወካይ መረጋገጥ አለበት። እንዲሁም በንብረቱ ውስጥ ሲኖሩ በሚገባ መያዝና መጠበቅ ይኖርብዎታል።

ለአስቸኳይ ጥገና

አጣዳፊ የሆነ ጥገና ካስፈለግዎ በቀጥታ ለባለንብረቱ ወይም ለንብረት ተወካዩ ማነጋገር። የሚከተሉት ችግሮች እንደ አስቸኳይ ሥራ ይቆጠራሉ፡

 • የውሃ አገልግሎት ሲበላሽ/ሲፈነዳ
 • ሽንት ቤት ሲዘጋ ወይም ሲበላሽ
 • የቤት ጣራ ውሃ ሲያንጠበጥብ
 • ጋዝ ሲንጠባጠብ/ሲሰርቅ
 • አደገኛ የሆነ ኤሌትሪክ ብልሽት
 • ጎርፍ
 • በሃይለኛ ማእበል ወይም እሳት ጉዳት
 • የውሃ ማሞቆያ፤ ውሃ፤ ምድጃ/ማብሰያ፤ ማሞቂያና የልብስ ማጠቢያ መገልገያዎች ሲበላሹ
 • የጋዝ፣ ኤሌትሪክ ወይም የውሃ መገልገያዎች ሲበላሹ
 • በባለንብረቱ የቀረቡ የውሃ መገልገያዎች በመበላሸት ለብዙ የውሃ ፍሳሽ ብክለት የሚያዳርጉ ከሆነ
 • በንብረቱ ላይ ለመኖር የሚያስፈርራና የሚያሰጋ ብልሽት ሲኖር
 • በእግር መወጣጫ ደረጃው ወይም አስካላ/ሊፍት ላይ ብልሽት ካለ

 

ለባለንብረቱ ወይም ለንብረት ተወካዩ ማነጋገር ካልቻሉ ወይም ባስቸኳይ መጠገን ያለበትን አናስጠግንም ካሉ፡

 • እስከ $1000 ዶላር የሚያወጣ ጉዳት በራስዎ ወጪ ካስጠገኑ በኋላ ገንዘቡ እንዲመለስልዎት መጠየቅ ይችላሉ (ደረሰኝ በሚገባ ማስቀመጥዎን ያረጋግጡ) ወይም
 • ለቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት/Victoria Civil and Administrative Tribunal በማመልከት ችግሩን ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ እንዲያስጠግን ትእዛዝ እንዲሰጥ ማድረግ።

 

አስቸኳይ ላልሆኑ ጥገናዎች

ችግሩ አጣዳፊ ካልሆነ መከተል ያለብዎን ሶስት እርምጃዎች አሉ።

 1. ለባለንብረቱ ማስጠንቀቂያ የሚል ቅጽ (ይህ ቅጽ በተከራይ ማሕበር ወይም በቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ ውስጥ ይገኛል)፤ ለርስዎ ባለንብረት ወይም የንብረት ተወካይ ይላካል። ይህ ማስጠንቀቂያ በ14 ቀናት ውስጥ ችግሩ እንዲጠገን ያሳስባል።
 2. በ14 ቀናት ውስጥ ችግሩ ካልተጠገነ በቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ በጽሁፍ ተደርጎ ጉዳዩ እንዲጣራ ማሳወቅ። ጥያቄዎን ለሚከተለው ማቅረብ፡
  The Director
  Consumer Affairs Victoria
  GPO Box 123A
  Melbourne, Vic 3001
 3. በቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ በጽሁፍ የጉዳይ አጣሪ የርስዎን ችግር በጽሁፍ ተደርጎ ሪፖርት ያደርጋሉ። ያጣሩትን አንድ ቅጂ ሪፖርት ለርስዎ ይላካል። የቀረበው የጥገና ሥራ በሪፖርቱ ላይ ከተደገፈ፤ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ እንዲያስጠግን ትእዛዝ እንዲሰጥ ለቪክቶሪያ ህዝባዊና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት ማመልከት ነው።

ለአገልግሎት ክፍያዎች

በተከራዩት ቤት የራሱ ቆጣሪ ካለው ለተጠቀሙበት የኤሌትሪክ፤ ጋዝና ውሃ ፍጆታ ክፍያ ማካሄደ አለብዎት። በተከራዩት ቤት የተለየ ቆጣሪ ከሌለው ባለንብረቱ የፍጆታ ክፍያውን ማጠናቀቅ አለበት። አስፈላጊ ከሆነ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች የርስዎ ቤት የተለየ ቆጣሪ ካለው ሊያነጋግርዎት ይችላሉ።

በአብዛኛው የቴሌፎን ክፍያን በተመለከተ የተከራዮች ሃላፊነት ይሆናል።

ግላዊነት

በተከራዩት ቤት ውስጥ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ሊገባ የሚችለው ምክንያት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ለምሳሌ፡ አስፈላጊ ጥገና ለማካሄድ ነው። ለመግባት የፈለጉበትን ምክንያት በጽሁፍ አድርገው መግለጽ አለብዎ።

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ወደ ቤትዎ ለመግባት የርስዎን ስምምነት ማግኘት አለበት ወይም ወደ ቤት ለመግባት ፍላጎታቸውን የ24 ሰዓታት ጽሁፋዊ ማሳሰቢያ መስጠት አለባቸው። የጽሁፍ ማሳሰቢያው በፖስታ ቤት የሚላክ ከሆነ እስኪላክ ድረስ የሁለት ቀን ጊዜ መጠበቅ ያስፈልጋል። ከህዝብ በዓላት በስተቀር ጥዋት ከ8am እስከ 6pm ከሰዓት በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ሊደርስ ይችላል። በተከራዩት ቤት ብዙጊዜ የሚመጡ ከሆነ ወይም የሚያሰጋዎ ከሆነ ወደ ቤትዎ እንዳይመጡ ትእዛዝ በቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት እንዲሰጣቸው ማመልከት ይችላሉ።

ያተከፈለ ውዝፍ የቤት ኪራይ

የ14 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ያልተከፈለ የቤት ኪራይ ካለብዎ የርስዎ ቤት ባለቤት ወይም የንብረት ተወካይ እርስዎን ከቤቱ ለማስለቀቅ መነጋገር ይጀምራል። በቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ካልተሰጠ በስተቀር ከቤቱ ማስወጣት አይችሉም፤ ከሆነም ፖሊስ ብቻ ነው ሊያስወጣዎት የሚችለው።

የቤት ኪራይ ጭማሪ

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ የቤቱን ኪራይ ለመጨመር እንዳቀደ የሚገልጽ የ60 ቀናት ጽሁፋዊ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት።

የቤቱን ኪራይ ለመጨመር የታቀደው አግባብ አይደለም ካሉ ለቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ በጽሁፍ አድርጎ ማቅረብ። ማስጠንቀቂያው ከደረሰዎት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ለቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ በጽሁፍ አድርጎ ማቅረብ አለብዎት። የቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ ተቆጣጣሪዎች ቤትዎን በማየት ስለ ኪራይ ጭማሪ በተመለከተ ጉዳይ ሪፖርት ያደርጋሉ። ያቀረቡት ሪፖርት አንድ ቅጂ ለርስዎ ይልካሉ።

የተደረገው የቤት ኪራይ ጭማሪ በሪፖርት ውስጥ ካልተደገፈ የታቀደው የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዲሰረዝ ለቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት ማመልከት ነው።

ልዩ ፍርድ ቤት ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ የቤት ኪራይ ጭማሪን መክፈል ወይም ያልተከፈለ ውዝፍ ገንዘብ ይኖርብዎታል።

የተከራይና አከራይ ኮንትራት ውል ሲያልቅ ለመልቀቅ ማሳወቅ

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ቤቱን እንዲለቁ ከፈለጉ በጽሁፍ አድርገው የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ መስጠት አለባቸው። እርስዎን ከቤቱ ለማስለቀቅ በሚያቀርቡት ምክንያት የማስጠንቀቂያው ክብደት ይወሰናል። ቤቱን ለመልቀቅ ካልፈለጉ ወይም ለመልቀቅ ጊዜ እንዲሰጥዎ እየፈለጉ እያለ የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ከደረሰዎ የተከራዮች ማሕበርን ያነጋግሩ። ያስተውሉ! የቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ካልሰጠ በስተቀር በራሳቸው ከቤቱ ማስለቀቅ አይችሉም።

መልቀቅ ሲፈለግ ማሳወቅ

ቤቱን ለመልቀቅ ከፈለጉ በጽሁፍ ተደርጎ ማሳሰቢያ ለባለንብረቱ ወይም ለንብረት ተወካዩ መሰጠት አለበት። ለመልቀቅ የሚሰጠው የማሳሰቢያው ክብደት እርስዎ ለመልቀቅ በሚያቀርቡት ምክንያት መሰረት ይወሰናል። በማሳሰቢያው ውስጥ የሚያቀርቡት የጊዜ ገደብ እንደ የርስዎ ሁኔታ ይወሰናል።

በአብዛኛው የጊዜያዊ/Periodic ኮንትራት ውል ካለዎት የ28 ቀናት ማሳሰቢያ መስጠት ወይም ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ/Fixed-term ኮንትራት ውል ከሆነ በመጨረሻው የውል ቀን ለመልቀቅ ከፈለጉ ይቻላል። ነገር ግን የጊዜያዊ/Periodic ኮንትራት ውል እያለዎት በአስቸኳይ ቤቱን መልቀቅ ከፈለጉ ምክር ለማግኘት የተከራዮች ማሕበርን ማነጋገር።

ከተወሰነ ጊዜ/Fixed-term ኮንትራት ውል ከማለቁ በፊት ቤቱን መልቀቅ ከፈለጉ፤ የሚያቀርቡት የጊዜ ገደብ እንደ የርስዎ ሁኔታ ይወሰናል። የተወሰነው ጊዜ/Fixed-term ኮንትራት ውል ከማለቁ በፊት ቤቱን ከለቀቁ፤ ለማስታወቂያ ወጪ፤ እንደውገና ለማከራየት የሚያስፈልግ ወጪ እንዲሁም አዲስ ተከራይ እስኪገኝ ድረስ የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ ባለንብረርቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ሊጠይቅዎት ይችላል። የበለጠ ምክር ለማግኘት የተከራዮች ማሕበርን ያነጋግሩ።

ለማስያዣ ገንዘብ ማካካስ እና ደብዳቤ መጻፍ

በተከራይና አከራይ ኮንትራት ውል ማለቂያ ጊዜ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ በተከራዩት ቤት ላይ ፍተሻ ቁጥጥር ያካሂዳል። በተከራዩት ቤት ላይ ጉዳት ከደረሰ፤ አጽድተው ካለቀቁ ወይም ያልተከፈለ ኪራይ ካለ እንዲከፍሉት ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።

እነሱ ካቀረቡት ጥያቄ ከተስማሙ የገንዘብ መያዣ መጠየቂያ ቅጽ ይሰጥዎታል። በቅጹ ላይ የተዘረዘረው መግለጫ ላይ ከተስማሙ ፈርመው ቅጹን ወደ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ይላኩት። ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ በሚያቀርበው ጥያቂ ገንዘብ ላይ ካልተስማሙ በቅጹ ላይ አይፈርሙ።

በቅጹ ላይ ከፈረሙ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ወደ ነዋሪዎች ተከራይ ገንዘም መያዣ ባለሥልጣን/Residential Tenancies Bond Authority ቅጹ ይልከዋል። እርስዎና ባለንብረቱ በቅጹ ላይ በተስማማችሁበት መሰረት ባለሥልጣኑ ክፍያውን ይፈጽማል።

በቀረበው ጥያቄ ላይ ካልተስማሙ መጠነኛ ወይም ሁሉንም የማዝያዣ ገንዘብ እንዲመለስልዎት ለቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት/Victoria Civil and Administrative Tribunal ማመልከት ይችላሉ። ባለንብረቱ ባቀረበው ጥያቄ ላይ እንድትከራከሩ ልዩ ፍርድ ቤት እድል ይሰጥዎታል።

የተከራይና አከራይ ኮንትራት ውል ማለቂያ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ጽሁፋዊ ማስረጃ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ጥሩ ሃሳብ ይሆናል። የቤት ኪራይ በወቅቱ እንዳጠናቀቁ ተከራይተው የነበሩትን ቤት በንጽህናና በጥሩ ሁኔታ እንዳስረከቡ በጽሁፍ እንዲገልጽልዎት መጠየቅ።

ካሳ

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ያለብዎትን ህጋዊ ሃላፊነት ባለመወጣት የተነሳ ችግር ከደረሰብዎ ለጠፋው ኪሳራ ካሳ መጠየቅ ይችላሉ። ለምሳሌ፡ በቤርቱ ጣራ ላይ ያለው ቀዳዳ ባለመጠገኑ የተነሳ የርስዎ የቤት ቆሳቁስ በውሃ ከተበላሸ ታዲያ ለተበላሸው እቃ መተኪያ ካሳ መጠየቅ ይችላሉ።

የተከራይና አከራይ ኮንትራት ውል ሳያልቅ ወይም ካለቀ በኋላ የካሳ ጥያቂ ማቅረብ ይቻላል።

የካሳ ጥያቄ ለማቅረብ ከፈለጉ ለግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ/Breach of Duty Notice ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ መላክ አለብዎት (ይህ ለግዲታ መጣስ ማሳሰቢያ ቅጽ በተከራዮች ማሕበር ወይም በቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ ይገኛል)። የሚያቀርቡትን የካሳ ጥያቄና ጉዳት ዝርዝር በዚህ ማሳሰቢያ ላይ ይዘረዘራል። በ14 ቀናት ውስጥ የማካካሻውን ክፍያ ካላገኙ ትእዛዝ እንዲሰጥልዎ ለቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት ማመልከት ይችላሉ።

እንዲሁም ማድረግ የሚገባዎትን ህጋዊ ሃላፊነት ካልተወጡ ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ የካሳ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል። ለምሳሌ፡ የቤት ኪራይ ሳያጠናቅቑ ቤቱን ከለቀቁ። ተመሳሳይ የአሰራር ዘዴ መከተል አለባቸው።

አንድ ሰው ለደረሰበት ስቃይና ችግር እንዲሁም የአካል ጉዳት ወይም ሞትን በተመለከተ ለሚቀርብ የካሳ ጥያቄና የደረሰው ጉዳት ከ$10 000 ዶላር በላይ ከሆነ ልዩ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት አይችልም።

የካሳ ጥያቄ ለማቅረብ ከፈለጉ ወይም ለግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ/ Breach of Duty Notice ወረቀት ከባለንብረቱ ወይም ከንብረት ተወካዩ ከደረስዎ የተከራዮች ማሕበርን ያነጋግሩ።

የቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት

በባለንብረቱና ተከራዮች መካከል ለሚፈጠር ክርክር የቪክቶሪያ ህዝባዊ አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት መፍትሄ ይሰጣል። ለልዩ ፍርድ ቤት ማመልከቻ ለማስገባት $30 ዶላር ያስከፍላል። ነግር ግን የገቢ መጠንዎ አነስተኛ ከሆነ ልዩ ፍርድ ቤት ላያስከፍልዎት ይችላል።

ልዩ ፍርድ ቤቱን ለማነጋገር አድራሻ፡

55 King St
Melbourne
ስልክ; 1300 01 VCAT, የነጻ ስልክ 1300 01 VCAT, ፋክስ; 9628 9822

ማመልከቻ በልዩ ፍርድ ቤት ካቀረቡ በሰባት ቀናት ውስጥ ለባለንብረቱ የማመልከቻውን ቅጂ መላክ አለበት። የርስዎ ጉዳይ የሚታይበትን ቀንና ቦታ ልዩ ፍርድ ቤቱ ያሳውቅዎታል። የርስዎ ችግር አጣዳፊ ከሆነ ማመልከቻውን በሚያቀርቡበት ጊዜ ለልዩ ፍርድ ቤቱ ማሳወቅ።

አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ ጉዳዩ ከሚታይበት ቀን በፊት ለልዩ ፍርድ ቤቱ ማሳወቅ። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው። የርስዎን ጉዳይ ለፍርድ ችሎት ለማቅረብ ዝግጅት ለማድረግ የተከራዮች ማሕበር ሊረዳዎ ይችላል። ለየት ያለ ሁኔታ ካለዎት ጉዳዩ በችሎት ሲታይ እርስዎን ወክለን መቅረብ እንችላለን። ይህ የነጻ አገልግሎት ነው።

በባለንብረቱ ወይም በንብረት ተወካዩ ስለሚቀርቡ ክሶች

ባለንብረቱ ወይም በንብረት ተወካዩ ህገወጥነትና ከሙያ ስነምግባር ውጪ ባለው ሁኔታ ካስተናገድዎ በቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ ክስ ማቅረብ ይችላሉ። ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ በርስዎ ላይ ህገወጥ ተግባር መፈጸሙ በቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳይ ቢሮ ከተረጋገጠ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ ይቀጣሉ።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Tenants’ Rights (summary of Tenants’ Handbook) | Amharic | July 2006

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept