ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

በደባል ቤት ነዋሪዎች

የሁሉም ደባል ነዋሪዎች አንድ ዓይነት ቅንጅት አይሆንም። በቤት ወይም ፍላት ላይ ከሌላ ሰው ጋር ሲዳበሉ ይህ የአብሮ ተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ሊባል ሁሉም ተከራዮች እኩል መብቶች ሊኖራቸው ይችላል፤ አንደኛው ተከራይ ከሌላው ተከራይ መከራየት ወይም የተከራይና አከራይ መብት ሳይኖርዎ ለመኖር ፈቃድ ስምምነት ሊሆን ይችላል።

ከሌላ ተከራዮች ጋር ተዳብለው ሲኖሩ በተለይ ቀደም ሲል በነበረ ‘የመዳበያ መኖሪያ ቤት’ ውስጥ ሲገቡ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ስለርስዎ ህጋዊ መብት ሊያጠራጥርዎ ይችላል እንዲሁም በእያንዳንዱ አብሮ ተከራዮች ስላለ ግንኙነት ወይም ለመኖር ፈቃድ ስምምነት ያሉት መብቶችና ግዴታዎች በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ (Residential Tenancies Act 1997) ውስጥ አይካተትም።

ይህ ገጽ

የአብሮ ተከራይና አከራይ ውል
በውሉ ላይ ስምች
ለቤት ኪራይና ለፍጆታ ክፍያዎች
በደባል ቤት ነዋሪነት ስለመልቀቅ
በተከራይና አከራይ ውል ላይ ሌላ አብሮ ማስገባት ድረግ
ለመኖር ፈቃድ/Licence
ምክር ስለማግኘት

የአብሮ ተከራይና አከራይ ውል

ይህ በጣም የተለመደ የደባል መኖሪያ ቤት ዓይነት ነው። የሁለትወይም ከዚያ በላይ ተከራዮች ስም በኮንትራት ውል ላይ ሲገባ የአብሮ ተከራይና አከራይ ውል ይፈጠራል።

በተከራይና አከራይ ስምምነት ላይ ስማቸው ያለ አብሮ ተከራዮች በምምነቱ መሰረት ‘በጋራ መጠቀምና ተጠያቂ’ ይሆናሉ። ይህ ማለት በንብረት ላይ ለደረሰበት ጉዳትና ብልሽት ክፍያ መጠን ለሁሉም አብሮ ተከራዮች ወይም ለተወሰኑት እንዲከፍሉ ባለንብረቱ መጠየቅ ይቻላል።

ሁሉም አብሮ ተከራዮች ከቤት ለቀው ቁልፎች እስካልተመለሰ ድረስ የአብሮ ተከራይና አከራይ ስምምነት አያልቅም። የተከራይና አከራይ ስምምነት ከማለቁ በፊት የደባል መኖሪያ ቤትን ሲለቁ ስምዎ በውሉ ላይ ካለ ታዲያ ቤቱን ከለቀቁ በኋላ ለሚከሰት ጉዳትና ብልሽጥ እርስዎም ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ።

በውሉ ላይ ስምች

አብሮ ተከራይ ከሆኑ የሁሉም ተከራዮች ስም በሙሉ በስምምነት ውሉ ላይ ስለመኖሩ ማረጋገጥ ወይም መጀመሪያ ውሉ ከተፈረመ በኋላ ባለንብረቱ ወይም የግል ንብረት ተወካዩ በጽሁፍ ያቀረበው ለውጥ ካለ ማረጋገጥ አለብዎ። ከባለንብረቱ ወይም ከግል ንብረት ተወካዩ ጋር ለሚያደርጉት ግንኙነት ምናልባት በኋላ እንደ ማስረጃ ስለሚጠቅም ቅጂውን ማስቀመጡ ጥሩ ዘዴ ነው።

አንድ ተከራይ ሲወጣና በሌላ ሲተካ፤ የወጣውን ተከራይ ስም ከውሉ ውስጥ ማውጣትና አዲስ በተከራየው ሰው ስም መተካት።

ባለንብረቱ ወይም የግል ንብረት ተወካዩ ንብረትን ፈትሸው አዲስ የንብረት መግለጫ ሪፖርት እንዲሞሉ መጠየቅ ይችላሉ፤ ግን ላያደርጉት ይችላሉ። ሪፖርት ላለመሙላት ከመረጡ እርስዎ የቤቱን ሁኔታ የሚያሳይ ፎቶግራፎች በማንሳት ምናልባት በኋላ ካስፈለገ እንደ ማስረጃ ይጠቅማል።

እንዲሁም በዚህ ጊዜ የተከራይ ማስያዣ ማስተላለፊያ (Bond Tenant Transfer) ቅጽ መሞላት አለበት። ለተከራይ ማስያዣ ማስተላለፊያ ቅጾች ከተከራይ ነዋሪዎች ማስያዣ ባለስልጣን (Residential Tenancies Bond Authority)፣ ከግል ንብረት ተወካዮች ወይም ከተከራይ ማሕበር ቢሮ ይገኛሉ።

ለቤት ኪራይና ለፍጆታ ክፍያዎች

የቤት ኪራይንና የፍጆታ ክፍያዎችን ለማካሄድ ዘዴ መፍጠር ይኖርብዎታል። ብዙ ጊዜ በደባል መኖሪያ ቤት ያለ አንድ ሰው የቤት ኪራይ ወይ የፍጆታን ሂሳብ ለመክፈል ሀላፊነት ይወስዳል። ይህ ሰው ከመክፈል ሲያቆም ወይም ሌሎች ነዋሪዎች ድርሻቸውን ካልከፈሉ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። የቤት ኪራይ ድርሻዎን ከከፈሉና ሌላው ካልከፈለና ውዝፍ የቤት ኪራይ ከ14 ቀናት በላይ ወደኋላ ያልተገፈለ ከሆነ ባለንብረቱ ሁላችሁንም ከቤት ለማስወጣት ያለውን ሂደት መከተል ይጀምራል። ባለንብረቱ የቤት ኪራይ ባልከፈለ ግለሰብ ብቻ እርምጃ አይወስድም።

በደባል ቤት ነዋሪነት ስለመልቀቅ

አንድ ሰው ሊወጣ ሲፈልግ ወይም እንዲወጣ ሲጠየቅ ለምን ያህል ጊዜ ማሳሰቢያ መስጠት እንዳለበት በስምምነት ላይ ማቅረብ አለብዎ። እንደገና በነዚህ ሁኔታዎች ላይ አብሮ ተከራዮች በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ (Residential Tenancies Act 1997) ውስጥ አይካተትም። የተከራዩ ስም በተከራይና አከራይ ውል ላይ ካለ ምንም እንኳን በንብረቱ ላይ የማይኖርም እስከ ኮንትራቱ አልቆ ሁሉም እስኪለቅ ወይም አዲስ የኮንትራት ውል እስኪደረግ ድረስ በስምምነቱ መሰረት የተከራዩ ሀላፊነት ይቀጥላል። በደባል ቤት ነዋሪዎችና በተከራዮች ከኒፈጠሩ ችግሮች ይህ አንደኛው ሲሆን የተከራይና አከራይ ውል ሲጀመር እነዚህን ጉዳዮች ስለመፍታት ስምምነት መደረግ አለበት።

በተከራይና አከራይ ውል ላይ ሌላ አብሮ ማስገባት ድረግ

ይህ አንድ ተከራይ (ዋና ተከራይ ይባላል) የኮንትራት ውሉን በሞላ ሳይሆን በከፊል ለሌላ ሰው ሲያስተላልፍ ነው። በዋናው ተከራይ ያለው ኮንትራት ውል ከማለቁ በፊት ምናልባት አንድ ክፍል ለሌላ ማከራየት ወይም ለተወሰነ ጊዜ ሁሉንም ንብረት ለሌላ ሰው ማከራየት ይቻላል።

ለሌላ ማከራየት ቅንጅት በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ (Residential Tenancies Act 1997) ውስጥ የተካተተ ነው: ዋና ተከራዩ እንደ ባለንብረት ይሆናል፣ አብሮ ተከራይ ደግሞ እንደ ተከራይ ይሆናል። በአብሮ ተከራይ ለሚደርስ ችግርና በባለንብረቱ ላይ ለሚደርስ ኪሳራ ዋናው ተከራይ ሀላፊነት ሊሆን ይችላል። በዚህን ጊዜ ለባለንብረቱ የሚኖራቸው ሀላፊነት አንድ ዓይነት ይሆናል።

በተከራይና አከራይ ውል ላይ ሌላ አብሮ ማስገባት ከአብሮ ተከራይና አከራይ ውል ጋር ሊቃረን የሚችል እንደሚከተለው ይሆናል:

  • አብሮ ተከራይ በክፍሉ ወይም በተወሰነ ንብረት ላይ ‘ለመገልገል መብት’ ይኖረዋል
  • የቤት ኪራይና/ወይም የማስያዣ ገንዘቡ ደረሰኞች በአንድ ተከራይ ስም ብቻ መሆን
  • አንደኛው ተከራይ ከሌላው(ዎቹ) ተከራይ የቤት ኪራይ ወስዶ ለባለንብረቱ መክፈል
  • ከባለንብረቱ ጋር የሚደረጉ ድርድሮች ሁሉ አንድ ተካራይ ሃላፊ ሲሆን
  • ከሌላው(ዎቹ) ተከራይ አንደኛው ቀድሞ የገባና የማስያዣ ገንዘብ ቀድሞ ለተካራዩ መክፈል
  • አንድ ተከራይ ከባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ጋር የጽሁፍ ስምምነት መፈረምና ሌላው(ዎቹ) አለመፈረም።

 

ባለንብረቱ በጽሁፍ ስምምነት ሳያደርግ ቀድሞ ተከራዩ ቤቱን ለሌላ ማስተላለፍ ወይም ከፊል የኪራይ ቤቱን ለሌላ ማከራየት አይችልም። ያለ ባለንብረቱ ጽሁፋዊ ፍቃድ የተደረገ የተከራይ ውል ዋጋ አይኖረውም። ይሁን እንጂ ባለንብረቱ ያለ በቂ ምክንያት ስምምነቱን ማዘግየትና መያዝ የለበትም፤ ስለዚህ ይህ አግባብ ስላልሆነ ተከራዩ ቤቱን ለሌላ ሰው ለማከራየት ትእዛዝ እንዲሰጥ ለቪክቶሪያ ሲቪል አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal)

ለመኖር ፈቃድ/Licence

በህጋዊ አባባል፤ ተከራይ ለመሆን የኪራይ ቤትን በሞላ ወይም በከፊል ላይ ‘ለሌላን ሳይጨምር የመጠቀም’ ያለው ሰው ነው። ነዋሪዎች ባሉበት ቤት ውስጥ ከገቡ እርስዎ እንደ ለመኖር ፈቃድ ያለው ሊቆጥሩ ስለሚችል በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ(Residential Tenancies Act 1997) መሰረት የተከራይ መብቶች አይኖርዎትም። ከባለንብረቱ ጋር በደባል የሚኖሩ ከሆነ እርስዎ እንደ ፈቃድ ያለው ነዋሪ ይቆጠራሉ። አንድ ክፍል ከተከራዩና በሩ መቆለፍ የሚችል ከሆነ እርስዎ እንደ ተከራይ ላይቆጠሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህ ለብቻው ለተከራይነት ለማስወጣት ብቁ ላይሆን ይችላል።

ፈቃድ ያለው ነዋሪ ያለውን ቅሬታ በአግባብ ንግድ አንቀጽ ህግ (Fair Trading Act 1999) መሰረት በልዩ ፍርድ ቤት ላይ የፍትሀ ብሄር ክስ ችሎት (Civil Claims List) እንዲታይ ማድረግ ሲችል ነገር ግን በዚህ ህግ አንቀጽ ያለ መከላከያ እንደ በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ (Residential Tenancies Act 1997) መሰረት የተከራይ መብቶች ጥሩ አይደለም።

ምክር ስለማግኘት

የተከራይ ማሕበር በደባል ቤት ነዋሪዎች መካከል ለሚፈጠር ክስ ምክር መስጠት አይችልም፤ ምክንያቱም ብዙዎች ሁኔታዎች በተከራይ ነዋሪዎች አንቀጽ ህግ 1997 ዓ.ም ላይ ስለማይካተቱና በተከራዮች መካከል ወገናዊነትን መውሰድ ስለማንችል ነው። ለዚህ ክርክር መፍትሄ ማስገኛ አንደኛው ዘዴ በክርክር መፍትሄ ማእከል (በክርክር መፍትሄ ማእከል) እርቅ ድርድር ሲሆን በስልክ 1300 372 888 መደወል ነው። ይሁን እንጂ ሁለቱም ተከራካሪ አካላት ለመሄድ መስማማት አለባቸው።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ስለመጀመር

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ ለሌላ ማስተላለፍና ለሌላ ማከራየት


Shared households | Amharic | May 2010

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept