እንዴት የመኖሪያ ቤት መፈለግና ማመልከት ይቻላል? ለተማሪ የመኖሪያ ቤት

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የመጠለያ ዝርዝሮች

መጠለያ የሚፈለግበት ብዙ ቦታዎች ሲኖር እንደሚፈልጉት የመጠለያ ዓይነት ይወሰናል። የተለያዩ መጠለያ ዓይነቶችን የት ማግኘት እንደሚቻል ከዚህ በሚከተለው ዝርዝር (ማስታወቂያ) ቀርቧል።

በቤት ማሳደሪያ

በአጠቃላይ ይህ መጠለያ በርስዎ ተቋም በኩል ይቀናጃል፤ ይሁን እንጂ የማቆያ አገልግሎት የሚያካሂዱ ብዙ በራሳቸው የሚመሩ ተወካዮች አሉ። (እነዚህን ተወካዮች ማግኘት የሚችሉት ከኢንተርኔት ‘በቪክቶሪያ ማሳደሪያ/homestay Victoria’ ስር ወይም በዋይት ፔጅስ የንግድ ሥራና መንግሥት (White Pages Business & Government) ተለፎን ማውጫ ላይ ነው።

በዩኒቨርሲቲ ካምፐስ መጠለያ

የርስዎን ተቋም ለተማሪ መኖሪያ ቤት አገልግሎት ማነጋገር ወይም ዝርዝሩብ በድረገጽ ላይ ማየት። ወይም በዋይት ፔጅስ የንግድ ሥራና መንግሥት ተለፎን ማውጫ ላይ በርስዎ ተቋም በሚለው ስር ማየት።

ለተማሪ ሆስተሎች

ለተማሪ የሆስቴል መጠለያ ማስታወቂያዎች ብዙ ጊዜ በኢንተርኔት፤ በዋይት ፔጅስ የንግድ ሥራና መንግሥት ተለፎን ማውጫ እና በርስዎ ተቋም በሚቀርብ ዌብሊንክ/ weblinks እና ጥራዝ ወረቀ በኩል ይወጣል።

በጋራ ክፍል መጠለያ ቤት

በጋራ ክፍል የመጠለያ ቤት ዝርዝር በጋዜጣ ላይ፣ በተማሪ ማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድና በድረገጽ፣ እንዲሁም በደባል የመኖሪያ መጠለያ ድረገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የግል ቤት ኪራይ

ከጓደኞች ጋር ተዳብሎ ለመኖር፤ ወይም ለብቻዎ ቤት ለመከራየት እቅድ ካለዎት በሚከተሉት በኩል የግል ቤት ኪራይ ማግኘት ይችላሉ:

 • የሚከራይ ዝርዝሮች– በንብረት ተወካይ በኩል ይቀርባሉ
 • ኢንተርኔት– የሚከራዩ ቤቶች ዝርዝር በንብረት ተወካዮች ድረገጽ እና በፍለጋ መሳሪያ (‘በቪክቶሪያ ንብረት (real estate Victoria)’ በሚል መፈለግ)
 • ጋዜጣዎች – The Age እና The Herald Sun ላይ ቅዳሜ በሚወጣ ማየት። እንዲሁም ለመኖር በፈለጉበት ሰፈር የአካባቢ ማህበረሰብ ጋዜጦች ላይ ማየት።

 

መዳበያ የመኖሪያ ቤት

በአሁን ጊዜ ተዳብሎ በሚኖርበት ቤት መግባት ከፈለጉ፤ ለክፍል ማስታወቂያዎች የሚያወጡ ብዙ ቦታዎች አሉ:

 • በማህበረሰብ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች – አንዳንድ ጊዜ በአካባቢ ሻሂ ቤትና የመጽሐፍ መደብር ይገኛሉ
 • ኢንተርኔት
 • በተማሪ መኖሪያ ቤት አገልግሎት – በማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ዝርዝሮች ይኖራቸዋል
 • በኮምፑተር መረጃ ባላቸው አንዳንድ ተቋማት – እነዚህን ለማግኘት ብዙጊዜ በተቋሙ መመዝገብ አለብህ
 • በጋዜጣዎች – The Age እና The Herald Sun ላይ ቅዳሜ በሚወጣ ማየት። እንዲሁም ለመኖር በፈለጉበት ሰፈር የአካባቢ ማህበረሰብ ጋዜጦች ላይ ማየት።

 

በግል የሚከራይ ቤት ማየትና ፍተሻ

ንብረቱን በሚያዩበት ጊዜ በቤት ውስጥና ውጭ ያሉትን በሚገባ መፈተሽ በጣም ጠቃሚ ነው። ምንም ዓይነት ፊርማ ወይም ክፍያ ከማድረግዎ በፊት በንብረቱ ላይ ደስተኛ ስለመሆንዎ ማረጋገጥ ነው።

እርስዎ በንብረት ላይ ጥገና መደረግ ያለበት ካለ መጠየቅ እንጂ ባለንብረቱ ወይም ይንብረት ተወካዩ መጥቶ ጥገና ያካሂዳል ብለው አይገምቱ።

በንብረቱ ላይ ተዘዋውረው በሚያዩበት ጊዜ የመብራት ማጥፊያ ማብሪያን ማየት፣ የአየር ማስወጫ ወይም ከራስ በላይ ላለ ማናፈሻ፣ ምድጃ፣ መጥበሻ፣ የቧንቧ መክፈቻ፣ የገላ መታጠቢያ (ለውሀ ግፊት) እንዲሁም ለማንኛውም ማሞቂያና የአየር ኮንዲሽን ስለመሥራቱ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ስልኩ ስለመቀጠሉ መጠየቅ። በቤቱ ላይ የተገጠሙት እንደ መጋረጃ ያሉት ጠንካራ ደህንነታቸው የተጠበቀ ስለመሆኑ ማረጋገጥ።

እንዲሁም መስኮቶች በሞላ መከፈትና መዘጋት እንዲሁ በሮች መቆለፍና መከፈት መቻላቸውን ማረጋገጥ። ምን ዓይነት መቆለፊያ እንደተገጠመ ማጣራት፤ ይህም በመስኮቶች ላይ መቆለፊያ ከሌለውና ከውጭ መግቢያ በሮች ላይ መቆለፊያ ከሌለው በስተቀር አብዛኛው የኢንሹራንስ ኩባንያ ለቤት እቃ ዋስትና አይሰጡም።

ንብረቱን በሚያዩበት ጊዜ ምን ማየት እንዳለብዎ Property inspection checklist (የንብረት መፈተሻ ዝርዝር ማጣሪያ) (ተማሪ መኖሪያ ቤት እውነታ ጽሁፍ ወረቀት) ይነግርዎታል።

በሆነ የንብረት ክፍል ላይ ወይም በተገጠሙት ወይም ገጽታ ላይ ጉዳት ካለ ወይም በደንብ የማይሰራ ከሆነ እንዲያጠግናቸው ለባለንብረቱ መጠየቅ ያስፈልጋል።

ለግል የኪራይ ቤት ስለማመልከት

ንብረቱን ተዘዋውረው ካዩት በኋላ ለመግባት ከመወሰኑ በንብረት ተወካዩ (ባለንብረት ተወካይ የሚጠቀም ከሆነ) የሚሰጥ ማመልከቻ ቅጽ መሙላት አለብዎ።

ስለርስዎ ጥያቄዎችን ሊጠየቁ ይችላሉ:

 • ገቢ ምንጭና የባንክ ዝርዝር
 • ቀደም ሲል የነበረ የተከራይ ታሪክ
 • የሥራና ቀጣሪ ዝርዝርና ታሪክ
 • ምስክርነት የሚሰጥ– ሁለት ሊጠየቁ ይችላሉ

 

ስለርስዎ መጠየቅ የማይችሉት:

 • ዘር
 • የጋብቻ ሁኔታ
 • የአካል ጉዳተኛ ወይም ጎደሎ
 • ወሲባዊ አገላለጽ
 • ሃይማኖት ወይም የፖለቲካ እምነቶች

 

ለማመልከቻ የሚቀመጥ ማስያዣ

በንብረት ተወካይ ወይም በባለንብረት ለማመልከቻ ማስያዣ እንዲቀመጥ ይጠይቃል። ማስያዣ የሚያስቀምጡ ከሆነ ደረስኝ ስለመውሰድዎ ያረጋግጡ። ተቀማጭ ገንዘቡ ለርስዎ መመለስ አለበት።

ተወካዮችና ባለንብረቶች ለሚከተሉት ማስከፈል ህገ-ወጥነት ነው:

 • ንብረቱን እንዲያዩና እንዲፈትሹ ስለፈቀዱ
 • በንብረቱ ላይ ሲገቡ ቁልፎችን ስለሰጡ
 • ንብረቱን ስላከራዩ ኮሚሽን ወይም ክፍያ
 • የቤት ኪራይ መክፈያ ካርድ ስለሰጡ
 • በቀጥታ ለመክፈል ቅንጅት በማድረግ

 

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

የግል ንብረት/ real estate አህጽሮት ቃል ምን ያመለክታል?
ከመግባቴ በፊት ማወቅ ያለብኝ ምንድ ነው? (በግል ኪራይ ቤትና በደባል መኖሪያ ቤት) ለተማሪ የመኖሪያ ቤት
ከመግባቴ በፊት ማወቅ ያለብኝ ምንድ ነው? (በደባል መኖሪያ ቤት) ለተማሪ የመኖሪያ ቤት
እውነታ ጽሁፍ ወረቀት
ጥገናዎች
የንብርት ፍተሻ ማረጋገጫ ዝርዝር: ለተማሪ የመኖሪያ ቤት (PDF)

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


How do I find and apply for housing? | Amharic | May 2010

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept