ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ለብቻ የመሆን ነጻነት እና ወደ ቤት ውስጥ የመግባት ሁኔታ

The Residential Tenancies Act 1997 states that you have a right to ‘quiet enjoyment’ of your home. አከራዮች እና የሪል እስቴት ተወካዮች የመግባት አንዳንድ መብቶች አላቸው ፣ ግን የተወሰኑ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። እነዚህን መስፈርቶች የማያሟሉ ከሆነ ወደ ቤትዎ እንዲገቡ ማድረግ የለብዎትም ፡፡

 የመግቢያ መብቶች

ተገቢው ማስታወቂያ እስከተሰጠ ድረስ አከራዩ ወይም ወኪሉ ወደ ቤትዎ ውስጥ ለመግባት ይችላሉ፤ እንዲሁም ወደ ቤቱ ለመግባት የፈለጉበትን ምክንያት ለማሟላት የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ሌላም ሰው ይዘው ለመግባት ይችላሉ፤ ይህም የሚሆነው፡

  • a ቤቱን እንዲለቁ የተሰጠ ማስታወቂያ ወይም ቤቱን እንዲለቁ ስለመፈለጋቸው የተሰጠ ማስታወቂያ ካለ እና የዚህም ማስታወቂያ ጊዜ ከ14 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የሚያልቅ ከሆነ እና ቤቱን ለመከራየት ለሚፈልግ ለሌላ ሰው ማሳየት ከፈለጉ 
  • ቤቱ የሚሸጥ ከሆነ ወይም ቤቱ ለብድር መያዣነት ሊሰጥ ከሆነ እና ንብረቱን ቤቱን ለመግዛት ለሚፈልግ ወገን ወይም ለአበዳሪ ለማሳየት ከፈለጉ (ማስታወሻ፡ ይህ ወደ ቤት ውስጥ የመግባት መብት “ለምርመራ እንዲከፍቱ” ወይም ቤቱን ለመሸጥ በመፈለግ ለማስታወቂያ ሲባል ቤቱን ፎቶግራፍ ለማንሳት ጉዳይ ሥራ ላይ ሊውል አይችልም –    ለተጨማሪ መረጃአከራይ ቤቱን ለመሸጥ ይፈልጋልየሚለውን ይመልከቱ) 
  • በኪራይ ስምምነቱ (የኪራይ)፣ በResidential Tenancies Act 1997,ወይም በሌላ ሕግ ውስጥ የተጠቀሰ ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ቤቱ መግባት ካስፈለጋቸው
  • ንብረቱን ለማስገመት ሲፈልጉ፣
  • በስምምነታችሁ (የኪራዩ ውል)፣ በ Residential Tenancies Act 1997 መሠረት ያለብዎትን ግዴታ ለመፈጸም ስላለመቻልዎ በቂ የሆነ ግምት ሲኖራቸው፣
  • በንብረቱ ይዞታ ላይ ምርመራ ማድረግ ሲፈልጉ (ይህን ማድረግ የሚችሉት ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ምንም ዓይነት ምርመራ ያልተደረገ ከሆነና የኪራይ ግንኙነቱ በተጀመረበት በ3 ወራት ውስጥ ካልሆነ ነው)


አከራዩ ወይም ወኪሉ ወደቤትዎ መግባት ከፈለጉ የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡-

እንዲሁም እርስዎ ከ7 ቀናት በፊት ወደ ቤትዎ መግባት እንዲችሉ ፈቃድዎን ሰጥተው ከሆነ አከራዩ ወይም ወኪሉ በማናቸውም ምክንያት ወደ ቤትዎ መግባት ይችላሉ፡፡ ይህም መግባት እርስዎ በተስማሙበት ሰዓት ውስጥ ሲሆን ለጉብኝቱ አስፈላኪ ከሆነ አከራዩ ወይም ነጋዴ ወይም ሌላ ሰው ይዘው መምጣት ይችላሉ፡፡

ተገቢውን ማስታወቂያ የሰጡዎት ከሆነ ሰዓቱ የማይመችዎት ቢሆንም ወይም ቤቱ ውስጥ የማይኖሩ ቢሆንም እንኳን አከራዩ ወይም ወኪሉ ወደ ቤቱ ውስጥ እንዲገቡ መፍቀድ ይኖርብዎታል፡፡   ሆኖም እርስዎ ሊመችዎት የሚችለውን ሰዓት መደራደር ይችላሉ፡፡ ወደ ቤትዎ የሚገባው ሰው ተገቢውን የሚጠበቅ ባህርይ ማሳየት የሚኖርበት ሲሆን የመጡበትን ጉዳይ እንደጨረሱም ወዲያውኑ ቤቱን ለቅቀው መሄድ ይኖርባቸዋል፡፡ 

በቂ አሳማኝ ምክንያት ካላቀረቡ በስተቀር አከራዩ ወይም ወኪሉ ትክክለኛውን ሥርዓት ካልተከተሉ ቤትዎ መግባታቸው የወንጀል ድርጊት ተደርጎ ሊወሰድ ይቻላል፡፡

አከራዩ ወይም ወኪሉ ቤትዎ ውስጥ በገቡበት ወቅት በንብረትዎ ላይ ጉዳት ደርሶ ከሆነካሣ እንዲሰጥዎት ለማመልከት ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእግድ ትዕዛዝ

አከራዩ ወይም ወኪሉ ተገቢውን ወደ ቤት የመግባት መሥፈርት ካልተከተሉ ወይም ተደጋጋሚ ወይም ምቾት በሚነሳዎት ሁኔታ የሚመጡ ከሆነ የዕግድ ትዕዛዝለማግኘት ለ Victorian Civil and Administrative Tribunal (VCAT) ማመልከት ይችላሉ፡፡  ይህም በስልክ ወይም ደብዳቤ በመጻፍ ምቾትዎን መንሳትን ይጨምራል፤ ምክንያቱም በሰላም በቤትዎ ውስጥ የመኖር መብትዎን የሚጥስ ስለሆነ ነው፡፡ የዕግድ ትዕዛዙአከራዩ ወይም ወኪሉ ወደ ቤትዎ እንዳይገቡ ለመከልከል ወይም ለማገድ፣ ወይም እንዳይገናኙዎት ለማድረግ የሚችል ሲሆን ይህም በፖሊስ አማከይነት እንዲፈጸም ለማድረግ ይችላል፡፡  አከራዩ ወይም ወኪሉ የዕግድ ትዕዛዝ የሚጥሱ ቢሆን ይህ የወንጀል ድርጊት ተደርጎ ሊወሰድ የሚቻል ሲሆን ክስ ሊቀርብባቸውም ይችላል፡፡  

 እንደ ድንገተኛ አደጋ የመሰለ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ተገቢውን መሥፈርት ሳያሟሉ ወደ ቤትዎ የገቡ ከሆነ ይህ የወንጀል ድርጊት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ሕጉን ያልተከተሉ ከሆነ ለConsumer Affairs Victoria ማመልከት የሚችሉ ሲሆን አከራዩ ወይም ወኪሉ ላይ ሕግ የመጣስ ማስታወቂያ ሊያወጣባቸው ይችላል፡፡

ቤቱን ለቅቆ ስለመውጣት

አከራዩ ወይም ወኪሉ ምቾት በሚነሳዎት ሁኔታ የሚነዘንዙዎት ከሆነ ውልዎን አቋርጠው ከቤቱ ለመውጣት ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ የጊዜ ወሰን ያለው የቤት ኪራይ ውል የሌለዎት ከሆነ የ28 ቀናት ማስታወቂያ ሰጥተው ከቤቱ ሊለቁ ይችላሉ፡፡ ማስታወቂያውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ በተመዘገበ ፖስታ መላክና ፖስታው እስከሚደርስም በቂ ጊዜ መስጠትዎ የሚመከር ሃሳብ ነው፡፡ የፖስታ ማድረሻ ጊዜያትን በተመለከተ Australia Post ንይመልከቱ፡፡ አከራዩ ቀደም ሲል ተስማምቶ ከሆነ ለመልቀቅ ፍላጎት ያለዎት መሆኑን የሚገልጸውን ማስታወቂያዎንበኤሌክትሮኒክስ ዘዴ (ለምሳሌ በኢሜይል) ለመላክ ይችላሉ፡፡ ማስታወቂያውን በኢሜይል የሚልኩ ከሆነ የኢሜይል አድራሻው አከራዩ ወይም የሪል ኤስቴት ወኪሉ የሰጡዎት አድረሻ መሆኑን ማረጋገጥ የሚኖርብዎት ሲሆን የሚቻል ከሆነ ማስታወቂያውን ያነበቡት ስለመሆኑ የሚያረጋግጡበትን ደረሰኝ ማግኘት ይኖርብዎታል፡፡

በጊዜ የተወሰነ የኪራይ ስምምነት ያለዎት ከሆነ በሰላም በቤትዎ የመኖር መብትዎን የጣሰ በመሆኑ ለአከራዩየ14 ቀናት ግዴታን ያለመወጣት ማስታወቂያመስጠት ይኖርብዎታል – አከራዮች ግዴታቸውን ሲጥሱ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ፡፡  ከዚያ በመቀጠል እንዲፈጸም የሚያስገድድ ትዕዛዝእንዲሰጥዎት ለ VCAT ማመልከት ይችላሉ፡፡ ምቾት በሚነሳዎት ሁኔታ መነዝነዛቸውን ካላቆሙ የ VCAT ትዕዛዝን በመጣሳቸው ለአከራዩየ14 ቀናት ከቤቱ ለመውጣት ሰለመፈለግዎ የሚገልጽ ማስታወቂያሊሰጡ ይችላሉ – ለተጨማሪ መረጃ ውልን ስለመጣስ  የሚለውን ክፍል ይመልከቱ፡፡ መቼ መልቀቅ እንደሚችሉ ምክር ከፈለጉ እኛን፣ የአካባቢዎን የTAAP አገልግሎት፣ Tenancy Plus ወይም የአካባቢ ሕግ ማዕከልን መገናኘት ይቸላሉ፡፡ 

አከራዩ ወይም ወኪሉ በቤትዎ ውስጥ በሰላም ለመኖር ያለዎትን የጣሱ በመሆኑካሣለመጠየቅ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 

ቁልፎች

የቤትዎን ቁልፍ የሚቀይሩ ከሆነ የቁልፉን ኮፒ ለአከራዩ መስጠት ይኖርብዎታል፡፡ በቤተሰብ ጸብ የደህንነት ማስታወቂያየጣልቃ ገብነት ትዕዛዝ፣ ወይምየግል ደህንነት ጣልቃ ገብነት ትዕዛዝሥር ካልሆኑ በስተቀር ደህንነትዎን ለመጠበቅ ብለው ቁልፉን ባይቀይሩ እንመክራለን፡፡   ቁልፉን ለአከራዩ ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑ አከራዩግዴታን የመጣስ ትዕዛዝሊያወጣብዎት ይችላል፡፡ 

የአከራዩን ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር የማስተር ቁልፍ ሲስተም አካል የሆነ ማናቸውንም ቁልፍ መቀየር አይኖርብዎትም (ብዙ በሮችን ለመክፈት የሚችል ለምሳሌ በአንድ ሕንጻ ላይ ያሉ ሁሉንም በሮች ለመክፈት የሚችል)፡፡   አከራዩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው የበሩ ቁልፍ መቀየሩን ከተቃወመ የአከራዩ ፈቃድ ባይኖርም ቁልፉ እንዲቀየር ትዕዛዝ እንዲሰጥልዎ ለ VCAT ማመልከት ይችላሉ፡፡

ቁልፎች እና የቤተሰብ ጸብ ወይም የግል ደህንነት ትዕዛዞች/ማስታወቂያዎች

በቤተሰብ ጸብ የደህንነት ማስታወቂያየጣልቃ ገብነት ትዕዛዝ፣ ወይም የግል ደህንነት ጣልቃ ገብነት ትዕዛዝመሠረት ጥበቃ የሚደረግልዎት ሰው ከሆኑና መልስ ሰጭው (ጥቃቱን የፈጠረው ሰው) ከቤትዎ እንዲገለል ተደርጎ ከሆነ የማስተር ቁልፍ ሲስተም አካል የሆነን ቁልፍ ጨምሮ የውጭ በርና መስኮቶችን ቁልፎች ለመቀየር መብት አለዎት፡፡  በውሉ ላይ ስምዎ እንደይጠቀስ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቤቱ ውስጥ ግን መኖር ይኖርብዎተል፡፡ ቁልፉን ለሌሎች በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ነዋሪዎች መስጠት ይገባዎታል (ከተጠሪው በስተቀር)፡፡

አዲሱን ቁልፍ እና የቤተሰብ ጸብ ወይም የግል ደህንነት ማስታወቂያ ትዕዛዙን ቅጂ ለአከራዩ ወይም ለወኪሉ መስጠት ይኖርብዎታል፤ ሆኖም ማስታወቂያው ወይም ትዕዛዙ ወቅታዊ እስከሆነ ድረስ አከራዩ ወይም ወኪሉ ቁልፉን ለተጠሪው እንዲሰጡ አይፈቀድላቸውም፡፡ 

ቁልፉን ለመቀየር ለሚከፍሉት ገንዘብ ድጋፍ የሚያስፈልግዎት ከሆነ ለአስቸኳይ ገንዘብ እርዳታ Victims of Crime Assistance Tribunal(VOCAT) ማመልከት ይችላሉ፡፡  ለበለጠ መረጃየወንጀል ሰለባዎችስልክ ቁጥር 1800 819817 (ነጻ ስልክ) ላይ ይደውሉ፡፡ እንዲሁምየአካባቢ የሕግ አገልግሎት ማዕከልየጣልቃ ገብነት ትዕዛዝ በማውጣት እና VOCAT ዘንድም ሊረዳዎት የሚችል ሲሆንThe Orange Doorየሚባለው ደግሞ የሕግና የገንዘብ ድጋፍ አገልግሎት ሊሰጡ ከሚችሉ አካላት ጋር ሊያገናኝዎት ይችላል፡፡

ምስጢር ስለመጠበቅ

እነዚህ ሕጎች የሪል ኤስቴት ወኪሎች የእርስዎን የግል መረጃዎች እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የሚቆጣጠሩ ሕጎች ናቸው፡፡ የእርስዎ የግል መረጃዎች እየተያዙ ባለበት ሁኔታ ላይ ቅሬታ ካለዎት የAustralian Information Commissionerበስልክ ቁጥር 1300 363 992ላይ ይደውሉ ወይም አቤቱታዎን በጽሁፍ ማቅረብ ከፈለጉ ለConsumer Affairs Victoria ወይም ለ Real Estate Institute of Victoriaያቅርቡ፡፡   

 

ሕጉ 

Residential Tenancies Act 1997 (AustLII website)
section 67 – quiet enjoyment
section 70 – locks
section 70A – locks for properties subject to intervention orders/notices
section 71 – applying to VCAT to change locks without consent
section 85 – entry of rented premises
section 86 – grounds for entry
section 87 – manner of entry
section 88 – what must be in notice of entry?
section 89 – duty to allow entry if requirements met
section 90 – applying to VCAT for compensation if damage is caused during entry
section 91 – applying to VCAT for a restraining order
section 91A – offence to enter premises without meeting requirements

ተዛማጅ ገፆች

ኣከራይ እየሸጠ ነው
ቅሬታ ማቅረብ
ለተከራዮች ስለሚሰጥ ካሣ
ከቤቱ መልቀቅ ሲፈልጉ
የኪራይ ውልዎን ስለማፍረስ
የቤት ኪራይ ስለመጀመር
በቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት (VCAT)

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept