ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ግላዊነት ፖሊሲ

የርስዎን መብት ለመከላከል ቃል መግባት

የርስዎም መረጃ ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ ለመጠቀም በቪክቶሪያ የተከራዮች ማሕበር/Tenants Union of Victoria/Tenants Victoria (TUV) ቃል ይገባል። በአውስትራሊያ የግላዊነት መርሀ ግብር/Australian Privacy Principles መመሪያ እንከተላለን እንዲሁም በሌላ ህጎችና ስነስርዓቶች/codes and standards ላይ ማትኮር አለብን።

የግለሰብን መረጃ ለንምና እንዴት መሰብሰብና የግላዊነትን መረጃ መጠቀም እንዳለብን እንዲገባዎት ይህ የግላዊነት ፖሊሲ እንደሚረዳዎ እንዲሁም ጥያቄዎች፣ አሳሳቢ የሆነ ነገር ወይም ቅሬታ ካለዎት ምን እንደሚያደርጉ ያስረዳዎታል። በዚህ ፖሊሲ ላይ ብዙጊዜ ለውጥ ስለምናደርግ ታዲያ በመጨረሻ ጊዜ የተቀየረበትን ቀን በታችኛው ገጽ ላይ እናሳውቃለን።

ያስታውሱ፡ ከእኛ ጋር ባለው የግላዊነት መረጃዎ ቁጥጥር ስር ነዎት።

በቪክቶሪያ ተከራዮች ህጋዊ የሆነ አገልግሎት (TULS) በኩል ህጋዊ የሆነ ምክርና እርዳታ የምናቀርብልዎት ከሆነ ያለንን ሙያዊ ግዴታ ለመፈጸም ሲባል መጠየቅ ያለብን አንዳንድ መረጃዎች አሉ። በእኛ ህጋዊ የሆነ አገልግሎት በኩል የግላዊነት መረጃን እንዴት መውሰድና መጠቀም እንደሚቻል የሚገልጽ የTULS ግላዊነት ፖሊሲ/ TULS Privacy Policy አለን።

በአብዛኛው ሁኔታ ላይ ለእኛ ምን ዓይነት መረጃ እንደሚያቀርቡ መምረጥ እንዲሁም እነዚህን ዝርዝር መረጃ በማንኛውም ጊዜ መጠቀም ወይም ለመቀየር ይችላሉ።

ምን ዓይነት መረጃ ነው የምንወስድ?

ከርስዎ ጋር እንድንሰራ የሚረዳ መረጃን ብዙጊዜ የቪክቶሪያ ተከራዮች ማሕበር/ TUV ይጠይቃል። ለምሳሌ፡ የርስዎን ገንዘብ ምጽዋት ማካሄድና ደረሰኝ መስጠት፣ ወይም የርስዎን በፌርማ ድጋፍ መመዝገብ ወይም ለፓርላሜንት አባል ደብዳቤ መጻፍ። ምን ያህል መረጃ ማቅረውብ እንዳለብዎ ይህ የርስዎ ምርጫ ነው (ስለዚህ አንዳንድ መረጃዎችን ካልሰጡ ለተጠየቀው ማሟላት አንችል ይሆናል)

በአጠቃላይ ምን ዓይነት መረጃ እንደምንሰበስብ ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ምሳሌዎች ናቸው:

 • ግላዊ ዝርዝር መረጃ እንደ ስም ወይም የተወለዱበት ቀን
 • ለማነጋገር ዝርዝር አድራሻ
 • ለገንዘብ ምጽዋት ክፍያ መረጃ
 • ፍላጎትና ግላዊ አመለካከት
 • በመስመር ላይ ተሳትፎ
 • ለእኛ ሥራ ያለዎት ድጋፍ እንደ በጋራ አቤቱታ ማቅረቢያ መፈረም፣ በድርጊት ፍጻሜ ማስተናገድ ወይም በፕሮጀክት ላይ ተሳትፎ ማድረግ
 • ምናልባት እርስዎ ለመደገፍ የሚፈልጉት ሌላ የእኛ ሥራ መስኮች
 • በንግግር ግንኙነት ማድረግ የሚፈልጉበት
 • ከእኛ ሠራተኞችና በፈቃደኛነት ከሚሰሩት ጋር ለመነጋገር በስልክ ወይንስ በኢሜል

 

በአብዛኛው ጉዳዮች ላይ ለዚህ መረጃ እኛ በቀጥታ እንጠይቅዎታለን (ለምሳሌ፡ ለምጽዋት ገንዘብ ኩቦንን ለመሙላት ወይም የጥናት መጠየቂያ ወረቀት መላክ) ይሁን እንጂ አንዳንድ መረጃዎች አውቶማቲካል በቀጥታ ይሰበሰባሉ (እንደ በእኛ ድረገጽ ለሚጠቀሙ ጎብኝዎች በመስመር ላይ እንቅስቃሴ) ወይም ከሌላ መገልገያ ምንጭ (ከአውስትራሊያ ፖስታ ወቅታዊ በሆነ እንደ የመላኪያ አድራሻ፣ በህዝባዊ አድራሻ ማውጫ ዝርዝር የቀረበ መረጃ፤ ወይም ከግንኙነትና እንክብካቤ ሰጭ ድርጅቶች ወይም ሶስተኛ አካል አቅራቢዎች ለወደፊት ደጋፊዎች የሚሆኑትን ዝርዝር መረጃ ማግኘት)።

እንዴት የርስዎን መረጃ ደህንነት መጠበቅና ማስቀመጥ እንችላለን?

የርስዎን ግላዊነትና ግላዊ መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በሚያነጋግሩን ጊዜ ማንነትዎን ለማረጋገጥ ቀደም ሲል ስለርስዎ ካስቀመጥናቸው ጥቂት ዝርዝር መረጃዎች እንዲነግሩን እንጠይቃለን ይህም እንደ የአሁኑ አድራሻዎ፣ ስልክ ቁጥር፣ እና ጠቃሚ የሆነ መለያ ወይም የገቢ ወጪ መግለጫ ቁጥር።

አብዛኛውን ግላዊ የሆነ መረጃዎን በእኛ ምክር ወይም የኮምፑውተር መረጃ ደጋፊ ውስጥ ደህንነቱ ይጠበቃል እንዲሁም የመረጃው ደህንነት የተጠበቀ ስለመሆኑ ለማረጋገጥር በየጊዜው ምርመራና ኦዲት ቁጥጥር ይደረጋል። የርስዎ መረጃ ቅጂ ወረቀቶች ማለት እንደ የመጽዋት መስጫ ቅጾች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንደሚቀመጥና አስፈላጊም ከሆነ ይደመሰሳል። ሠራተኞችና በፈቃኛነት የሚሰሩ ሰዎች ከግላዊነት ጋር በተዛመደ የእኛ ፖሊሲዎች ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል እንዲሁም ስሜት በሚነካ ተግባራት ለማካሄድ የፖሊስ ማጣሪያ ይካሄዳል።

አንዳንድ ጊዜ የርስዎ መረጃ ከአውስትራሊያ ውጭ በሌላ አገር ማስቀመጥ ወይም መጠቀም ያስፈልገን ይሆናል፤ ምክንያቱም አንደኛው የእኛ ተክኒካል አሰራር ዘዴ በዚያ አገር ስላለ ወይም ጥሬ መረጃን በውጭ አገር ማጣራት ስለሚያስፈልግ (ለምሳሌ፡ ሶሻል መዲያ ቻነልስ/social media channels)። ይህ ፖሊሲ ለመጨረሻ ጊዜ ወቅታዊ ለውጥ ሲደረግ፤ ጥሬ መረጃ በምንጠቀምባቸው አገሮች የሚካተት:

 • ካናዳ/Canada
 • ዩናይትድ ኪንግዶም/United Kingdom
 • ዩናይትድ ስተትስ/United States

 

እንዴት ይህንን መረጃ እንጠቀማለን?

የእኛን ዋና ሥራ ለማሟላት ሲባል ግላዊ የሆነ መረጃ እንሰበስባለን ይህም ከህዝባዊ ጋር ለመሥራት ስለሚረዳ፤ ስለ ተከራይና አከራይ ጉዳዮች በጥቀስ ለማሳወቅ እና የገንዘብ እርዳታ ለማሰባሰብ ይረዳል። በሚገባ ብቃት ባለው እንድናውቅ እንዲረዳን እና ከ TUV ጋር ሲገናኙ የርስዎ ታሪክ ትክክለኛ ሪኮርድ መዝገብ እርግጠኛ ስለለመሆኑ ለማጣራት ከርስዎ መረጃ እንሰበስባለን። ለምሳሌ፡ ይህንን መረጃ የምንጠቀመው እርስዎ ከሚፈልጉት ጉዳይ ጋር መረጃዎን ወቅታዊ ለማድረግ፣ የTUV ሥራን ለመደገፍ እድሉን ለማቅረብ ወይም እኛ ልንረዳዎ ወይም እርስዎ ሊረዱን የሚችሉበትን ሌሎች መንገዶች ለማሳወቅ ነው።

አልፎ አልፎ ባሉን እንቅስቃሴ ተግባራት ላይ የውጭ አቅራቢዎች እንዲረዱን ስለሚፈለግ ታዲያ ይህንን ለማከናወን የርስዎን መረጃ ሊሰጣቸው ይችላል – ለምሳሌ፡ ብዛት ያለው የታተሙ ደብዳቤዎች ለእኛ አቅራቢዎች ይሰጣል።

መረጃውን ሌላ ሰው መጠቀም እንዲችል ከፈለጉ ወይም እርስዎን ወክሎ ዝርዝር መረጃዎን የሚቀይር ሰው (ባልና ሚስት፣ የህግ ወይም የፋይናሻል ተወካይ) ካለ በጽሁፍ አድርገው ለእኛ ማሳወቅ እንደሚችሉና ታዲያ ለዚህ የፈቃድ ሪኮርድ መመዝገብ እንችላለን።

እንዲሁም ምጽዋት አቅራቢ ወይም ደንበኛ ለመሆን ፍላጎት ካለዎት ለግንኙነትና እንክብካቤ ሰጭ ድርጅቶችን በመወከል በየጊዜው ለርስዎ መረጃ ለመላክ ያለዎትን መረጃ ልንጠቀም እንችላለን። የእርስዎ ዝርዝር መረጃ ለእነሱ እንደማይሰጥና በቀጥታ ለነርሱ የሚሰጡት መረጃ በነሱ ሪኮርድ ምዝገባ ለማስቀመጥ ብቻ ነው። በነዚህ ዓይነት ግንኙነት ላይ እንድናነጋግርዎ ካልፈለጉ፤ እባክዎ ያነጋግሩን (ከዚህ በታች በቀርቧል)።

በሆነ ምክንያት የርስዎን መረጃ ከሶስተኛ አካል ጋር መለዋወጥ ካስፈለገን ታዲያ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንደሚሆን ማረጋገጥ እንዳለብንና ይህም ከዚህ በላይ ለተጠቀሰው ዓላማ ብቻ ይሆናል።

በመስመር ላይ እንቅስቃሴ እና ብዝባዊ መገናኛ ዘዴ

በእኛ ድረገጽ ላይ ለማየት በጎግል ትንተና/Google Analytics እና በሌላ የድረገጽ አገልግሎት/ webserver ማመልከቻዎች ላይ ከፍተን እንደምንጠቀምና ታዲያ በጥሩ ሁኔታ ያለንን ድረገጽ ለመክፈት ይህንን መረጃ መጠቀም፤ ማለት እንደ ጉብኝት፣ የጉብኝት ጊዜ፣ የሚታዩ ገጾች እና የእኛ ጎብኝዎች ተክኒካል አቅም ይሆናል። ብዙጊዜ የዚህ ጥሬ መረጃ ማንነት ስለማይታወቅ፤ አንዳንድ ጊዜ ይህንን መረጃ በተመለከተ ከርስዎ ጋር እናገናኛለን፤ ለምሳሌ፡ ድረገጽ ገጽን/ webpage በግላዊነት መያዝ፤ ወይም ስለርስዎ ዝርዝር መረጃ ያለውን ቅጽ ቀደም ብሎ መሙላት። ለበለጠ መረጃ በጎግል ግላዊነት ፖሊሲ ላይ የጎግል ግላዊነት ፖሊሲ/Google’s Privacy Policy የሚለውን ማንበብ።

እንዲሁም የእኛን ይዘት ለማየት መቸ ኮምፑውተር ወይም መሳሪያ መጠቀም እንዳለብን የሚነግር መሳሪያዎች እንጠቀማለን ታዲያ በእኛ ድረገጽና በሌላ የድረገጽ ማስታወቂያ ማስተላለፊያ መርበብ በኩል የሚተላለፍና በርስዎ ጉብኝትና ባህሪ መሰረት ባደረገ የርስዎ መሳሪያ ማሳያ/cookies አማካኝነት ይሆናል። እንዴት ማሳያው/cookies እንደሚጠቅም እና በርስዎ ብራውዘር ማውጫ ላይ ምን እንደደሚቀናጅ መቆጣጠር ይችላሉ።

እንደ ፌስ ቡክ/ Facebook, ትዊተር/Twitter, ኢንስታግራም/Instagram ወዘተ。ያሉት ከ TUV ህዝባዊ መገናኛ ዘዴ ጋር ሊገናኙ ይችላሉ። በእያንዳንዱ የድረገጽ ድባብ በኩል ለሚያገኙት ይዘት ሁልጊዜ መቆጣጠር እንደሚችሉ ነው። በርስዎ ሪኮርድ ላይ ባለው ዝርዝር መረጃ ማለት እንደ ኢሜል አድራሻ የማይጠቀሙ ከሆነ አልፎ አልፎ በህዝባዊ መገናኛ ዘዴ በኩል ልናገኝዎ እንችል ይሆናል። በዚህ ዓይነት እንድናገኝዎት ካልፈለጉ እባክዎን ያነጋግሩን።

የርስዎን መረጃ ስለመንከባከብ

ከርስዎ የወሰድነውን መረጃ ወቅታዊ ማድረግ ወይም ማረም ይችላሉ ወይም ከርስዎ ጋር እንዴት ግንኙነት ማካሄድ እንዳለብን ፍላጎትዎን ለእኛ አስተዳድር ቡድን በማነጋገር ያሳውቁን:

 • በስልክ: 03 9411 1444 (ከሰኞ እስከ ዓርብ 9am – 5pm, AEST/AEDT)
 • በኢሜል: admin@tuv.org.au
 • በፖስታ: Tenants Union of Victoria Ltd, P O Box 234, Fitzroy VIC 3065

 

ጥያቄ ወይም ቅሬታ ክስ ስለማስገባት

የርስዎን ግላዊ የሆነ መረጃ በእንዴት መልኩ ስለምንይዘው ጥያቄ ወይም ቅሬታ ካለዎት ወይም ከዚህ የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ ከዚህ በላይ ባለው መረጃ በመጠቀም ለአስተዳደር ቡድን ማነጋገር ይችላሉ።

ቅሬታ አስገብተው ከሆነ ለአስተዳደር ቡድን ስለመድረሱ የሚገልጽና የእነሱ ዝርዝር መረጃ አድራሻ ያለበት ደብዳቤ ይደርስዎታል እንዲሁም የርስዎ ቅሬታ ሁኔታ መቸ ወቅታዊ ማድረግ እንደሚችሉ ግምታዊ የሆነ ጊዜ ይሰጥወታል።

ስለርስዎ ግላዊነት መረጃ ስለመጠበቁ የበለጠ መረጃ ለማግኘት OAIC website የሚለውን ድረገጽ ማየት

[መጨረሻ የተሻሻለበት ቀን: 30/6/2014]


Privacy policy | Amharic

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept