ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የመንግሥት መኖሪያ ቤት ጥገና

በተከራዩት ቤት ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥገና ያስፈልጋል።

የተከራይና አከራይ ህግ እንደሚለው በቪክቶሪያ ውስጥ ሁሉም ባለንብረቶች የ Director of Housing, ጭምር ያከራዩትን ንብረት ላይ ጥሩ ጥገና ማካሄድ ይኖርባቸዋል።

አንዳንዴ በቤትዎ ላይ ጥገና እንዲደረግ ከፈለጉ በተቻለ ፍጥነት ለጥገና የስልክ ማእከል በስልክ  13 11 72
ማነጋገር።

ለጥገና የስልክ ማእከል በቀን ለ24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት መደወል ይችላሉ (ከሥራ ሰዓት ውጭ የሚደወለው አስቸኳይ ለሆነ ጥገና ብቻ ነው)።

እርስዎ የሚናገሩትን ቋንቋ መናገርና በስልክ ጥሪ ማእከል በኩል አስተርጓሚ ይቀናጅልዎታል።

ለጥገና የስልክ ማእከል ሲደውሉ የሚከተለውን መናገር ጠቃሚ ነው።

 • ስምዎንና የስልክ ቁጥር
 • የርስዎን አድራሻ
 • ችግሩ ምን እንደሆነ (የማይሠራው ወይም ጥገና የሚያስፈልገው ምንድ ነው)

 

ችግሩን በዝርዝር መግለጽ። ችግሩ ምን እንደሆነ በጣም ትክክለኛ መሆን። ለምሳሌ፡ የሚያንጠበጥብ ቧንቧ ካለዎት ለአስተናጋጁ የሙቅ ውሀ ወይም የቀዝቃዛ ውሀ መዝጊያና መክፈቻ መሆኑን መናገር። ሌላ ምሳሌ፡ የተሰበረ ምድጃ ካለዎት፤ የጋዝ ወይም የኤሌትሪክ ስለመሆኑና የትኛው መጣጃ እንደተሰበረ ወዘተ. ለአስተናጋጁ ማሳወቅ።

ሁልጊዜ የScheduled Contract Number (SC Order) ቁጥሩን ይጠይቁ፡፡ ይህ ቁጥር ስለ መደወልዎ ማስረጃ ነው።

ምን ዓይነት ጥገናዎች?

ጥገናዎች እንደ አስቸኳይ ሊመደቡ ይችላሉ ወይም አስቸኳይ ባልሆነ መልኩ ይመደባል።

አስቸኳይ ጥገናዎች

እነዚህ ጥገናዎች በ24 ሰዓት ውስጥ መጠናቀቅ አለባቸው።

በነዚህ ላይ የሚካተት:

 • የውሀ አገልግሎት በድንገት ሲፈነዳ
 • የሽንት ቤት መዘጋት ወይም መሰበር
 • ከፍተኛ የጣራ ማፍሰስ
 • ጋዝ ሲያንጠባጥብ
 • አደገኛ የኤሌትሪክ ብልሽት
 • ጎርፍ ወይም በጎርፍ ከባድ ጉዳት ሲደርስ
 • በከባድ ዝናብ ወይም የእሳት አደጋ
 • በ Director of Housing የቀረበ የውሀ፣ ሙቅ ውሀ፣ የምግብ ማብሰያ፣ ማሞቂያ ወይም የልብስ ማጠቢያ መሳሪያ አገልግሎት ሲበላሽ ወይም ሲቆም
 • በመወጣጫ ደረጃ ላይ ወይም ኤሌቨተር ላይ ከባድ ችግር
 • በንብረት ላይ ድህንነቱ ያልተጠበቀ ብልሽት ወይም ጉዳት ሲኖር (የጢስ ማስጠንቀቂያ አላርም ብልሽትን ወይም ጉዳትን ያካትታል)

 

የቅድሚያ ጥገናዎች

እነዚህ ጥገናዎች በ7 ቀናት ውስጥ ጥገናው መጠናቀቅ አለበት።

በቅድሚያ ጥገና የሚመደቡት ከባድ የሆኑ ወዲያውኑ በጤና እና ደህንነት ላይ ችግር የማይፈጥሩ፤ ለምሳሌ የሚያንጠባጥብ የቧንቧ መክፈቻና መዝጊያ።

የቧንቧ መክፈቻና መዝጊያ ብዙ ውሀ የሚያፈስ ከሆነ እንደ አስቸኳይ ጥገና መጽደቅ ይችላል። ለጥገና የስልክ ማእከል በሚያነጋግሩበት ጊዜ ትክክለኛ ችግሩን መግለጽና ምን ያህል ውሀ እንደሚፈስ መናገር።

ምን ያህል ውሀ እንደሚፈስ ለመለካት በስር ላይ የብረድስት ማድረግና በምን ያህል ጊዜ እንደሚሞላ ለጥገና የስልክ ማእከል መናገር (ለምሳሌ፡ በየአንድ ሰዓት).

አስቸኳይ ያልሆነ ጥገና

እነዚህ ጥገናዎች በ14 ቀናት ውስጥ ጥገናው መጠናቀቅ አለበት።

በአስቸኳይ ወይም በቅድሚያ ጥገና ደረጃ ላይ የማይመደቡ ጥገናዎች አሉ። ለምሳሌ፡ በኩሽና ቁምሳጥን፣ በግድግዳ ላይ ቀዳዳ፣ የተበላሸ መጋረጃ ወይም የልብስ ማስጫ የደረሰ ጉዳትን ያካትታል።

ጥገናውን ስለማካሄድ

አንዴ ለጥገና የስልክ ማእከል ካነጋገሩ በኋላ ኮንትራክተሮች ወደቤትዎ መጥተው ችግሩን ለመጠገን ማእከሉ ያቀናጃል።

ጥገናው አስቸኳይ ከሆነ ኮንትራክተሩ በ24 ሰዓት ውስጥ መምጣት አለበት።

ጥገናው የቅድሚያ ወይም አስቸኳይ ካልሆነ ወደ ቤትዎ ለመምጣት ተስማሚ ጊዜ ለማቀናጀት ኮንትራክተሩ ይደውላል።

ኮንትራክተሩ ወደ ቤት እንዲገባ ከመፍቀድዎ በፊት መታወቂያ ማየት አለብዎ።

ኮንትራክተሩ ሲመጣ ቤት ካልሆኑ የስልክ መደወያ ካርድ ትቶ ይሄዳል። ይህም የደወሉበት ቀንና ሰዓት፣ በተጨማሪም የነሱን ስምና ስልክ ቁጥር ያካትታል።

ለኮንትራክተሩ መደወል አይኖርብዎም። ለስልክ ጥሪ ማእከል በቁጥር  13 11 72
መደወልና በካርዱ ላይ ያለውን ስም መነጋገር። ከዚያም ለኮንትራክተሩ ደውለው ተስማሚ ጊዜ ያቀናጃሉ።

ጥገናው ካልተካሄደስ ምን ይደረጋል?

እንደገና ለስልክ ጥሪ ማእከል በመደወል ሥራው እንዳልተካሄደ መናገር። እንዲሁም ምክር ለማግኘት የTenants Union/Tenants Victoria በስልክ 1800 068 860 ያነጋግሩ።

ጥገናው አስቸኳይ ከሆነ ጥገና ለማካሄድ ትእዛዝ እንዲሰጥ ለ Victorian Civil and Administrative Tribunal (VCAT) ማመልከት ይችላሉ።

ጥገናው አስቸኳይ ካልሆነ በንብረቱ ላይ ፍተሻ እንዲካሄድ የጥያቄ ደብዳቤ ለ Consumer Affairs Victoria (CAV) መጻፍ አለብዎ። የደንበኛ ጉዳይ ፈታሽ ወደ ቤትዎ መጥቶ ካየ በኋላ ጥገና ማድረግ ካስፈለገ ፈታሹ ለ Director of Housing በማነጋገር በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ጥገናው እንዲካሄድ ያቀናጃል።

አሁንም ጥገናው ካልተካሄደ፤ በደንበኛ ጉዳይ ፈታሽ በኩል ለጥገና የቀረበውን ሪፖርት ቅጂ ይልኩልዎታል። ከዚያም ጥገናው እንዲካሄድ ትእዛዝ በVictorian Civil and Administrative Tribunal (VCAT) እንዲሰጥ ማመልከት ይችላሉ። በ VCAT ፍርድ ችሎት እንዲታይ ማመልከቻ ሲያዘጋጁ የ Tenants Union/Tenants Victoria ሊረዳዎ ይችላል።

ቅሬታ የማቅረብ መብትዎ የተጠበቀ ነው! ከዚህ በላይ ያሉትን እርምጃዎች መውሰድ ወይም በተባለው ጊዜ ውስት ጥገናው ካልተካሄደ፤ የሥራው ጥራት መጥፎ ከሆነ ወይም ኮንትራክተሩ ባለጌ ወይም አናዳጅ ከሆነ ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።

አንዴ ሥራው እንደተጠናቀቀ በሥራ ማዘዣው ላይ እንዲፈርሙ ይጠየቃሉ። (በባዶ የሥራ ማዘዣ ወረቀት ላይ አለመፈረም)።

ካለፈው ገጽ የቀጠለ

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Public housing repairs | Amharic | June 2012

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept