ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ለተከራዩ  ቤቶች ጥገናዎች

አከራዮች በ የመኖርያ ቤት የኪራይ ደንብ (Residential Tenancies Act) 1997 መሰረት የሚያከራዩት ቤት በ መልካም ጥገና  እንደተጠበቀ  ማረጋገጥ ኣለባቸው። ይህ በተጨማሪም የኣከራይ  የሆኑ ወይም የሚተዳደሩ የጋራ ቦታዎችንም ይመለከታል።

የእርስዎ  የኪራይት ጥገናዎች የሚያስፈልገው ከሆነ የመኖርያ ቤት የኪራይ ደንብ (Residential Tenancies Act) 1997 ውስጥ የተጠቀሱትን ደረጃዎች መከተል ይገባዋል። ህጉ ሁለት የተለያዩ የጥገናዎች ኣሰራሮች ያቀርባል፣ ሳንድ ለ አስቸኳይ ጥገናዎች  እንዲሁም ሌላ ለ አስቸኳይ ላልሆኑ ወይም አጠቃላይ ጥገናዎች።

የኣየር ማቀዝቀዣዎች

የኛን የኣየር ማቀዝቀዣ ጥገናዎችንገጽ ይመልከቱ።

አስቸኳይ ጥገናዎች

የ ኣከራይ  አስቸኳይ ጥገናዎችን ወዲያውኑ መፈፀም ኣለበት። የእርስዎ የኪራይ ወቅት መጀመሪያ ላይ፣ ኣከራይ ወይም የንብረት ወኪሉ አስቸኳይ ጥገናዎች ያስፈለገ  እንደሁነ ሊያገኙዋቸው የሚችሉበትን የስልክ ቁጥር ሊሰጥዎ ይገባል።

ለአስቸኳይ ጥገናዎች የሚሆኑ ምክሮች

አስቸኳይ ነው ብለው ቢያስቡም፣ ህጉ ላይፈቅድ ይችላል፡፡
በአስቸኳይ ዝርዝር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፤ ወደ አከራይ ወይ በቀጥታ ይደውሉ፡፡ ከሰዓታት በኃላም ቢሆን
እነርሱን ለማግኘት ጥረት ያደረጉበት ቀን፣ ሰዓት እና ማንኛውንም ነገር መጻፍዎ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
የችግሩን ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ያንሱ፡፡
በቀጥታ መልስ ካልሰጡ ጥገናውን ለማድረግ ክፍያ መክፈል ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአስቸኳይ ዝርዝር ካለ ብቻ ነውው፡
አከራዩ ምክንያታዊ ወጪዎችን በ14 ቀናት Gእስከ ST ጨምሮ $1800 ሊከፍልዎት የገባል- ደረሰኝ እና በጽሁፍ ማስተዋቅያን ከላኩ፡፡
ለጥገናዎች መክፈል ካልፈለጉ ወይ ዋጋው ከ$1800 በላይ ቢሆን ከዛ ይልቅ VCAT ማመልከት ይችላሉ፡፡
አስቸኳይ ጥገናዎች ሲሆኑ VCAT በ2 የስራ ቀናት ይመለከታል፡፡
ኪራይ መክፈልዎን አያቁሙ! የኪራይ ገንዘብ ለጥገናዎች ክፍያ አይጠቀሙበት፡፡
ኪራይዎን ካልከፈሉ አከራዩ ሊያስወጣዎት ይችላል፡፡
ራስዎን አይጠግኑ ዳግም እንዲሰሩ ለማድረግ ክፍያዎን ማቆም ይችላሉ፡፡
ጥገናዎቹ ካልተደረጉ ወይ ለመስራት ብዙ ጊዜ ከፈጁ ከአከራዩ ካሳ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

አስቸኳይ ጥገናዎች በአንቀጽ ህጉ ስር የተገለጹ ናቸው:

 • ፍንጥቅ ብሎ ለወጣ ውሃ አገልግሎት
 •   የተደፈነ ወይም የተሰበረ የሽንት ቤት
 • በከባድ የሚያንጠባጥብ ጣራ
 • የሚያስተነፍስ ጋዝ
 • አደገኛ የኤሌትሪክ ብልሽት
 • ጎርፍ ወይም ከባድ የጎርፍ ጉዳት
 • ከባድ አውሎ ነፋስ ወይም የእሳት ጉዳት
 •   ኣከራይ ወይም ባለቤቱ የሚያቀርበው ኣስፈላጊ ኣገልግሎት ወይም ቁሳቁስ ለ ውሃ፣ ሙቅ ውሃ፣ የምግብ ማብሰያ፣ ማሞቂያ ወይም የልብስ ማጠቢያ የተበላሸ ወይም የተሰበረ
 • ኣከራይ ወይም ባለቤቱ የሚያቀርበው ማንኛውም እቃ ወይም ቁስ ተበላሽቶ  ወይም ተሰብሮ  ብዛት ያለው ውሃ እንዲባክን ያደረገ እንደሆን
 • የጋዝ፣ ኤሌትሪክ ወይም የውሀ አቅርቦት  አለመቻል ወይም መሰበር
 • ኣሳንሰር ወይም ደረጃ ላይ ከፍተኛ ብልሽት
 • ንብረቱን አደገኛ ወይም ያላስተማማኝ የሚያደርግ ማንኛውም ብልሽት ወይም ጉዳት

 

እርስዎ  ኣስቸኳይ ጥገና ያስፈለግዎት እንደሆነ፣ ለኣከራዩ  በፅሁፍ ማሳወቅ ኣያስፈልግዎትም ነገር ግን በራስዎ ጥገና ለማስደረግ ከመሞከርዎ በፊት  ኣከራዩን ወይም ወኪሉን ለማግኘት ሙከራ ማድረግ ኣለብዎ በ ኣከራይ ወይም ወኪል ጥገናዎችን ለማስፈፀም የወሰደዋቸውን እርምጃዎች በሙሉ መዝግበው ይያዙ (ለምሣሌ የስልክ ጥሪዎች፥ ኢሜይሎች፥ጊዜ እና ቀኖች  ዝርዝር)  ኣከራይዎን ወይም ወኪሉንል ማግኘት ካልቻሉ ወይም ወዲያውኑ ምላሽ ያልሰጥዎት ከሆነ፣ እርስዎ እስከ $ 1800 (GST ጨምሮ) ዶላር-  የሚያስወጡ ጥገናዎች እንዲደረጉ የራስዎን ማመቻቸት ማድረግ ይችላሉ። ወጪው ተቀባይነት ያለው መሆን ይኖርበታል ስለዚህ ጥቂት የዋጋ ግምቶች እንዲኖርዎት ይሻሉ። ገንዘቡን መልሶ  ለማግኘት፥ ማስታወቂያ ለኣከራዩ  (Notice to Landlord) የተደረጉትን ጠገናዎች በመግለፅ እና ምን ያህል እንዳስወጡ በመግለፅ ይላኩ፥ ደረሰኝዎችንም ያያይዙ።  ኣከራዩ ማስታወቂያው በደረሰው በ 14 ቀናት ውስጥ ገንዘብዎን መመለስ ይኖርበታል።     ይሁን እንጂ፥ አስቸኳይ ጥገናዎች እንዲደረግ ኣመቻችተው የነበረ ከሆነ እና ዋጋው (GST ጨምሮ) ከ $ 1800 በላይ ከነበረ ኣከራይ እስከ $ 1800 ብቻ ተጠያቂ መሆኑን ማሰብ የገባዎታል። ኣከራይ በ 14 ቀናት ውስጥ ካሣ ያልከፈለ ከሆነ፣ እነሱ ይህን እንዲያደረጉ የሚያዝ ትእዛዝ ለ ቪሲኤቲ ማመልከት ይችላሉ።

እርስዎ ለኣስቸቋ አስቸኳይ ጥገናዎች ራስዎ መክፈል የማይችሉ ከሆነ፣ጥገናዎቹ ከ$ 1800 በላእ የሚያስወጡ ከሆነ፣ ወይም በቀላሉ ጥገናዎቹን እንዲያደርግ ኣከራዩን ማግኘት ካልቻሉ፣  የ ኣከራይ ጥገናዎቹን እንዲያከናውን ትእዛዝ ለ የቪክቶሪያ ሲቪል እና ማስተዳደርያ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከት ይችላሉ። ልዩ ፍርድ ቤቱ በ 2 የሥራ ቀናት ውስጥ የአስቸኳይ ጥገናዎች  ማመልከቻዎችን  መስማት አለበት።

የኪራይ ገንዘብዎን ከኣከራዩ ኣይያዙበት ወይም ጥገናዎች ለማስፈጸም የ ኪራይ ገንዘብን አይጠቀሙ። በእርስዎ ኪራይ ከበክፈል በ 14 ቀናት የዘገዩ  እንደሆነ ኣከራይ ቤቱን እንዲለቁ የ 14 ቀን ማስታወቂያ ጋር መስጠት ይችላል።

አስቸኳይ ያልሆኑ (አጠቃላይ) ጥገናዎች

አንድ ጥገና ‘አስቸኳይ’ ከተባሉት ምድቦች በአንዱ ውስጥ ሊካተት ካልቻለ፥  ከኣከራይ ለዚህ እንደሚከፍል የፅሁፍ ስምምነት ካላገኙ በስተቀር በእራስዎ እንዲደረግ ማመቻቸት የለብዎትም።  አስቸኳይ ባልሆኑ ጥገናዎች ሂደት ውስጥ 3 ደረጃዎች አሉ፤

1. ማስታወቂያ ለ ኣከራይ

ማናቸውም ኣስፈላጊ ኣጠቃላይ ጥገናዎችን በ ማስታወቂያ ለኣከራይ (Notice to Landlord) ቅፅ ላይ ይዝርዝሩዋቸው።     ይህ ማስታወቂያ የዘረዘሯቸው ሁሉ ነገሮች በሙሉ በ 14 ቀናት ውስጥ መጠገን እንዳለባቸው ለ ኣከራይ ያሳውቃል። ቅፁ ለኣከራዩ እንጂ ለንብረት ተወካዩ  እንዳልተላከ ያረጋግጡ፣ በርግጥ በወኪሉ በኩል ለኣከራዩ  ሊላክ ይቻላል። (የህዝብ ተከራይ ከሆኑ፣  ኣከራይዋ  የቤቶች ጉዳይ ሃላፊ (Director of Housing) ነው።) ለ ኣከራዩ  ወይም ወኪሉ አንድ ቅጂ ይስጡ እና ለራስዎ አንድ ቅጂ ያስቀምጡ። ማስታወቂያውን በተራ ደብዳቤ ወይም ኢሜይል መላክ ይችላሉ (ኣከራዩ ወይም ወኪሉ በኢሜይል ማስታወቂያዎች እንዲሰጡ የተስማሙ ከሆነ) ነገር ግን እንደደረሳቸው ማስረጃ ይሆንዎ ዘንድ በተመዘገበ ደብዳቤ ወይም እራስዎ በኣካል እንዲሰጥዋቸው እንመክራለን። የኢሜይልዎን ደረሰኝ ያስቀምጡ። እርስዎ ማስታወቂያውን በኢሜል የላኩ ከሆነ፣ በኣከራዩ ወይም በንብረት ወኪሉ የተሰጠ የኢሜይል አድራሻ መሆኑን ያረጋግጡ እናም ከተቻለ የመነበቡን ደረሰኝ ይጠይቁ።

ከ ኣከራዩ  ካሳ ለመፈለግ ኣቅደው ከሆነ፣  በዚያው ጊዜ ሃላፊነትን ባለማከናውን(Breach of Duty) ማስታወቂያ መላክ ኣለብዎት።

2. ለተጠቃሚ ጉዳይ (Consumer Affairs) ጥያቄ ማቅረብ

ኣከራዩ  ማስታወቂያው በደረሰው በ 14 ቀናት ውስጥ ጥገናውን ካላከናወነ፣ ወይም ጠገናዎቹን በኣጥጋቢ ደረጃ ካልሰራ፣ ለተጠቃሚ ጉዳዮች ቪክቶሪያ (Consumer Affairs Victoria) ግምገማ እንዲደረግ ‘የጥገናዎች ግምገማ ጥያቄ’ (Request for repairs Inspection) ወይም ‘የኪራይ ግምገማ’ (Rent Assessment) ቅፅ በመጠቀም መጠየቅ ይችላሉጠቃሚ ጉዳዮች ቪክቶሪያ (Consumer Affairs Victoria) ህረ ገፅ) ተቆጣጣሪ ቤቱን ለመገምገም ለማመቻቸት ይገናኝዎታል። ከግምገማው በኋላ እነርሱ ኣከራዩን ወይም ወኪሉን በመገናኘት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥገናዎች እንዲከናወኑ ሊደራደሩ ይሞክሩ ይሆናል። ተቆጣጣሪውም  አስፈላጊ የሆኑ ጥገናዎች የሚገልፅ ሪፖርት መጻፍ እና ልርስዎም ቅጂ መስጥት አለበት

3. ፍርድ ቤት ማመልከቻ

እርስዎ የተቆጣጣሪውን ሪፖርት ቅጂ ኣንዴ እንደያዙ፣ የፍርድቤት ጉዳይ ለ የቪክቶሪያ ሲቪል እና ማስተዳደርያ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከት ይችላሉ። አርስዎ ሪፖርቱ እንደደረስዎ በ 60 ቀናት ውስጥ ማመልከት አለቦት፣ ነገር ግን በ 90 ቀናት ውስጥ አንድ ቅጂ ያላገኙ ከሆነ ያለሱ ለልዩ ፍርድ ቤት ማመልከት ይችላሉ። ከፍርድ ቤቱ ማመልከቻ ጋር የተቆጣጣሪውን ሪፖርት ቅጂ ያያይዙ። ፍርድ ቤቱ ኣከራዩ ጥገናዎችንእንዲያከናውን ለማዘዝ ይችላል፡

የኪራይ ልዩ ሂሳብ (Rent Special Account)

ኣከራዩ ጥገናዎቹን ማከናዎን ካቃተው እርስዎ ኪራይዎ ወደ የኪራይ ልዩ ሂሳብ (Rent Special Account) እንዲከፍሉ ለፍርድ ቤቱማመልከት ይችላሉ። ይህ ሁለቱንም አስቸኳይ የሆኑ እና አስቸኳይ ያልሆኑ ጥገናዎች ይመለከታል።  ኣብዛኛውን ጊዜ  ፍርድ ቤቱ ክፍያው ለ የኪራይ ልዩ ሂሳብ (Rent Special Account) እንዲደረግ የሚያዘው ኣከራዩ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ጥገናዎች ማድረግን ካላከበረ ነው።

ካሳ

እርስዎ ችግር ከደረሰብዎት እና/ዎይም  ቁሳቁስዎ  ከተበላሸ ለካሳ  ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ መክንያቱም ኣከራዩ ከ፤

 

 • አስቸኳይ ጥገናዎችን ወዲያውኑ ካላከናወነ
 • አጠቃላይ ጥገናዎችን ውስጥ በ 14 ቀናት ውስጥ ካላካሄደ
 • በ መልካም ጥገና ውስጥ ቤቱን ካልጠበቀ

ጉዳት በተከራዮች

በእርስዎ  ወይም በ እርስዎ እቤትዎ እንዲመጣ በጋበዙት ሰው በደረሰ ጉዳት መክንያት ጥገ ናዎች ካስፈለጉ፥ እርስዎ ለጥገናዎች መክፈል ሊኖርብዎ ይችላል እንዲሁም እራስዎ  ሊያቀንባብርዋቸው ይሆናል። ኣከራዩ ወይም ወኪሉ ግዴታ በመጣስ (Breach of Duty ) ወይም ‘የጥገና ማስታወቂያ’ (repair notice) እርስዎን በ 14 ቀናት ውስጥ ብልሽቱን እንዲጠግኑ በሚያስገድድ ክስ ሊከስዎ  ይችላሉ።     እርስዎ የማያከናውኑ ከሆነ፣ እነርሱጥገናዎች ይደረጉ ዘንድ ሊያመቻቹ እና ለርስዎ ጥገናዎቹ ምን ያህል ወጪ እንዳስዎጡ የሚገልፅ ተጨማሪ ማስታወቂያ  ሊልኩልዎት እና ለጥገናዎቹን ወጪ ሃላፊ ሊሆኑ ይችላሉ። እርስዎ ካልከፈሉ፥  ኣከራዩ  እርስዎ  እንዲከፍሉ ትእዛዝ እንዲሰጥ ለልዩ ፍርድ ቤቱ ማመልከት ይችላል። እርስዎ ለብልሽቱ ተጠያቂ መሆንዎን ማረጋገጥ የኣከራዩ ሃላፊነት ነው፣ እንዲሁም እርስዎ የእርስዎን በኩልጉ ዳይዎን  ለማቅረብ እድል ይሰጥዎታል። እርስዎ ተጠያቂነትን ቢያምኑም እንኳ፣ ኣሁንም ቢሆን ተገቢ የሆነ እርጅና እና እልቂትን ግምት ውስጥ በማስገባት የተጠየቀው መጠን ተገቢ እንዳልሆነ መቃወም ይችላሉ። የጥገና ማስታወቂያ የደረስዎት እንደሆነ፣ ያግኙን .

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

እኛን ያግኙን

ለተከራዮች ምክር (advice for tenants)
እኛን ያግኙን (contact us)

የቪክቶርያ ተከረዮች | የተከራዮች የድጋፍ መስመር 1800 068 860| tuv.org.au
የቪክቶርያ ተከራዮች የቪክተርያ መንግስት ድጋፍ ዕውቅና ይሰጡታል፡፡

የታተመ: ግንቦት 2017

Repairs | Amharic | May 2017


Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept