ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ

ኣከራይዎ  ቤቱን ለቅው እንዲወጡ የፈለገ እንደሆነ፣ ልእርስዎ  ህጋዊ የሆነ የመልቀቅ ማስታወቂያ (notice to vacate) መስጠት ኣለባቸው። ኣከራይዎ  የመልቀቅ ማስታወቂያ (notice to vacate) እንዲሰጥዎት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ የማስታወቂያው የጊዜ መጠንም በ ኣከራይዎ ለምን ማስታዎቂያውን እንደሰጥዎት እና እርስዎ ውስን-ወቅት የኪራይ ስምምነት (fixed-term tenancy aggreement) እንዳለዎ ወይም እንደሌለዎ ይወሰናል።

የመልቀቅ ማስታወቂያ (notice to vacate) ስለደረስዎት ብቻ፣ ለቀው መውጣት ኣለብዎት ማለት ኣለመሆኑን ማወቅ ኣስፈላጊ ነው። ኣከራይዎ  ሊያስወጥዎ  ከፈለጉ፣ በመጀመርያ በ የቪክቶሪያ ሲቪል እና ማስተዳደርያ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከት፣ እንዲሁም የ ንብረት የመያዝ ትእዛዝ (possession order) እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ማሳመን ኣለባቸው።

ወዲያውኑ ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ

ኣከራይ የተከራዩት ቤት ከተበላሸ ወይም እንዲኖርበት ብቁ ካልሆነ ወዲያውኑ ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ ሊለጥዎ ይችላል። እርስዎ (ወይም ቤትዎ የመጣ እንግዳ) ኣውቆ ንብረትን ካበላሹ ወይም የጎረቤቶን ደህንነት ኣደጋ ላይ ከጣሉ ኣስቸኳይ ማስታወቂያ ሊሰጥ ይችላል።

ፍርድ ቤቱ በነዚህ ኣይነት ጉዳዮች ከፍተኛ ማስረጃ ከኣከራዩ ይፈልጋል።  እርስዎ  ወዲያውኑ ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ የደረስዎት እንደሆን ለኣጣደፊ ምክር እኛን ያግኙን።

በ14-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ

በ14-ቀን ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ ሊሰጥ የሚችለው፤

 

 • ኪራይዎ ክፍያ 14 ቀናት ከዘገየ (ማለትም ካልተከፈለ)
 • የክራዩን ውል መያዣ ክፍያ ያልከፈሉ እንደሆነ (የኪራይ ውልዎ የመያዣ ክፍያ መክፈል ኣለብዎ የሚል ከሆነ)
 • እርስዎ ያለኣከራዩ ፈቃድ ቤቱን ከሰጡ ወይም ካከራዩ
 • የክራይዎ ውል ሁኔታ በቤቱ ልጆች እንዲኖሩ የሚከለክል ከሆነ እና እርስዎ ይህንን ሁኔታ ካፈረሱ
 • ቤቱን ለህገወጥ ጉዳይ ከተጠቀሙ (ወይም ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉ ከፈቀዱ)
 • በፍርድ ቤቱ በ ኣር ቲ ኤ (RTA)ክፍል 212 መሰረት በተደረገ መሟላት ያለበት ትእዛዝን ለሟሟላት ካላሳኩ
 • ሃላፊነትን ካፈረሱ እናም ከዚህ በፊት ያንኑ ሃላፊነት በማፍረስ ሁለት ጊዜ የ ሃላፊነትን ያለመወጣት ማስታወቂያ ደርስዎት ከነበረ
 • እርስዎ ህዝባዊ ተከራይ (public tenant) ከሆኑ እና የህዝባዉ ቤቶች ኣከራይን ስለ ለህዝባዊ ቤት ብቁነትዎ የዋሹ እንደሆነ
 • እርስዎ ህዝባዊ ተከራይ (public tenant) ከሆኑ እና በቤቱ ውስጥ ወይም በጋራ ቦታ ላይ ዕፅ የሚነግዱ ወይም ለመነገድ የሞከሩ እንደሆነ፣ ከ18 ዓመት በታች ለሆነ ዕፅ የሰጡ እንደሆነ፣ የዕፅ ተክል ያሳደጉ ወይም ለማሳደግ የሞከሩ እንደሆነ፣ ወይም ለመነገድ የሚያመቻቹ እቃዎችን የያዙ እንደሆነ

 

የኣከራይ ዋና የመኖርያ ቤት ቦታ

ቤቱ እርስዎ  ከመግባትዎ  በፊት የኣከራይ ዋና የመኖርያ ቤት ቦታ የነበረ እንደሆነ፣ ለመልቀቅ የ14—ቀናት ማስታወቂያ ሊሰጡዎት ይችላሉ፣

 • እርስዎ  ውስን—ወቅት (fixed-term) የኪራይ ውል ስምምነት ያለዎት፣ እንዲሁም
 • በማስታወቂያው ላይ ያለው እለት በ የኪራይ ወቅት ስምምነት ማብቂያ ቀን ወይም በኋላ የሆነ እንደሆነ፣ እንዲሁም
 • በኪራዩ የስምምነት ላይ እርስዎ ከመግባትዎ በፊት ቤቱ የኣከራይ ዋና የመኖርያ ቤት ቦታ እንደነበረ ከተጠቀሰ፣ እንዲሁም
 • ኣከራዩ  በ ውስን የኪራይ ወቅቱ መጨረሻ ላይ ተመልሶ ሊገባበት ሃሳብ እንዳለው በኪራይ ስምምነቱ ላይ የተጠቀሰ እንደሆነ።

 

በ 28-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ  በ የቦታው ባለንብረት

እርስዎ  ከመከራየትዎ  በፊት በቤቱ ላይ በባለንብረትነት የተጠቀሰ ካለ፣ ባለንብረቱም (ኣብዛኛውን ጊዜ ባንክ) የቤቱ ይዞታ፣ ወይም ቤቱን የመሸጥ መብት ከተሰጠው፣ ባለንብረቱ  በ 28-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ (Notice to Vacate) ሊሰጥዎ  ይችላል።
በኣብዛኞች ሁኔታዎች፣ ተከራዮች የንብረት ይዞታ ችሎቱን ለመሳተፍ፣ እናም የመውጣት ትእዛዙ በፖሊስ ከመተግበሩ በፊት ጊዜውን ለማዘግየት ሊጠይቁ ይችሉ ይሆናል ፍርድ ቤቱ በትልቁ እስከ 30 ቀናት ሊሰጥ ይችላል ትእዛዙ ከመውጣቱ በፊት።
በ ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ በባለ ንብረቱ (Notice to Vacate by the mortgagee) ምክንያት ቤቱን ለመልቀቅ ከተገደዱ፣  ከኣከራዩ  ካሳ ለመጠየቅ ይችሉ ይሆናል። ለነዚህ ጉዳዮች ምክር መፈለግ ያስፈልጋል።

በ 60-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ

በ 60-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ የሚሰጠው ውስን ወቅት  ኪራይ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ብቻ ነው፣ ወይም በማስታወቂያው ላይ ያለው የማብቂያው እለት (ይህም እንዲለቁ በተሰጥዎ ወይም እስከ ተሰጥዎ እለት)በ ውስን ወቅት ኪራይ ስምምነቱ ማብቂያው እለት ወይም ከዛ በኋላ ነው።

ኣከራይ ከ60-ቀን ጊዜው እንዳበቃ፣ ወዲያውኑ የ 60-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ ሊሰጥዎ ይችላል፣ ይህም የሚሆንበት መሰረቱ፣

 

 • የፈረሰ
 • ከኪራይ ቤት ሌላ ለማንኛውም ጥቅም የዋለ እንደሆነ (እንደ ንግድ)
 • ኣከራይ የገባበት እንደሆነ፣ ወይም የኣከራይ ባለቤት፣ ወንድ ልጅ፣ ሴት ልጅ፣ ወላጅ ወይ የባለቤት ወላጅ፣ ወይም በተለምዶ ከኣከራይ ጋር የሚኖር እና በኣከራይ ጥገኛ የሆነ ሰው
 • የተሸጠ ወይም በባዶ ሁኔታ ለሽያጭ ከቀረበ
 • ጥገና፣ እደሳ ወይም እንደገና መሰራት፣ እናም ይህ ቦታው ባዶ ካልሆነ በስተቀር ሊደረግ የማይቻል ከሆነ
 • ለህዝብ ጉዳይ ጥቅም ላይ ከዋለ (የህዝብ ንብረት ከሆነ)

 

ኣከራዩ ከላይ ለተጠቀሱት የመጀመሪያዎቹ 4 ምክንያቶች ማስታወቂያ ከሰጠ፣ ማስታወቂያ ከሰተሰጠ ለ 6 ወራት ቤቱን እንደገና መልሰው  ማከራየት ኣይችሉም (በማስታወቂያው ላይ ለተጠቀሱት ኣንዱ ሰው ካልሆነ ወይም ከፍርድ ቤቱ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር)።

ኣከራይ የተከራየውን ቤት ለመሸጥ ኮንትራክት ውስጥ ከገባ የ በ 60-ቀን ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ ሊሰጥ ይቻላል።

በ 120-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ

ኣከራይ በ 120-ቀን ያለምክንያት ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያ ሊሰጥ ይችላል ጊዜያዊ የኪራይ ስምምነት ከሌለ (ይህም፣ ውስን ወቅት ከሌለ ወይም ውስን ወቅቱ ከተፈፀመ) ወይም ማስታወቂያው ላይ ያለው የማብቂያ ቀን (ይህም እንዲለቁ በተሰጥዎ ወይም እስከ ተሰጥዎ እለት)በ ውስን ወቅት ኪራይ ስምምነቱ ማብቂያው እለት ወይም ከዛ በኋላ ነው።

ውስን ወቅት የኪራይ ጊዜ (fixed-term lease) ማብቂያ

ኣከራዩ ውስን ወቅት ኪራይ ሲያበቃ ለቀው እንዲወጡ ማስታወቂያ ሊሰጥዎ ይችላል። በማስታወቂያው ላይ ያለው የማብቂያ ቀን ከ ውስን-ወቅት ስምምነት ማብቂያ ቀን ጋር ኣንድ መሆን ኣለበት። ከ 6 ወራት ያነሰ ውስን-ወቅት ስምምነት ከሆነ ያለዎት፣ ኣከራዩ  በ 60-ቀን ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ ሊሰጥ ይችላል፡ 6 ወራት ወይም ከዚያ የበለጠ ውስን-ወቅት ስምምነት ከሆነ ያለዎት፣ ኣከራዩ በ 90-ቀን ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ ሊሰጥ ይችላል።

ውስን ወቅቱ ከመጠናቀቁ በፊት ከለቀቁ ውስን ወቅቱ እስከሚያበቃበት እለት ድረስ ለኪራይ ሃላፊነት ሊኖርብዎ ይችል ይሆናል።

ማስታወቂያ መስጠት

ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ  በተገቢው ቅፅ መሆን ያለበት እና በኣከራዩ  ወይም ወኪሉ ተፈርሞ ቀን የተፃፈበት መሆን ኣለበት።

እንዲያው በደብዳቤ ሳጥንዎ ውስጥ ወይንም በበርዎ ስር ሊተው ኣይችልም። ለእርስዎ  በኣካል መሰጠት፣ በተመዘገበ ደብዳቤ መላክ ኣለበት፣ ወይም ኣከራዩ  በኤለክትሮኒክ መንገድ ለምሳሌ እርስዎ ከተስማሙ በኢሜል ሊሰጥዎ ይችላል። ማስታወቂያ  በኤሌክትሮኒክ ከደረስዎ እና እርስዎ ካልፈቀዱ፣ የኪራይ ኮንትራክትዎን ይመልከቱ ለተጨማሪ ምክርም ይገናኙን።

ማስታወቂያው በደብዳቤ ከተላከ፣ የማስታወቂያው ጊዜ ለእርስዎ የሚደርስባትን ጊዜም መጨመር ኣለበት። ኣውስትራሊያ ፖስጣ የማድረስ ጊዜያትን ይመልከቱ።

ህጋዊ እንዲሆን፣ የመልቀቅ ማስታወቂያው በህግ የሚጠየቀውን ያነሰውን የማስታወቂያ ጊዜ፣ በተጨማሪም ለፖስታው ያሚያስፈልርን ጊዜ፣ እንዲሁም ከመፈፀሚያው እለት ተጨማሪ ኣንድ ቀን መስጠት ኣለበት። የመፈፀሚያው እለት የ ማስታወቂያውን እለት ኣያካትትም። እርስዎም ይህንን የተመዘገበ ደብዳቤ እና የመቆጣጠርያ ቁጥሩን (tracking number) ያስቀምጡ ኣስፈላጊ ማስረጃ ሊሆን ይችላል እና። የተመዘገበውን ደብዳቤ ባይቀበሉም እንኳን፣ ፍርድ ቤቱ በህጋዊ መንገድ እንደደረስዎ ሊቆጥር ይችላል።

ለማስታወቂያው ምክንያቱ በግልፅ መጠቀስ ኣለበት ከነ በቂ ዝርዝር እንዲሁም ምክንያቱ ተቀባይነት ያለው መሆን ኣለበት (ከ የ 120-ቀን ያለ ምክንያት የመልቀቅ ማስታወቂያ  በስተቀር)።

እነዚህን ሁሉ የተጠየቁ ነገሮችን ካላሟላ፣ የመልቀቅ ማስታወቂያ ህገወጥ ነው። ስለ የመልቀቅ ማስታወቂያዎ ህጋዊነት ጥርጣሬ ካለዎት፣ ባስቸኳይ ምክር ይፈልጉ።

ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያን መቃወም

እርስዎ ህገወጥ ነው ብለው ካሰቡ፣ የ 60-ቀን ለቆ ለመውጣት ማስታወቂያን ሊቃወሙ ይችላሉ (የውስን-ወቅት ስምምነት የማብቅያ  ማስታወቂያ ካልሆነ በስተቀር)። ነገር ግን፣ ኣከራዩ ለመውሰድ ችሎት (Poseession Hearing) ለፍርድ ቤቱ ከማመልከቱ በፊት ለመቃወም ከፈለጉ፣ እርስዎ ይህንን የመልቀቅ ማስታወቂያው በደረስዎ 30 ቀናት ውስጥ ማድረግ ኣለብዎት። በ 30 ቀናት ውስጥ ካለተቃወሙ፣ ኣሁንም በ ለመውሰድ ችሎት (Possession Hearing) ላይ ሊቃወሙ ይችላሉ።

እንዲሁም የ 120-ቀን ያለምክንያት ለቆ የመውጣት ማስታወቂያን (120-day no-reason Notice to Vacate) ሊቃወሙ ይችላሉ እርስዎ ማስታወቂያው የተሰጠዎ በ የመኖርያ ቤት የኪራይ ደንብ (Residential Tenancies Act) 1997 መሰረት ላስከበሩት መብትዎ  (ምሳ ጥገናዎችን በመጠየቅ) ብቀላ ነው ብለው ካመኑ። የሚከተሉት የጊዜ ገደቦች በብቀላ ለተሰጡ ማስታወቂያዎች ቅዋሜን ይመለከታሉ፤

 

 • የ 120-ቀን ያለ ምክንያት ለቆ የመውጣት ማስታወቂያን ለመቃወም 60 ቀናት
 • የ 60-ቀናት ውስን-ወቅት ማብቂያ ለቆ የመውጣት ማስታወቂያን ለመቃወም 21 ቀናት
 • የ 90-ቀናት ውስን-ወቅት ማብቂያ ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ ለ የ 6 ወራት ወይም በላይ ውስን ወቅት ለመቃወም 28 ቀናት

 

ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ  የደረስዎት እንደሆነ እና ሊቃወሙት ይችሉ እንደሆነ ለማወቅ ከፈለጉ፣ በተቻለ ፍጥነት ይገናኙን።

ማስታወቂያው ከመውደቁ በፊት ስለመልቀቅ

ውስን-ወቅት ስምምነት ካለዎት ህጋዊ የሆነ ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ  እስካልደረስዎት ድረስ እና ፍርድ ቤቱ ለኣከራዩ  የመውሰድ ትእዛዝ (possession order) እስካልሰጠው ድረስ የኪራዩ  ወቅት እስኪያልቅ ድረስ የመቆየት ህጋዊ መብት ኣለዎት። የውስን-ወቅት ስምምነቱ ከማብቃቱ በፊት ባለ ቀን ለመልቀቅ ኣስበው ማስታወቂያ የሰጡ እንደሆነ፣ ኪራዩን ኣስቀድመው በማቋረጥዎ ቅጣት ይኖረው ይሆናል። የወስን-ቀን ከማብቃቱ በፊት፣ ወይም በማስታወቂያው ከተጠየቀው ኣስቀድመው ለቀው ለመውጣት ከፈለጉ ሁል ጊዜም ከኣከራይ ወይም ከወኪሉ ጋር ለመስማማት መሞከር ይችላሉ። ስምምነቱን በፅሁፍ ማግኘትዎን ያረጋግጡ፣ በእርስዎ እና በኣከራዩ ወይም ወኪሉ የተፈረመ።

ተከታታይ የኪራይ ስምምነት (periodic tenancy) የሆነ ካለዎት፣ በኣንዳንድ ሁኔታዎች ጊዜ ለቆ የመውጣት ማስታወቂያ ከደረስዎት በኋላ የ 14-ቀን ለመልቀቅ የመፈለግ ማስታወቂያ ሊሰጡ ይችሉ ይሆናል። መቼ መልቀቅ እንደሚችሉ ያጣሩ

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የታተመ: ጁን 2017

Notice to Vacate | Amharic | June 2017


Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept