ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ካሳ ለተከራዮች

ኣከራይዎ በክራይ ስምምነት (lease) ወይም በ የኪራይ ቤቶች ደንብ 1997 (Residential Tenancies Act) መሰረት ሊያደርግዋቸው የሚገቡ ሃላፊነቶችን ካልተወጡ፣ እርስዎ ለ የቪክቶሪያ የሲቪል እና ኣስተዳደር ፍርድቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal)  ለካሳ ማመልከት ይችላሉ።

ካሳ ሲጠይቁ፥ ጉዳት እንደደረሰብዎት (ምሳ የተበላሹ እቃዎች፣ የጠፉ እቃዎች፣ የጠፋ ገንዘብ) ወይም ከፍተኛ ኣለመመቸት (ምሳ፣ ቤትዎን ለመጠቀም ኣለመቻል)፣ እንዲሁም ይህ የኣከራዩ ወይም የተወካዩ ስራ ወይም ካለ መስራት የተነሳ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ኣለብዎት።

መቼ እና ምን መጠየቅ ይችላሉ?

የጊዜ ገደብ

ካሳ ለማመልከት ከፈለጉበት ብልሽት ከደረሰ እለት እስከ 6 ኣመታት ኣለዎት። በዚህ 6 ኣመት ገደብ ውስጥ እስካሉ ድረስ በክራይዎ ወቅት ወይም ከዚያ በኋላ ማመልከት ይችላሉ።

ለመጠየቅ ምክንያቶች

በፍርድ ቤቱ ካሳ መጠየቅ የሚችሉበት ሁኔታዎች ጥቂት ምሳሌዎች፤

  • ኣከራዩ እርስዎ የነገርዋቸውን ችግር (ምሳ የሚያፈስ ጣራ) ያልጠገኑ እንደሆነ
  • ኣከራዩ  በህገወጥ መንገድ ካስወጥዎ ወይም በህገወጥ መንገድ ሊያስዎጣዎ ከሞከረ
  • ኣከራዩ የኪራይ ቤትዎን ‘የጸጥታ ቦታን’ የረበሸ እንደሆነ (ምሳ ኣከራዩ  ወይም ወኪሉ ያለ ማስጥንቀቂያ  ወይም/እና ያለ በቂ በደንቡ ስር በተዘረዘሩ ምክንያት መምጣት ካበዙ)
  • ለመከራየት የገቡ ጊዜ ቦታው በተገቢ ሁኔታ ያልጸዳ ከሆነ

 

ፍርድ ቤቱ ምን ያህል ካሳ እንደሚያገኙ ለመፍረድ እንዲወስን እርስዎ  ጉዳቱን ለመከላከል ያደረጉትን ማንኛውንም ነገር ግምት ውስጥ እንደሚያስገባ ሊገነዘቡ ይገባል። ይህ ማለት እርስዎ ሊያደርሱት የሚችሉትን ዋጋ ለመቀነስ ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ ኣለብዎት። እንዲሁም ኣከራዩ ችግሮቹን እንዲያስተካክል ለማድረግ ለመሞከር እርምጃዎችን መውሰድ ኣለብዎት፣ እንደ ያቀረቡትን ጥያቄዎች ካልተከናወኑ ክትትል ማድረግ ያለ።

የመኖርያ ቤቶች ኪራይ ደንብ 1997 መሰረት ፍርድ ቤቱ $ 10 000 የካሳ ወሰን ኣለው። ። ከ $ 10 000 በላይ ለመጠየቅ የፈለጉ እንደሆን የኣከራዩ ፈቃድ ያስፈልግዎታል፣ ወይም ማመልከቻዎን ለ ያገር ዳኛ ፍርድ ቤት (Magistrates’ Court) ማድረግ ይችላሉ። ባማራጩ፣ ጥያቄዎን ገደብየለሽ የገንዘብ ፍርድ ላለው በ የኣውስትራሊያ  ተጠቃሚ ህግ እና ተገቢ ንግድ ደንብ 2012 (ቪክ)(Australian Consumer Law and Fair Trading Act 2012 (Vic)) ስር ማድረግ ይችላሉ።

የ ህመም፣ የስቃይ፣ የኣካል ጉዳት ወይም ሞት ካሳ የፈለጉ እንደሆነ፣ የግለሰብ ጉዳት ጠበቃ (Personal Injury Lawyer) መገናኘት ኣለቦት።

ለ የግል ጉዳት በሌላ ህግ ስር መጠየቅ ይችላሉ—በ የኪራይ ቤቶች ደንብ 1997 (Residential Tenancies Act) ግን ያልሆነ—ስለዚህ የሚወስዱዋቸው እርምጃዎች የተለዩ  ይሆናሉ። ትክክለኛውን ጠበቃ ማግኘት (Finding the right lawyer) (FCLC ድህረ ገፅ) ወይም ጠበቃ ያግኙ (Find a lawyer) (LIV ድህረ ገፅ) ይመልከቱ

ጥገናዎች

በጣም የተለመደው ያካሳ ጉዳይ ኣከራዩ ጥገናዎችን ከማከናወን ያልተወጣ እንደሆነ  ነው። የካሳ ጥያቄ ከማቅረብዎ በፊት ጥገናዎች እስከሚደረጉ ድረስ በጠበቅ መልካም ሃሳብ ነው፥ ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ በመጨመር ላይ ያሉ የካሳ ጉዳዮችን ሁል ጊዜ ስለማይሰማ ነው። ነገር ግን፣ ለኣከራይዎ የካሳ ጥያቄ ለማቅረብ ሃሳብ እንዳለዎ ሊያሳውቁት ይገባል፣ እንዲሁም ጥገናዎቹን ከማድረግ በዘገዩ መጠን እርስዎም የሚጠይቁትንም ሊያበዙት ይችላሉ። ይህ ኣንዳንዴ ኣከራዩ ጥገናዎችን በፍጥነት እንዲያከናውን ሊገፋፉው ይችላል።

እንዲሁም በ ቪሲኤቲ (VCAT)በኩልም ኣከራዩ ጥገናዎችን እንዲያጠናቅቅ ትእዛዛት የመሻት እርምጃዎች እንዲወስዱ እንመክራለን። እርስዎ ከቪሲኤቲ (VCAT) የመጠገን ትእዛዛት ካልፈለጉ ቪሲኤቲ ጥገናው ላልተደረገበት ጊዜ ሁሉ ኣከራዩ ካሳ እንዲከፍልዎ ለማዘዝ ያመነታ ይሆናል።

እንዴት እንደሚጠይቁ

እርስዎ  በ የኪራይ ቤቶች ደንብ 1997 (Residential Tenancies Act) መሰረት ሃላፊነትን ባለመወጣት ካሳ ለመጠየቅ የፈለጉ እንደሆነ እናም እስካሁንም በቤቱ ውስጥ ያሉ እንደሆነ፥ ለኣከራዩ ሃላፊነትን ያለመወጣት ማስታወቂያ (Notice for Breach of Duty) ሊሰጡት ይገባል (በ የተጠቃሚዎች ጉዳይ ቪክቶሪያ  (Consumer Affairs Victoria  website) ድረ ገፅ ይገኛል)።

ሃላፊነትን ያለመወጣት ማስታወቂያ (Notice for Breach of Duty) ሲሞሉ ማካተት ያለብዎት፣

 

  • የኣከራዩ  ስም (የወኪሉ ስም ሳይሆን)
  • ኣከራዩ  ያልፈጸሙትን ነገር ዝርዝር (ያደረጉትን ስህተት)
  • ኣከራዩ  ችግሩን ለማስተካከል ማድረግ ያለባቸው ድርጊቶች (ምሳ ጣራውን መጠገን)
  • እርስዎ ለጠፋ ወይም ለብልሽት የሚጠይቁት ካሳ (ምሳ ልብሶችን የማፅጃ ዋጋ እና ጣራው በማፍሰሱ ምክንያት የረጠቡ ወይም የቆሸሹ እቃዎች) ወይም ጣራው በማፍሰሱ ምክንያት እርስዎ የደረሰብዎት ኣለመመቻቸት (ምሳ ጣራው ባፈሰሰበት ወቅት ጓደኛዎ ቤት የቆዩበት)
  • ለማንኛውም ሊጠገን የማይችል ነገር (ምሳ በጣራው በኩል በፈሰሰ ውሃ በንብረትዎ ላይ ለደረሰ ብልሽት) የሚጠይቁት ገንዘብ መጠን

ኣስፈላጊ ባይሆንም፣ የ ሃላፊነትን ያለመወጣት ማስታወቅያ (Breach of Duty Notice) ላይ ማስረጃዎችን ማያያዝ ኣለብዎት፣ ይህ በውሃላ ለፍርድ ቤቱ ሊቀርብ ይገባዋልና። ማስረጃዎ ባስተማማኝ ሁኔታ መቀመጡን እና መቀዳቱን ያረጋግጡ።

ብዛት ላላቸው ነገሮች በኣንድ ቅፅ መጠየቅ ይችላሉ። ተጨማሪ ቦታ ያስፈለግዎ እንደሆነ ተጨማሪ ገፅ ያያይዙ። እርስዎ ለ ኣለመመቻቸት ጥያቄ ማቅረብ ከፈለጉ (ይህም ቦታውን ሙሉ ጥቅሙን መጠቀም ያልቻሉ እንደሆነ)፣ ለዚህ የገንዘብ መጠን ማስቀመጥ ያስፈልግዎታል። በችሎቱ ወቅት የጠየቁትን መጠን ማስረዳት እና ለያንዳንዱ ነገር የጥያቄዎን ማስረጃ ማቅረብ መቻል ኣለብዎት።

የ ኣለመመቻቸት ጥያቄዎን  ለማስላት፥ የዕለት ኪራይዎን ከመቶ መጠን (ፐርሰንቴጅ) ያስሉና (ቤቱ በተጎዳበት መጠን መሰረት) ይህንን ችግሩን ባሳለፉበት ቀናት ቁጥር ያባዙት። ምን ያህል መጠየቅ እንዳለብዎ  ለማስላት እገዛ የፈለጉ እንደሆነ፣ ይገናኙን።

ሃላፊነትን ያለመወጣት ማስታወቂያ (Notice for Breach of Duty) ቅጂ ለኣከራዩ  ወይም ለወኪሉ ይስጡ እንዲሁም ለራስዎ ኣንድ ቅጂ ይያዙ። ማስታወቂያውን በተራ ደብዳቤ ወይም ኢሜይል መላክ ይችላሉ (ኣከራዩ ወይም ወኪሉ በኢሜይል ማስታወቂያዎች እንዲሰጡ የተስማሙ ከሆነ) ነገር ግን እንደደረሳቸው ማስረጃ ይሆንዎ ዘንድ በተመዘገበ ደብዳቤ ወይም እራስዎ በኣካል እንዲሰጥዋቸው እንመክራለን። የኢሜይልዎን ደረሰኝ ያስቀምጡ። እርስዎ ማስታወቂያውን በኢሜል የላኩ ከሆነ፣ በኣከራዩ ወይም በንብረት ወኪሉ የተሰጠ የኢሜይል አድራሻ መሆኑን ያረጋግጡ እናም ከተቻለ የመነበቡን ደረሰኝ ይጠይቁ። ከዛም ኣከራዩ  ካሳውን ይከፍልዎት እንደሆነ ለማየት 14 ቀናት መጠበቅ ኣለብዎት። በደብዳቤ የላኩት እንደሆነ፣ ደብዳቤው እንዲደርስ ተጨማሪ ቀናት መጠበቅ ያስፈልግዎታል። ኣውስትራሊያ ፖስጣ የማድረስ ጊዜያትን ይመልከቱ።

ኣከራዩ  ካልከፈለ፣ ለ ቪክቶሪያን ሲቪል እና ኣስተዳደር ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከት ይችላሉ። የ ቪሲኤቲ (VCAT) ቅፅ ይሙሉና ሃላፊነትን ያለመወጣት ማስታወቂያ (Notice for Breach of Duty) ቅጂ  ያያይዙ። የ ቪሲኤቲ (VCAT) ማመልከቻ ክፍያ መክፈል ይኖርቦት ይሆናል እንዲሁም የማመልከቻውን ክፍያ እንዲመስልዎት በማመልከቻዎ ላይ መጠየቅ ኣለብዎት። ማንኛውም የማመልከቻ ክፍያ መመለስ ውሳኔ የፍርድ ቤቱ ሲሆን በፍርዱ ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።

ከቤቱ ለቀው የወጡ እንደሆነ

ቤቱን ለቀው ከወጡ በኋላ የካሳ ጥያቄ ለማድረግ የፈለጉ እንደሆነ፣ ሃላፊነትን ያለመወጣት ማስታወቂያ (Notice for Breach of Duty) መስጠት ኣያስፈልግዎትም። እርስዎ  በቀላሉ የ ቪክቶሪያን ሲቪል እና ኣስተዳደር ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከቻ ቅፅ መሙላት ይኖርብዎታል። በማመልከቻ ቅፁ ላይ ምን ያህል ካሳ እንደሚጠይቁና ለምን እንደሚጠይቁት መግለፅ ኣለብዎት።

ከማመልከትዎ በፊት ጉዳዩን ፍርድ ቤት ከመሄድ በፊት ለመስማማት ይቻል እንደሆነ  ለማየት ለኣከራዩ ቢፅፉለት መልካም ሃሳብ ነው። በደብዳቤዎ  ውስጥ በተወሰነ ጊዜ ለምሳሌ 14 ቀናት ውስጥ ለምክፈል ካልተስማሙ ለቪክቶሪያን ሲቪል እና ኣስተዳደር ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) እንደሚያመለክቱ መግለፅ ኣለብዎት። የደብዳቤውን ቅጂ ያስቀምጡ በፍርድ ቤቱ እንደማስረጃ ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ።

በኣብዛኛዎች ጉዳዮች፣ ኣከራዩ በ የውል መያዣዎ ላይ ጥያቄ ያቀርባል፣ ለካሳዎ ምላሽ ጥያቄ (counter claim) ማቅረብ ተገቢ ይሆን ይሆናል። በዚህ መንገድ በሁለት ችሎት ምትክ ሁለቱም ጥያቄዎች ባንድ ጊዜ  ይወሰናሉ። እንዲሁም ከተሳካሎት ኣብዛኛውን የውል መያዣዎን መልሰው ያገኙ ይሆናል።

ጥያቄዎን ማረጋገጥ

በፍርድ ቤቱ ለካሳ ካመለከቱ፣ ለችሎቱ  መሄድ እና ጉዳይዎን ማረጋገጥ ኣለብዎት። ኣከራይዩ ማድረግ የሚገባውን ሃላፊነት ያለመወጣቻቸውን እና በሱም ምክንያት እርስዎ  እጦት እና/ወይም ብልሽት እንዳጋጠምዎ ለፍርድ ቤቱ ማሳመን ይገባዎታል።

ማስረጃ (ምሳ ፎቶግራፍ፣ ምስክር፣ ለኣከራይዎ ወይም ወኪሉ የፃፏቸው ደብዳቤዎች፣ ለተበላሹ እቃዎች የማሳደሻ ወጪ ወይም ተመን ደረሰኝ)ያስፈልግዎታል።

እንዲሁም የካሳዎን ጥያቄ  እንዴት እንዳሰሉት ለፍርድ ቤቱ ማብራራት መቻል ኣለብዎት።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የታተመ: ጁን 2017

Compensation | Amharic | June 2017


Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept