ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የግዴታን መጣስ ማስጠንቀቂያ የሚያኙት መቸ ነው

Residential Tenancies Act 1997 አንቀጽ ህግ መሰረት ያለዎን ግዴታ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ አላሟሉም ብሎ ባለንብረቱ ካመነበት ለግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ይሰጥዎታል።

ይህ ገጽ

የተከራዮች ግዴታዎች ምንድ ናቸው?
በግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ላይ ምን መካተት አለበት?
ማካካሻ ገንዘብ እና ህጋዊ የሆነ ትእዛዝ
ለማስለቀቅ ማስጠንቀቂያ
ለባለንብረቱ የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት

የተከራዮች ግዴታዎች ምንድ ናቸው?

በአንቀጽ ህጉ መሰረት በሚከተለው ዝርዝር የተከራይ ግዴታዎችን ያሳያል። በነዚህ ግዴታዎች መሰረት ተከራዩ ማድረግ ያለበት:

 • በተከራዩ ጎረቤታሞች ደህንነት ላይ የማናደድ ወይም ጣልቃ የመግባት፣ ምቾትና ግላዊነት ችግር አለመፍጠር
 • የንብረቱን ንጽህና በሚገባ ደረጃ መጠበቅ
 • በንብረቱ ወይም በጋራ መገልገያ አካባቢ ላይ ጉዳት አለማድረስ
 • በንብረቱ ግድግዳ ላይ (እንደ ስእሎችን ማጣበቅ) ወይም ያለ ባለንብረቱ ፈቃድ በንብረቱ ላይ ለውጥ ማካሄድ አይቻልም
 • በንብረቱ ላይ ለውጥ ተደርጎ ከሆነ ቤቱን ከመልቀቅዎ በፊት የንብረቱን ሁኔታ መጀመሪያ እንደነበረው ማድረግ
 • በውጭ ባለ በር ወይም መስኮት ላይ መቆለፊያ ሲቀይሩ ወይም ተጨማሪ ሲያስገቡ ለባለንብረቱ ቁልፍ መስጠት
 • ባለንብረቱ ተገቢ የሆነ ማስጠንቀቂያ በጽሁፍ ካቀረበ ወደ ንብረቱ እንዲገቡ መፍቀድ

 

የግዲታ መጣስ ማሳሰቢያ መደበኛ ማስጠንቀቂያ ሲሆን እንደ ተከራይ መጠን ‘የግዴታ መጣስ ተግባርዎን’ ማቆም እንዳለብዎ እና/ወይም ማስጠንቀቂያው እንደደረስዎ በ14 ቀናት ውስጥ የገንዘብ ማካካሻ መክፈል አለብዎት። ይህንን ካላደረጉ፤ የማስፈጸሚያ ህጋዊ ትእዛዝ በVictorian Civil and Administrative Tribunal እንዲሰጥ ባለንብረቱ ማመልከት ይችላል።

በግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ላይ ምን መካተት አለበት?

የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ህጋዊነት ማግኘት እንዲችል:

 • በአንቀጽ ህጉ መሰረት የትኛው ግዴታ ወይም ግዴታዎች በርስዎ ተጥሷል ብሎ ባለንብረቱ ያመነበትን መጥቀስ
 • ግዴታን በመጣስ ሳቢያ የደረሰን ጉዳት ወይም ወጪ በዝርዝር መስጠት
 • ለጣሱት ግዴታ ማስተካከል እንዳለብዎ እና/ወይም የማካካሻ ገንዘብ መክፈል እንዳለብዎ መግለጽ
 • ለጣሱት ግዴታ መድገም እንደማይኖርብዎ ምክር
 • በተገቢ ሁኔታ ምላሽ ካልሰጡ ባለንብረቱ ለማካካሻ ገንዘብ የሚሆን እና/ወይም ህጉን ስለመጣስ ህጋዊ ትእዛዝ በ Victorian Civil and Administrative Tribunal በኩል እንዲሰጥ ባለንብረቱ ማመልከት ይችላል
 • ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ግዲታዎን ከጣሱ የ14 ቀን ከቤት ማስለቀቂያ ማስጠንቀቂያ በባለንብረቱ በኩል ሊሰጥዎ እንደሚችል ምክር መስጠትና ቀደም ሲል ስለተፈጸሙ ለሁለቱም የግዴታ መጣስ ህጋዊ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጥዎ መምከር
 • በእጅዎ መስጠት እንዳለበትና በፖስታ ከተላከ እስከሚደርስ 2 የሥራ ቀናት ጭማሪ መስጠት
 • በአንቀጽ ህግ Residential Tenancies Act 1997 መሰረት ይህን መጠቀም የሚቻለው ለግዲታ መጣስ ብቻ እንጂ ለሌላ ምክንያት መሆን የለበትም

 

በግዴታ መጣስ እና በተከራይና አከራይ ስምምነት (ኮንትራት) ውል መጣስ መካከል ልዩነት አለ። ለምሳሌ፡ የቤት እንስሳት ማስቀመጥ የርስዎን ተከራይና አከራይ ስምምነት ውል መጣስ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በአንቀጽ ህግResidential Tenancies Act 1997 መሰረት ለግዲታ ውለታን መጣስ አይደለም። ለተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ጊዜ ገደብ መጣስ ባለንብረቱ ለግዲታ ውለታ መጣስ የሚል ማስጠንቀቂያ ሊሰጥ አይችልም፤ ነገር ግን ህጋዊ ትእዛዝ እንዲሰጥ ለልዩ ፍርድ ቤቱ ማመልከት ይችላሉ።

ማካካሻ ገንዘብ እና ህጋዊ የሆነ ትእዛዝ

ባለንብረቱ የማካካሻ ገንዘብ እና/ወይም ህጋዊ ትእዛዝ ለማግኘት ለVictorian Civil and Administrative Tribunal ካመለከቱ ታዲያ ላመለከቱበት ቅጽ ቅጂውን ለርስዎ መላክ አለባቸው። ከዚያም የፍርድ ችሎቱ የሚካሄድበትን ሰዓት፣ ቀንና ቦታ በልዩ ፍርድ ቤቱ በኩል ማሳሰቢያ ይደርስዎታል። ባለንብረቱ ባቀረበው ጥያቄ ላይ ለመከራከር ከፈለጉ በልዩ ፍርድ ቤቱ ችሎት ስያሜ ላይ መቅረብ አለብዎት። በፍርድ ችሎቱ ላይ ካልሄዱ እርስዎ በሌሉበት ጉዳዩ ይታይና ባለንብረቱ በርስዎ ላይ ላቀረበው ጥያቄ ለማሸነፍ ጥሩ እድል ይከፍትለታል።

ባለንብረቱ ባቀረበው ጥያቄ እና/ወይም የማካካሻ ገንዘብ መጠን ስለመቀነስ በልዩ ፍርድ ቤቱ ችሎት ላይ ለመከራከር እድሉ ይሰጥዎታል።

በአንቀጽ ህጉ Residential Tenancies Act 1997 መሰረት እርስዎ ህጉን እንደጣሱ ባለንብረቱ ልዩ ፍርድ ቤቱ ማሳመን ስላለበት ታዲያ ላቀረቡት ጥያቄ የሚደግፍ ማስረጃ ስለሚያቀርቡ፤ እርስዎን ይህንን ለመከላከል ዝግጅት ማድረግ አለብዎት (ለምሳሌ፡ ፎቶግራፎች፣ ምስክር በአካል ወይም የምስክር ህጋዊ ጽሁፍ ማስረጃ ማምጣት)።

ለማስለቀቅ ማስጠንቀቂያ

የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ከተሰጥዎት በኋላ በ14 ቀናት ውስጥ ግዴታዎን አልተወጡም ብሎ ባለንብረቱ ካመነበት ሁለተኛ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥዎት እንደሚችል እና/ወይም ህጋዊ የሆነ ትእዛዝ ለማግኘት ወደVictorian Civil and Administrative Tribunal ማመልከት ይችላሉ። ልዩ ፍርድ ቤቱ ለባለንብረቱ የሚደግፍ ትእዛዝ ከሰጠ እና ካልተቀበሉት ባለንብረቱ የ14 ቀን ከቤት ማስለቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥዎት ይችላል።

በልዩ ፍርድ ቤቱ የተሰጠን ትእዛዝ ባለመቀበል የ Consumer Affairs Victoria ክስ መመስረት ሲችል ይህም ሁለቱንም ማለት በገንዘብም ሆነ ገንዘብ ነክ ባልሆነ ትእዛዝ ላይ ተግባራዊ ይሆናል። በሚታተምበት ጊዜ ቅጣቱ $2442.80 ዶላር በተጨማሪም ትእዛዙ ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ በየቀኑ $610.70 ዶላር፤ ከፍተኛ መጠን እስከ $7328.40 ዶላር ይሆናል።

እንዲሁም ተመሳሳይ ግዴታን ለሶስተኛ ጊዜ ከጣሱ እና ቀደም ሲል በነበሩት ሁለት የህጋዊ ግዴታን መጣስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥትዎት ከነበረ ባለንብረቱ ወደ ልዩ ፍርድ ቤቱ ሳይሄድ የ14 ቀን ማስለቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥዎት ይችላል።

ለባለንብረቱ የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት

በአንቀጽ ህግ Residential Tenancies Act 1997 መሰረት ባለንብረቱ ያለበትን ግዴታ አልተወጣም ብለው ካሰቡ እንደ ተከራይ መሆንዎ መጠን የግዴታ መጣስ ማስጠንቀቂያ ለባለንብረቱ መስጠት ይችላሉ።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች
ለማካካሻ ክፍያ ጥያቄ ስለመከራከር
የግዲታ መጣስ ማሳሰቢያ ለባለንብረትዎ ስለመስጠት
በቪክቶሪያ ሲቪልና አስተዳደር ልዩ ፍርድ ቤት

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


When you get a breach of duty notice | Amharic | September 2011

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept