ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የመንግሥት መኖሪያ ቤት ኪራይ

ይህ ገጽ

የቤት ኪራይ ምንድን ነው?
የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ እንዴት ይሰላል?
በየስንት ጊዜ የቤት ኪራየ ይጨምራል?
Director of Housing’s ባደረገው የቤት ኪራይ ግምገማ ላይ ካልተስማማሁ ምን ይደረጋል?
ከቤት ኪራይ የሚቀነስ ገንዘብ

የቤት ኪራይ ምንድን ነው?

በቪክቶሪያ የተከራይና አከራይ ህግ መሰረት የቤት ኪራይ ማለት ‘በተከራዩበት ንብረት ገብቶ ለመኖር መገልገያና አገልግሎቶችን ለመጠቀም ተከራዮች ለባለንብረቱ የሚከፍሉት የተወሰነ የገንዘብ መጠን ነው’።

በመንግሥት መኖሪያ ቤት ኪራይ ሁለት የተለያየ ትርጉም አለው:

በገበያ ተመን ቤት ኪራይ ይህ የቤት ኪራይ ንብረቱ በግል የሚከራይ ገበያ በኩል ቢቀርብ ኖሮ መክፈል የነበረብዎ መጠን ነው። በገበያ ተመን ለእያንዳንዱ የቤት ኪራይ በቪክቶሪያ ተማኝ-አጠቃላይ ይወሰናል።

ስለዚህ ብዙዎቹ የመንግሥት ቤት ተከራዮች ከገበያ ኪራይ የዋጋ ቅናሽ ያገኛሉ። ለቤት ኪራይ በበለጠ አቅም እንዲኖር ለማድረ ከገበያ ተመን ኪራይ ላይ የሚቀነሰው ገንዘብ ዋጋ ቅናሽ ይባላል።

በቅናሽ ዋጋ ኪራይ በገበያ ተመን የቤት ኪራይ ላይ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎ የሚከፍሉት የቤት ኪራይ ነው።

የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ እንዴት ይሰላል?

የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ ከጠቅላላ የቤተሰብ ገቢ መጠን እንደ ክፍል ተቆጥሮ ይሰላል ይህም የቤተሰብ አባላት በሙሉ ያለው ጠቅላላ ገቢ ይታያል።

በቅናሽ ዋጋ የቤት ኪራይ ለመወሰን ሶስት የገቢ ዓይነቶች ግምት ውስጥ ይገባል። እነዚህም:

  • መሰረታዊ ገቢ– እንደ ሳምንታዊ ክፍያ፣ ደመወዝ፣ ጡሮታ፣ ድጎማ ክፍያ፣ አበል፣ ሱፐራኑየሽን፣ ተጠራቅሞ የሚሰጥ ክፍያ፣ ከሚያስቀምጡት ገንዘብ ወለድ ወይም ለሥራ ካወጡት ገንዘብ ገቢ።
  • በዋጋ ቅናሽ መልኩ-የሚታይ ገቢ – እንደ በ Centrelink የሚከፈል የቤተሰብ ግብር ክፍያ//Family tax benefits እና በህጻን ድጋፍ ተወካይ ወይም በማያሳድግ ወላጅ የሚሰጥ ለህጻን መዶጎሚያ ክፍያ
  • ከግዴታ ነጻ የሆነ ገቢ– እንደ በጡሮታ ለተገለሉ ክፍያዎች።

 

በመሰረቱ የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ የሚሰላው እንደ ቤተሰቡ መሰረታዊ የገቢ መጠን ከመቶ 25 እጅ እና በተጨማሪም ከማንኛውም በቅናሽ ዋጋ – ከሚታይ ገቢ መጠን ከመቶ15 እጅ ይሆናል።

በየስንት ጊዜ የቤት ኪራየ ይጨምራል?

በመንግሥት መኖሪያ ቤት ላይ የገበያ ተመን ኪራይ በየ 12 ወራት ይገመገማል።

የገበያ ተመን ኪራይ ከጨመረ ታዲያ የቤት ኪራይ ስለመጨመሩ የሚገልጽ ማሳሳቢያ ይደርስዎታል። የተደረገው ጭማሪ ከገበያ ተመን ኪራይ በላይ ነው ብለው ካመኑት፣ እንደገና የቤት ኪራይ ግምገማ እንዲካሄድ ለDirector of Consumer Affairs ማመልከት ይችላሉ። በአብዛኛው የመንግሥት ተከራዮች ላይ እንደገና የቤት ኪራይ ግምገማ እንዲካሄድ አይፈልጉም ምክንያቱም ካላቸው የዋጋ ቅናሽ ኪራይ ጋር ምንም ለውጥ ስለማያመጣ ነው።

የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ በወቅቱ ባለው የቤተሰብ ገቢ መጠን ተመርኩዞ በዓመት ሁለት ጊዜ ሲስተካከል ይህም ለ26 ሳምንታት አይቀየርም (ምንም እንኳን ግምገማ ሲደረግ ባለው ጊዜ ውስጥ የቤተሰብ ገቢ መጠን ቢጨምርም)።

ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ መካከል የቤተሰብ ገቢ መጠን ከቀነሰ፤ ተከራዩ ያላቸው ዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ እንዲቀንስ ማመልከት ይችላሉ።

በየጊዜው የርስዎ ዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ ሲገመገም፣ የቤተሰብዎን ገቢ መጠን እንዲናገሩ የሚጠይቅ ደብዳቤ ከDirector of Housing* ይደርስዎታል።

ይህንን ደብዳቤ በጥንቃቄ ማየቱ አስፈላጊ ነው። የተገለጸው መረጃ ዝርዝር ሁሉ ወቅታዊና ትክክለኛ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለብዎ። የገቢ መጠኑ መግለጫ ትክክል ካልሆነ የአካባቢዎን የመኖሪያ ቤት ቢሮ* በማነጋገር በተቻለ ፍጥነት እርምት መደረግ አለበት።

በየጊዜው በተደረገ የገቢ መጠን ግምገማ ላይ መረጃ ለማቅረብ በአካባቢዎ የመኖሪያ ቤት ቢሮ መሄድ ይኖርብዎታል።

የርስዎን ገቢ መጠን ዝርዝር ሁኔታ በተመለከተ ከDirector of Housing የሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ ነው። ስለርስዎ የገቢ መጠን መረጃ የDirector of Housing ካልደረሰው፤ የነበርዎ ዋጋ ቅናሽ የቤት ኪራይ ውድቅ ይሆንና በቤት ኪራይ እዳ ይዘፈቃሉ በመጨረሻም ቤቱን ይለቃሉ።

የገቢ ምንጭዎ ከ Centrelink ከሆነ ለገቢ ማረጋገጫ አገልግሎት መፈረም ይችላሉ። ይህ ማለት የርስዎ ገቢ መጠን መረጃ በቀጥታ ከ Centrelink ወደ መኖሪያ ቤት ዳይሬክተር ይሄዳል። የርስዎ ጡሮታ ወይም አበል ክፍያ በሚቀየርበት ጊዜ እና የዋጋ ቅናሽ ኪራይ ግምገማ ሲካሄድ በወቅቱ የነበረ ገቢ መጠን ትክክለኛ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ መረጃውን ለመኖሪያ ቤት ዳይሬክተር ይተላለፋል።

እንዴት የገቢ መጠን እንደሚታይና የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ ሲሰላ ተጽእኖ የሚፈጥሩ የተለያዩ ፖሊሶዎች አሉ። ለርስዎ የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ በ Director of Housing በኩል ትክክለኛ ስሌት አልተደረገም ብለው ካመኑ፤ ምክር ለማግኘት የ Tenants Union/Tenants Victoria ማነጋገር አለብዎ። ስልክ 1800 068 860

Director of Housing’s ባደረገው የቤት ኪራይ ግምገማ ላይ ካልተስማማሁ ምን ይደረጋል?

ለርስዎ የዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ በ Director of Housing በኩል ትክክለኛ ስሌት አልተደረገም ብለው ካመኑ፤ በመጀመሪያ ጉዳዩን ለመፍታት ከአካባቢዎ የመኖሪያ ቤት ቢሮ ጋር መነጋገርና የተደረገውን ስምምነት በጽሁፍ አድርገው እንዲሰጡዎት መጠየቅ አለብዎ።

በአካባቢዎ መኖሪያ ቤት ቢሮ መፍትሄ ካላገኙ ከዚህ በመቀጠል መደበኛ ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።

ቅሬታ ለማቅረብ አያስከፍልም እንዲሁም በአካባቢዎ የመኖሪያ ቤት ቢሮ በአካል ሂዶ ወይም በስልክ ማቅረብ ይችላሉ። የርስዎን ቅሬታ ሲያስገቡ ጥያቄ ካለዎ ወይንም እርዳታ ከፈለጉ ለ Housing Complaints Management Unit

እንዲሁም Director of Housing በውስጥ አቤቱታ ሰሚ አሠራር አለው። በDirector of Housing ያለን ፖሊሲና አሠራር ሂደት በተገቢው ተግባራዊ አልሆነም ብለው ካመኑ፤ ወይም የርስዎን ዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ ሲሰላ ስህተት ተደርጓል ብለው ካመኑ፤ ለውስጥ አቤቱታ ሰሚ ማመልከት ይችላሉ።

ስለ የውስጥ አቤቱታ ሰሚ አሠራር የበለጠ መረጃ ለማግኘት የእኛን ስለ መንግሥት መኖሪያ ቤት ውሳኔ አቤቱታ የሚለውን እውነታ ጽሁፍ ይመልከቱ።

ከቤት ኪራይ የሚቀነስ ገንዘብ

ከዋጋ ቅናሽ ቤት ኪራይ በተጨማሪ በሚከተሉት አንዳንድ ሁኔታዎች መሰረት የቤት ኪራይ ድጎማ ለማግኘት ይፈቀድልዎ ይሆናል:

  • ንብረቱ በእሳት ወይም በጎርፍ የተጎዳ ከሆነ
  • በንብረቱ ላይ እያሉ ቤቱ የሚታደስ ከሆነ
  • እርስዎ የተከራይ አገናኝ ሃላፊ/ Resident Liaison Officer ወይም የተከራይ ተንከባካቢ/ Resident Caretaker ከሆኑ
  • እድሜዎ ወደ 100 ዓመት እየሞላ ከሆነ

 

የቤት ኪራይ ድጎማ የሚፈቀድልዎ ከመሰለዎት ለአካባቢዎ የመኖሪያ ቤት ቢሮ ያነጋግሩ።

እንዲሁም ምክር ለማግኘት Tenants Union/Tenants Victoria ማነጋገር ይችላሉ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ለTenants Union/Tenants Victoria Advice Line በስልክ 1800 068 860መደወል።

*የመንግሥት አካል የሆነው የህዝብ መኖሪያ ቤቶችን የሚያስተዳድር መስሪያ ቤት ቀደም ሲል ብዛት ያለው ስም ይጠቀም ነበር ከነዚህ መካከል the Housing Commission, Department of Housing and Office of Housing ናቸው። በአሁን ጊዜ Housing and Community Building Division of the Department of Human Services ተብሎ ይጠራል። ይህንን አገልግሎት በሚገባ ለመግለጽ ሲባል የ name Director of Housing የሚለውን ስም Tenants Union/Tenants Victoria እንደ አማራጭ ይጠቀማል።
እባክዎ ያስተውሉ፤ በአሁን ጊዜ የአካባቢዎ መኖሪያ ቤት ቢሮ በ Department of Human Services ውስጥ ይገኛል።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Public housing rents | Amharic | June 2012

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept