Changes were made to renting laws on 29 March. As parts of our website are not updated yet, see how the changes might affect you.
ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።
የርስዎ ባለንብረት ያለባቸውን ግዲታ ካልተወጡ በነዋሪ ተከራዮች አንቀጽ ህግ/Residential Tenancies Act 1997 ዓ.ም, መሰረት ስለግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይችላሉ። ባለንብረቱ ያለውን ችግር ማስተካከል እንዳለበት በዚህ ማሳሰቢያ በኩል ይነገራል ወይም ግዲታቸውን ባለመወጣት (ወይም በሁለቱም) ለደረሰው ማንኛውም በደልና ጥፋት ማካካሻ ይከፍላሉ።
የግዴታ መጣስ ማሳሰቢያን መቸ ነው መስጠት የሚችሉት?
ባለንብረቱ ግዴታውን ስለመወጣት
የማካካሻ ክፍያ ስለመጠየቅ
የግዴታ መጣስ ማሳሰቢያን እንዴት እንደሚሞላ
ለግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ ምክንያት
ለግዴርታ መጣስ ማሳሰቢያ እንዴት ማደል እንደሚቻል
የርስዎ ባለንብረት ግዴታን የሚጥሰው ለሚከተሉት ካላሟላ ይሆናል:
ባለንብረቱ ጥገና እንዲያካሄድ ከፈለጉ ለግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ መስጠት ይኖርብዎታል። ለምሳሌ፡ ባለንብረቱ በሚኖሩበት ቤት ያለማስጠንቀቂያ እየመጣ ‘ጸጥታ ከነሳዎ’ ታዲያ የግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ መስጠት ወይም ‘መላክ’ ይኖርብዎታል።
ማሳሰቢያ: በደባልነት ቤትና በካራቫን ፓርክ መጠለያ ነዋሪዎች ለየት ያለ የግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ መስጠት ይቻላል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት የተከራዮች ማሕበርን ማነጋገር ነው።
የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ለባለንብረቱ ማሳሰቢያ ሲሆን ይህም ለችግሩ መፍትሄ ካላቀረቡ እና/ወይም የማካካሻ ክፍያ ካልሰጡ ታዲያ ይህንን ማካሄድ እንዳለባቸው ትእዛዝ እንዲሰጥ ለቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት (VCAT) ማመልከት ይችሉ ይሆናል።
የልዩ ፍርድ ቤት ትእዛዝን አለመከተል ወንጀል ሲሆን ይህም ለገንዘብም ሆነ ገንዘባዊ ላልሆነ ትእዛዝ ተግባራዊ ይሆናል።
ባለንብረቱ ያለበትን ማንኝውንም ግዴታ ካልተወጣና በዚህ ምክንያት ለተሰቃዩት ወይም ላጠፉት የግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ በማቅረብ የማካካሻ ክፍያ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ።
የግዴታ ጥሰት ሲፈጸም ባለንብረቱ ያለበትን ግዴታ እንዲያከብር የግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ መስጠት (ቀደም ሲል በዚህ የእውነታ ጽሁፍ ወረቀት ላይ እንደተገለጸው) እንዲሁም ችግሩ ከተስተካከለ በኋላ ለማካካሻ ክፍያ ማመልከቻ በልዩ ፍርድ ቤት ላይ ማቅረብ። ይህ የሆነበት ምክንያት ችግሩ ከመስተካከሉ በፊት ጠቅላላ ጉዳት ወይም የጠፋን ሙሉ በሙሉ ማስላት ስለማይቻል ነው።
የግዴታ ጥሰት ከተፈጸመ ከጥቂት ጊዜ በፊት ከሆነና ችግሩ ከተሰተካከለ አሁንም የማካካሻ ክፍያን ለመጠየቅ የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያውን መጠቀም ይችላሉ። በቅጹ ላይ የሚካተተው የጠየቁት መጠን፣ የትኛው ግዴታ እንደተጣሰ እና ስለ ችግሩ መጀመሪያ ለባለንብረቱ ያነጋገሩበት ቀን ይሆናል።
ከተከራዩበት ቤት ወጥተው ከሆነ የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ መስጠት የለብዎም። ለርስዎ የማካካሻ ክፍያ በቀጥታ ለልዩ ፍርድ ቤት ማመልከት ይችላሉ።
በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ማቅረቡ ያለዎትን የተከራይ ስምምነት ውል ለመጨረስ የመጀመሪያ እርምጃ ሊሆን ይችላል።
የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ከተከራዮች ማሕበር ማግኘት ሲቻል ወይም ከቪክቶሪያ ደንበኛ ጉዳይ ድረገጽ www.consumer.vic.gov.au ላይ ማግኘት ይቻላል።
በማስጠንቀቂያው ላይ ባለ ሳጥን ውስጥ መረጃን መጻፍ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንዴት አድርጎ ቅጹን መሙላት እንደሚቻል መመሪያዎች ናቸው።
የባለንብረቱ ዝርዝር መረጃ
የተከራይ ዝርዝር መረጃ
የአገልግሎት ዝርዝር መረጃ
የተሞላን ግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ለባለንብረቱ በመደበኛ ፖስታ አድርጎ መላክ ወይም በአካል ለባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ማቅረብ ሲቻል ታዲያ ባለንብረቱ ስለደረሰው ማረጋገጥ ይችላሉ። የማስጠንቀቂያውን ቅጅ እና የላኩበትን ደረሰኝ ያስቀምጡት።
አንዴ ማማስጠንቀቂያውን ካደሉ በኋላ ለ14 ቀናት መጠበቅ አለብዎ (ተጨማሪ 2 ቀናት ለፖስታ መፍቀድ)። ከዚያም ባለንብረቱ ችግሩን ካላስጠገነ እና/ወይም የማካካሻ ክፍያ ካልሰጠ፤ ማሳሰቢያውን እንዲፈጽም ትእዛዝ በቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት (VCAT) ላይ ማመልከት ይችላሉ።
በልዩ ፍርድ ቤት ለማመልከት ቅጽ ሞልተው የግዴታ መጣስ ማሳሰቢያ ቅጂውን አብሮ ማያያዝ ይኖርብዎታል። ለበለጠ መረጃ የቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት/Victorian Civil and Administrative Tribunal የሚለውን እውነታ ጽሁፍ ወረቀት ማየት።
ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።
ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች
ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።
Giving your landlord a Breach of Duty Notice | Amharic | July 2013