ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የኪራይ ወቅት መጀመር

[column width=”1/3″ place=”first” ][feature color=”ico-black” title=”this page” icon=”ico-hand-down” iconcolor=”ico-black” ]የኪራይ ስምምነቶች
ለኤለክትሮኒክ ማስታወቂያዎች ስምምነትዎ
ሊያገኝዋቸው የሚገቡ ማስረጃዎች (documents)
የሁኔታ ሪፖርት
ፎቶዎች ያንሱ
ውል
ኪራይ [/feature] [/column]
[column width=”1/3″ place=”last” ]
[/column]

የኪራይ ስምምነቶች

የኪራይ ስምምነት (አንዳንዴ ሊዝ ተብሎ የሚጠራው) በጽሁፍ ወይም በቃል ሊሆን ይችላል     ለተወሰነ ወቅት (ለምሳ 6 ወይ 12 ወራት) ወይም ጊዚያዊ (ባብዛኛው ከወር ወር) ሊሆን ይችላል።

ውስን-ወቅት ስምምነቶች የበለጠ አስተማማኝ ናቸው ምክንያቱም አከራዩ ሊያስወጣዎት ከባድ ያደርጉበታል፣ ግን የተወሰነው ጊዜ ከማለቁ በፊት ለመልቀቅ ከፈለጉ ውድ ሊሆኑ ይችላሉ።      የውሉን ሙሉ ወቅት ለመቆየት እንደሚፈልጉ እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ የውስን፟-ወቅት ስምምነት ውስጥ ይግቡ።

ማንኛውም ገንዘብ ከመክፈልዎ እና ከመግባትዎ በፊት በቤቱ ሁኔታ ደስተኛ መሆንዎን ያረጋግጡ።  አከራዩ እርስዎ ከመግባትዎ በፊት ቤቱን ለመጠገን ወይም ለማሻሻል ከተስማማ (ምሳ ማሞቅያ ለማስገባት)፣ ይህ በኪራይ ስምምነትት ውስጥ መካተቱን ወይም ቃል መግባቱን በጽሁፍ ማኝኘትዎን ያረጋግጡ።

በጽሁፍ የሰፈረ የኪራይ ውሉ ካለ፣ ከመፈረምዎ በፊት አንድ ቅጂ እንደተሰጥዎት ያረጋግጡ።  አስፈላጊ ከሆነ፣ ከመፈረምዎ በፊት ምክር ይፈልጉ፣ በተለይ “ተጨማሪ ውሎች” (additional terms) የተያያዙ እንደሆነ። ውሉን በፈረሙ በ14 ቀናት ውስጥ አንድ ቅጂ መሰጠት አለብዎት።

ማስታወቂያዎች በኤለክትሮኒክ እንዲላክልዎት ፈቃደኝነትዎ

የኪራዩን ውል በሚፈርሙበት ወቅት፣ አከራዩ ወይም የንብረቱ ተወካይ አከራዩ ማስታወቂያዎችን በኤሌክትሮኒክ እንዲልክልዎ እንዲስማሙ ሊጠይቅዎ ይችላል (ለምሳሌ፣ በኢሜል)  ይህንን በተመለከተ በውሉ ውስጥ አንቀጽ ሊያካትቱ ይችላሉ።  ኢሜልዎን በየጊዜው የሚያዩ ከሆነ ብቻ ለዚህ ይስማሙ።   እነሱ ማስታወቂያ የሚልኩበት የኢሜል አድራሻ የተጠቀሰ መሆኑን ያረጋግጡ።   አከራዩ ወይም የንብረቱ ተወካይ የላኩት ኢሜል ወደ አይፈለጌ መልዕክት ተቀይሶ ወይም በመጠኑ ምክንያት ተመላሽ የመሆን እድል እንዳለ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብዎት።

ማስታወቂያዎች በኤሌክትሮኒክ እንዲላክሉዎ ያለመስማማት ይችላሉ፣ ግን ቢስማሙም እንኳን ለወደፊቱ ሃሳብዎን ከቀየሩ ፈቃደኛነትዎን ማንሳት ይችላሉ።

ለኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ስምምነትዎን ካነሱ፣ ስምምነትዎን ማንሳትዎን ማስረጃ መያዝዎን ያረጋግጡ።  ለምሳሌ፣ አከራዪ ማስታወቂያዎችን በኤለክትሮኒክ እንዳይልክልዎት የነገሩበትን ኢሜል ወይም ደብዳቤ ቅጂ ያስቀምጡ።

ሊያገኝዋቸው የሚገቡ ማስረጃዎች (documents)

የክራይ ጊዜዎ መጀመርያ ላይ፣ አከራዪ ለርስዎ መስጠት ያለበት፤  [list type=square_list]

  • ቤት መከራየት፣ መምርያ ለተከራዮች (Renting a Home: a guide for tenants) [(መጽሃፍ ከቪክቶሪያ ተጠቃሚ ጉዳዮች (Consumer Affairs Victoria)]
  • የውል መያዣ (bond) የከፈሉ እንደሆነ፣ የውል መያዣ መመዝገብያ ቅጽ (bond lodgment form) እና 2 የተሞሉ የ ሁኔታ ሪፖርት (Condition Report) ቅጅዎች
  • የአከራዪ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ እና ፋክስ ቁጥሮች
  • ተወካይ ያለ እንደሆን፣ ተወካዪ አስቸኳይ ጥገናዎችን የመፍቀድ ስልጣን ያለው እንደሆነ እና እንዳልሆነ፣ እንዲሁም መፍቀድ የሚችሉት መጠን በጽሁፍ
  • የአከራዪ የአደጋ ጊዜ ስልክ ቁጥር፣ ወይም የተወካዩ ስልክ እና ፋክስ ቁጥር፣ ምናልባት አስቸኳይ ጥገናዎች ያስፈለጉ እንደሆነ

[/list]

የሁኔታ ሪፖርት

ውል መያዣ የከፈሉ ከሆነ አከራዩ 2ቅጂ የሁኔታ ሪፖርት ከመግባትዎ በፊት ሊሰጥዎ ይገባል። ሪፖርቱ በኣከራዩ፣ ወይም ተወካዮቻቸው፣ መፈረም ኣለበት፣ እንዲሁም ሪፖርቱ በተዘጋጀበት ወቅት ያለውን የጥገናውን ደረጃ እና የቤቱን ጠቅላላ ሁኔታ (የውስጡንም የውጩንም) መዘርዘር ኣለበት።

ከዚያም እርስዎ የሁኔታ ሪፖርቱን ለመሙላት እና ለመፈረም እንዲሁም ኣንዱን ቅጂ ለኣከራዩ ወይም ተወካዩ ለመመላስ ከገቡበት እለት ጀምሮ 3 የስራ ቀናት ኣለዎት።
የሁኔታ ሪፖርቱ እርስዎ በገቡበት ወቅት ስለነበረው የቤቱ ሁኔታ እንደ ተጨባጭ ማስረጃ ሊተማመኑበት ይችላሉ። ስለዚህ የሪፖርቱን ቅጂ ፈርመው ከመመለስዎ በፊት ቤቱን ይጎብኙና ማንኛውም ችግሮች እና ጉዳዮች በሁለቱም ቅጂዎች ላይ መጥቀስ ኣለብዎት፣ በተለይ የርስዎ ሃሳብ ከኣከራዩ ወይም ወኪሉ የተለየ እንደሆነ፣ ለምሳሌ በኣከራዩ ወይም ወኪሉ ያልተመዘገበ በምንጣፍ ላይ ያለ ምልክት/እድፍ።  ይህ ኣስፈላጊ ነው በተለይ የሁኔታ ሪፖርቱ የተከረይነትዎ ማብቂያ ወቅት የውል ገንዘብ ወይም ለብልሽትየካሳ ጥያቄ ወይም ማጽጃ ወጪ ለመከራከር ሊያግዝዎ ይችላል።

በሁኔታ ሪፖርት ቅጽ ላይ በቂ ስፍራ የሌለ እንደሆነ በኣስፈላጊ ቦታ ላይ “see attached” (የተያያዘውን ይመልከቱ)ብለው ይጻፉና ተጨማሪ ገጽ ያያይዙ።
ሲጠናቀቅ፣ ፈርመው ኣንድ ቅጂ ለኣከራዩ ይመልሱና ሌላውን ቅጂ ምናልባት የኪራይዎ ወቅት ሲያበቃ ያስፈልግዎት እንደሆነ በ ኣስተማማኝ ስፍራ ያስቀምጡ።

ፎቶዎች ያንሱ

ፎቶዎች የቤቱን ሁኔታ ለማሳየት በጣም ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ወደቤቱ የገቡ ጊዜ ብዛት ያላቸው ፎቶዎች እንዲያነሱ እናሳስባለን፣ እንደገናም ለቀው ሲወጡ፣ ስለዚህ ቤቱን እንዴት እንደተረከቡት እና ለቀውት እንደወጡ የራስዎ የሆነ ማስረጃ ይኖርዎታል።

ውል

ኪራይዎ $350 በሳምንት ወይም ከዚያ በታች ከሆነ፣ ኣከራዩ ከኣንድ ወር ክራይ በላይ የሆነ መያዣ ሊጠይቅዎ ኣይችልም።

በኣብዛኛው ጊዜ፣ ሁለቱንም የመያዣ ቀብድ (bond) እና ዋስትና (guarantee) ሊጠየቁ ኣይቻልም። ከተጠየቁ፣ ለምክር ይገናኙን።

መያዣዎን ሲከፍሉ፣ ኣከራዩ ወይም ወኪሉ የመያዣ መመዝገቢያ ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ቅጹን እርስዎ እንዲፈርሙት መስጠት ኣለባቸው።  ከዚያም እነርሱ ቅጹን እና የመያዣ ገንዘቡን በ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በ የመኖርያ ክራይ መያዣ ባለስልጣን (Residential Tenancies Bond Authority) ጋር ማስመዝገብ ኣለባቸው።  የመያዣ ባለስልጣኑም በደረሰው በ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ደረሰኝ ይልክልዎታል።

ኪራይ

ኪራይዎ  በሳምንት $300 ወይም በታች ከሆነ በቅድሚያ እንዲከፍሉ ሊጠየቁ የሚቻለው ቢበዛ የኣንድ ወር ኪራይ ነው።  ነገር ግን የኪራይ ስምምነቱ ኪራዩ በየሳምንቱ ይከፈላል የሚል ከሆነ፣ በቅድሚያ እንዲከፍሉ ሊጠየቁ የሚቻለው ቢበዛ የ 2 ሳምንታት ነው።

ኪራይዎን በኣካል የሚከፍሉ ከሆነ፣ ደረሰኝ ወዲያውኑ ሊሰጥዎት ይገባል። ኪራይዎን ለመክፈል ሌላ መንገድ የሚጠቀሙ ከሆነና በሚከፍሉበት ወቅት ደረሰኝ የጠየቁ እንደሆነ፣ ደረሰኝ በ 5 የስራ ቀናት ሊሰጥዎ ይገባል። በወቅቱ ደረሰኝ ባይጠይቁም እንኳን፣ ኪራዩን ከከፈሉበት ቀን እስከ 12 ወራት ውስጥ የመክፈልዎን ማስረጃ መጠየቅ ይችላሉ።   የ ማስረጃው ግልባጭ በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ሊሰጥዎ ይገባል። ደረሰኝ ለመስጠት እምቢ ማለት ህጋዊ ኣይደለም።

እንዲሁም ወኪሎች (ወይም ሶስተኛ ወገንንም ጨምሮ ሌላ ማንም)  ለ የመጀመርያ ጊዜ ለሚሰጥ የኪራይ መክፈያ ካርድ ወይም የቀጥታ መክፈያ ግልጋሎቶች መመስረት እና/ወይም መጠቀም ማስከፈል ህጋዊ ኣይደለም።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።


[disclaimer-rta-amharic]


[feature color=”ico-black” title=”related pages” icon=”ico-more-items” iconcolor=”ico-black”]

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

የግል መኖሪያ ቤት ኪራይ ስለማመልከት

ማስያዣ ገንዘብ

ኮንትራትን ስለማቋረጥ

ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች

የቤት ኪራይ ስለመጨመር

[feature color=”ico-black” title=”the law” icon=”ico-bank” iconcolor=”ico-black”]

የመኖርያ ቤት የኪራይ ደንብ (Residential Tenancies Act) 1997 (AustLII ድረገጽ)

ክፍል 29 (Section 29) – የኪራይ ውል ቅጂዎች ለተከራይ እንዲሰጡ
ክፍል 31, 32, 33 – የውል መያዣ ከፍተኛ መጠን
ክፍል 35 – የሁኔታ ሪፖርት
ክፍል 36 – የሁኔታ ሪፖርት የጥገና ደረጃ ማስረጃ ነው
ክፍል 37, 38 – ማስተማመኛዎች
ክፍል 40, 41 – የኪራይ የቅድሚያ ክፍያ
ክፍል 51 – ለኪራይ መክፈያ ካርዶች/ቀጥታ ክፍያ ማስከፈል
ክፍል 66 – የመብት እና የኣከራይ/የወኪል መረጃ ማግለጫ
ክፍል 406 – የውል መያዣን መመዝገብ ሃላፊነት

[/feature]


Starting a tenancy | Amharic | March 2019

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept