ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የኪራይ ውዝፎች

በአብዛኛዎቹ የኪራይ ስምምነቶች መሠረት የቤት ኪራይ የሚከፈለው በቅድሚያ ነው፡፡ በጣም የተለመደው አሰራር የመጪውን ወር የሚሸፍን ሆኖ በእያንዳንዱ ወር በተመሣሣይ ቀን በቅድሚያ መክፈል ነው፡፡

መክፈል ባለብዎት ቀን ሳይከፍሉ ቢቀሩ ክፍያውን ሳይፈጽሙ በንብረቱ ላይ ለሚቆዩበት ለእያንዳንዱ ቀን ክፍያ ያልተደረገበት አንድ ቀን ወይም ’በኪራይ ውዝፍ ’ ውስጥ ይሆናሉ፡፡

 ማድረግ የሌለብዎት የኪራይ ውዝፍ ውስጥ መግባት 

ገቢዎ አነስተኛ ከሆነ ወይም በጡረታ ላይ ከሆኑ ወይም ከመንግሥት ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኙ ከሆነ ኪራይዎን ለመክፈል ቀላል የሚሆንልዎት ገቢዎን እንዳገኙ በየሁለት ሣምንቱ በሚከፈል ዘዴ ቢከፍሉ ነው፡፡ ሆኖም ብዙዎቹ የቤት ኪራይ ስምምነቶች ኪራዩ በየወሩ እንዲፈጸም የሚደነግጉ ናቸው፡፡ እርስዎ ኪራዩን መክፈል የሚፈልጉት በየወሩ ሳይሆን በየሁለት ሣምንቱ ከሆነ የአከራዩን ወይም የወኪሉን ፈቃድ ለማግኘት መሞከር ይኖርብዎታል፡፡  

እርስዎ በጡረታ ላይ ከሆኑ ወይም ከመንግሥት ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኙ ከሆነ ከዚሁ ላይ የኪራዩ መጠን ተቀናሽ እንዲደረግና በCentrelink የሚተዳደረውን Centrepay በመጠቀም በቀጥታ ለመክፈል ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስለ Centrepay ማግኘት ከፈለጉ Centrelink ንያግኙ፡፡

ኪራይዎን በCentrepay በኩል የሚከፍሉ ከሆነ ከቤቱ በሚለቁበት ወቅት ክፍያው እንዲቋረጥ ማድረግ የእርስዎ ሃላፊነት ነው፡፡ እንዲሁም የሚቀጥለው የክፍያ ጊዜ ከመድረሱ አስቀድሞ ከቤቱ የሚለቁ ከሆነ የመጨረሻውን የኪራይ ክፍያ መጠን ማስተካከል እንዳለብዎ መዘንጋት አይኖርብዎትም፡፡  

የቤት ኪራይ ደረሰኞች ኪራዩ የተከፈለበትን ጊዜ ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ኪራዩን የከፈሉት እስከመቼ ጊዜ ድረስ መሆኑን ሊያሳይዎት ይገባል፡፡ ኪራይ በሚከፍሉበት ጊዜ ሁሉ ደረሰኝ እንዲሰጥዎት መጠየቅ ይኖርብዎታል፡፡ ኪራይዎ የተከፈለው እስከመቼ ጊዜ ድረስ እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆኑ አከራዩን ወይም ወኪሉን በማግኘት የኪራይ ክፍያ መዝገብ (ብዙውን ጊዜ ሬንት ሌጀር ተብሎ ይጠራል) ቅጂ እንዲሰጥዎት ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

 ማድረግ ያለብዎ የኪራይ ውዝፍ ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ 

የ14 ቀን የቤት ኪራይ ውዝፍ ካለብዎት አከራዩ   ቤቱን እንዲለቁ የ14 ቀን ማስታወቂያ ሊሰጥዎት ይችላል፡፡  . የ 14 ቀናት ውዝፍ እዳ ተከታታይ ቀናት ሊሆን፣ ወይም በተለያዩ ሣምንታት ወይም ወራት ውስጥ ኪራይዎን እያሳላፉ ከፍለው ከሆነ ደረጃ በደረጃ በጊዜ ውስጥ የተጠራቀመም ሊሆን ይችላል፡፡  ውዝፍ ዕዳው በማናቸውም መንገድ የተጠራቀመ ቢሆን አከራዩ  ቤቱን እንዲለቁለት ማስታወቂያ ለመስጠት   እርስዎ ኪራዩን ሳይከፍሉ 14 ቀናት ያለፈዎት መሆን ይኖርበታል፡፡

  ቤቱን እንዲለቁ ማስታወቂያ ሊሰጥዎት የሚችለው  የክፍያ ጊዜው ላለፈበት ኪራይ ብቻ ነው፡፡ ኪራዩን እስቀድመው ባለመክፈልዎ ምክንያት ቤቱን እንዲለቁ ማስታወቂያ ሊሰጥዎት አይችልም፡፡    ቤቱን እንዲለቁ ማስታወቂያ በተሰጥዎት ወቅት  የ14 ቀናት የቤት ኪራይ ውዝፍ ከሌለብዎት ማስታወቂያው ሕጋዊ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

የኪራይ ውስጥ ከገቡ እና ክፍያውን መፈጸም ካልቻሉ ሳይዘገዩ አከራዩን ወይም ወኪሉን ማግኘትና መቼ ለመክፈል እንደሚችሉ ይንገሯቸው፡፡

ውዝፍ ኪራዩን በአንድ ጊዜ መክፈል ባይችሉ በጊዜ ውስጥ ቀስ እያሉ መክፈል እንዲችሉ ሃሳብ ማቅረብ ይችላሉ (ለምሣሌ 20$ ተጨማሪ በየሣምንቱ)፡፡ ከሚችለው በላይ ለመክፈል አይክፈሉ.   ከአቅምዎ በላይ ለመክፈል ሃሳብ አያቅርቡ፡፡     ሃሳብዎን በጽሁፍ ያቅርቡ እና ቅጂውን ይያዙ – አከራዩ ወይም ወኪሉ ሃሳብዎን ባይቀበሉትም እንኳን ችግሩን ለመፍታት ስለመሞከርዎ ደብዳቤውን እንደማስረጃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

እርስዎን አከራዩ ወይም ወኪሉ በግላቸው ከቤቱ ለማስወጣት ከሞከሩ ድርጊቱ ሕገ ወጥ ነው፡፡ እርስዎን ከቤቱ አስገድደው ለማስወጣት የሚችሉት ፖሊሶች ብቻ ሲሆኑ እነርሱም ቢሆኑ እንኳን ከቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል (Victorian Civil and Administrative Tribunal) አግባብነት ያለው  የመያዣ ትዕዛዝ   እና የመያዣ ወረቀት  መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

የክፍያ ዕቅድን አስመልክቶ እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ National Debt Helpline   1800 007 007   ላይ በመደወል የፋይናንስ አማካሪ ለማነጋገር ይችላሉ፡፡

በኪራይ ውዝፍ ዕዳ ውስጥ ያሉ ከሆነ በገንዘብ ጉዳይ ዕርዳታ ሊያደርጉልዎ የሚችሉ ስለቤት ጉዳይ አገልግሎት የሚሰጡ አሉ፡፡ እነዚህን አገልግሎቶች በዚህ 1800 825 955ቁጥር ላይ በመደወል ሊያገኙዋቸው ይችላሉ (24 ሰዓት ነጻ የጥሪ መስመር)፡፡

 በኪራይ ውዝፍ ዕዳ ምክንያት ከቤት አስገድዶ የማስወጣት ሥነ ሥርዓት  

እርስዎ ከቤቱ ተገደው እንዲወጡ ሊደረግ የሚችለው  ሕጋዊ የሆነ ቤቱን እንዲለቁ የሚጠይቅ ማስታወቂያ ሲደርስዎት ,ጉዳይዎ በቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ዘንድ ታይቶ የነበረ ከሆነ፣ ትራይቡናሉ ለአከራዩ ቤቱን መልሶ እንዲይዝ   የመያዣ ትዕዛዝ ሰጥቶ ከሆነ፣ አከራዩ  የመያዣ ወረቀት አግኝቶ ከሆነና  ፖሊስ መያዣውን ለማስፈጸም ቤቱ ድረስ ሲመጣ ነው፡፡

አከራዩ ወይም ወኪሉ  እርስዎ ያቀረቡትን ሃሳብ ካልተቀበሉት ወይም እርስዎ ምንም ዓይነት ክፍያ ማድረግ ካልቻሉ አከራዩ እርስዎን  አስገድዶ ከቤቱ ለማስወጣት  ተገቢውን ሕጋዊ ሥርዓት መከተል ይኖርበታል፡፡

 የፍርድ ቤት መጥሪያ ከቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል ከደረሰዎትና ከቤቱ ተገደው ለመውጣት ካልፈለጉ  በመጥሪያው መሠረት ከትራይቡናሉ ፊት መቅረብ ይገባዎታል፡፡

አከራዩ ወይም ወኪሉ ያለብዎትን ውዝፍ ኪራይ ከፍለዋል በማለት (ወይም ሌላ ማናቸውም ምክንያት በመስጠት) ወደ ችሎቱ ዘንድ መሄድ አያስፈልግዎትም ብለው ቢነግሩዎ በትክክልም ማመልከቻቸው የተነሳ መሆኑን ለማረጋገጥ ለትራይቡናሉ በ  1300 01 8228 (1300 01  ላይ ይደውሉ፡፡ ማመልከቻው ያልተነሳ መሆኑን ካወቁ ወደ ፍርድ ቤቱ መሄድ ይኖርብዎታል፡፡

በችሎቱ ላይ የትራይቡናሉ አባል   የመያዣ ትዕዛዝ  ሊሰጥ ወይም አከራዩ ያቀረበውን  መልሶ የመያዣ አቤቱታ  ውድቅ ሊያደርገው ወይም በሌላ ጊዜ እንዲታይ ትዕዛዝ ለመስጠት ይችላል፡፡ አባሉ አቤቱታው በሌላ ጊዜ እንዲታይ ትዕዛዝ ለመስጠት የሚችለው፡

  •   እዳውን ለመክፈል ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑን ሲያሳዩ፣ ወይም 
  •  ለትራይቡናሉ ዕዳውን እንዴት አድርገው መክፈል እንደሚችሉ እና አከራዩ ምንም ዓይነት የገንዘብ ኪሣራ እንደማይደርስበት ሲያሳዩ ነው፡፡ 

ያለባቸውን የቤት ኪራይ ዕዳ መልሶ ለመክፈል ምክንያታዊ ዕቅድ ካላቸው አብዛኛዎቹ ተከራዮች የቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል  የመያዣ ትዕዛዝ  እንዳይሰጥ የሚያቀርቡት ጥያቄ ውጤታማ ነው፡፡

በተቻለ መጠን ያሉዎትን ማስረጃዎች ሁሉ ወደ ቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል በመውሰድ እንዴት ወደዚህ ዕዳ ለመግባት እንደቻሉና ዕዳውንም እንዴት መክፈል እንደሚችሉ ማሳየት ይኖርብዎታል፡፡ ማስረጃዎቹ ማካተት የሚኖርባቸው የፋይንናሺያል ካውንስለር ገቢዎንና ወጭዎን ያሰላበትን ሰነድ ወይም ሌሎች  ያላቸውን ሰነዶች (እንደ የደመወዝ መቀበያ ወረቀት፣ የCentrelink የክፍያ መግለጫ ወይም የቤት ኪራይ ክፍያ ማስረጃ) ነው፡፡ እንዲሁም የእርስዎን ጉዳይ ሊደግፍልዎ የሚችል ሰው ካለ ከችሎቱ ዘንድ ቀርቦ የምስክርነት ማስረጃ እንዲሰጥልዎ ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

የቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል ጉዳዩን ለሌላ ጊዜ ካስተላለፈው አብዛኛውን ጊዜ ከ3-6 ወራት ሆኖ ጊዜ ወስኖ ጉዳዩን በይደር ያቆየዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ‘ጉዳዩን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ’  በማስገደድ ከቤቱ የማስወጣቱ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ሳይፈጸም እንዲቆይ በማድረግ ለእርስዎ ሁለተኛ ዕድል መስጠት ማለት ነው፡፡ እርስዎ ውዝፍ ዕዳውን በቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል ትዕዛዝ መሠረት በተወሰነልዎት የጊዜ ገደብ ውስጥ ውዝፍ ዕዳውን መክፈል ከቻሉ የቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል አቤቱታውን በማንሳት መዝገቡን ይዘጋዋል፡፡

ይሁንና እርስዎ በቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል ትዕዛዝ መሠረት መፈጸም ካልቻሉ (ለምሣሌ ክፍያውን ለመፈጸም ከዘገዩ) አከራዩ ማመልከቻውን ‘ሊያድሰውና ’ የፍርድ ቤት  የመጥሪያ ትዕዛዝ ሊደርስዎት ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ ወደተጠሩበት ሥፍራ መሄድና. በትዕዛዙ መሠረት ያልፈጸሙበትን በቂ ምክንያት ማቅረብ የሚኖርብዎት ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ተገደው ሊወጡ የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል፡፡

የቪክቶርያ ሲቪል ኤንድ አድሚኒስትሬቲቭ ትራይቡናል ጉዳዩን ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ካደረገውና  የመያዣ ትዕዛዝ  , ከሰጠ የማስወጫ ማዘዣ ሳይሰጥ እንዲዘገይ የትራይቡሉን አባል ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡   ይህም ፖሊስ የማስወጫ ትዕዛዙን ለማስፈጸም እርስዎን አስገድዶ የሚያስወጣበትን ጊዜ ያዘገየዋል፡፡  ትራይቡናሉ የማስወጫ ትዕዛዙን እስከ 30 ቀን ድረስ ሊያዘገየው ይችላል፡፡  የማስወጫ ትዕዛዙ እንዲዘገይ በሚመረምሩበት ወቅት የትራይቡናሉ አባል እርስዎ ያለበዎትን ችግር እና ትዕዛዙ ቢዘገይ አከራዩ ሊደርስበት የሚችለውን ችግር ይመዝናሉ፡፡  ይህ ጉዳይ በሚታይበት ወቅት ችግርዎን ሊያሳዩ የሚችሉ መረጃዎችን (ሌላ ቤት ለመከራየት ጥያቄ ስለማቅረብዎ ማስረጃ፣ የሕክምና ሰርቲፊኬት፣ የድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ደብዳቤ) ይዘው መቅረብ ይኖርብዎታል፡፡

ማስታወሻ፡ አከራዩ በኪራይ ውዝፍ ምክንያት እርስዎን ከቤቱ አስገድዶ ለማስወጣት እርምጃ እየወሰደ ከሆነ የእኛን eviction ገጽ እንዲያነቡ እንመክራለን፤ ምክንያቱም አከራዩ በአማራጭነት ከትራይቡናሉ  የመያዣ ትዕዛዝ   ለማግኘት ሊያመለክት ስለሚችል ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ እኛን፣ የአካባቢዎን የTAAP አገልግሎትን፣    የቴናንሲ ፕላስ ፕሮቫይደርን   ወይም   የኮሚዩኒቲ ሌጋል ሲንተርን ያግኙ፡፡

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

[disclaimer-rta-amharic]


ተዛማጅ ገፆች

ከቤት ማስወጣት
ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ
መቸ ነው ቤቱን መልቀቅ የሚፈልጉ
ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች
የመያዣ ገንዘብ ክፍያዎችን እና የክፍያዎቹ ኣመላለስ
ስለ ተከራይ የተቀመጡ መረጃዎች ወይም “በጥፋተኝነት የተመዘገበ/blacklists”

ሕጉ

Residential Tenancies Act 1997 (AustLII website)
Section 246 – Notice to Vacate for rent arrears
Section 331- application for possession may be dismissed or adjourned
Section 352- postponement of the warrant of possession

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept