ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

እባክዎ የቋንቋዎን ስም በራስዎ ፊደል ጽፎ ማስገባት

ከ ቪሲኤቲ (VCAT) ችሎት ጋር የተያያዙ ወጪዎች በ “ክፍያዎች” (fees) እና “ወጪዎች” (costs) ይከፈላሉ።

ክፍያዎች ወይስ ወጪዎች?

ክፍያዎችለቪሲኤቲ (VCAT) የሚከፍሉት መጠን ናቸው። ለዚህ ምሳሌ ለችሎት የማመልከቻክፍያ ነው። ሌሎች ክፍያዎች ለ ንብረትን ለመያዝ ማዘዣ ክፍያ ወይም ለ የፍርድ ቤት መቅረብ መጥሪያ ለመስጠትን ያካትታሉ። ወጪዎች ሌሎች ማናቸውም ወደችሎት ለመሄድ እና ጉዳይዎን ለማቅረብ የሚከፍሏቸው መጠን ናቸው።     ምሳሌዎች የመጓጓዣ ወጪዎች እና ማስረጃ ለማዘጋጀት ክፍያዎች ያከትታሉ።

የማመልከቻ ክፍያዎች

የጤና እንክብካቤ ካርድ (Health Care Card) ካለዎለዎት ወይም የመያዣ ገንዘብዎን ለማስመለስ ከሆነ የሚያመለክቱት ስለተከራዩት ቤት ጉዳይ ቪሲኤቲ ችሎት የማከልከቻ ዋጋ መክፈል ኣያስፈልግዎትም።

የማመልከቻ ክፍያው ከ 1 ጁላይ 2019ጀምሮ $65.30 ነው፣ ነገር ግን ሊቀየር ይችላል። ወቅታዊ ክፍያዎችን (ቪሲኤቲ ድረገጽ) (VCAT website)ይመልከቱ። የጤና እንክብካቤ ካርድ ከሌለዎት ወይም ክፍያውን ለመክፈል ኣቅም ከሌለዎት፣ የክፍያ ምህረት (ቪሲኤቲ ድረገጽ) (VCAT website)መጠየቅ ይችላሉ። ክፍያውን በጥሬ ገንዘብ መክፈል ከፈለጉ፣ ማመልከቻዎን ለ ቪሲኤቲ እራስዎ መውሰድ ያስፈልግዎታል።

ገንዘብዎን መልሶ ማግኘት

ኣብዛኛውን ጊዜ ለቪሲኤቲ ችሎት ሁሉም ሰው የየራሳቸውን ክፍያዎች እና ወጪዎች ይከፍላሉ። ሌላው ወገን ለእነዚህ እንዲከፍል ማድረግ የማይመስል ነው፣ ቢያሸንፉም እንኳን።

በኣንዳንድ ሁኔታዎች ቪሲኤቲ ኣንደኛው ወገን የሌላኛውን ወገን ክፍያዎች እና ወጪዎች እንዲከፍል ሊያዝ ይችላል።ቪሲኤቲ ይህንን የሚያደርገው ኣንደኛው ወገን ለሌላኛው ወገን ሸንጎውን ኣግባብየለሽ ያደረገ እንደሆነ ብቻ ነው። በዚህ የሚካተቱ ምሳሌዎች፤ ያለጥሩ ምክንያት ኣንድን ሰው ወደ ቪሲኤቲ ሸንጎ መውሰድ፣ ለሌላኛው ወገን የማስረጃ  ቅጂዎችን ያለመስጠት፣ እና ችሎቱ እንዲቀየር (እንዲተላለፍ)ማድረግ።

መጠየቅ የሚችሉዋቸው ወጪዎች

ከዚህ በፊት ቪሲኤቲ ኣከራዮች ለተከራዮች እንዲከፍሉ ያዘዛቸው ኣንዳንድ ወጪዎች እኝሁና፤

 • የመጓጓዣ ወጪዎች (ምሳ፤ የባቡር ክፍያ፣ የነዳጅ፣ የመኪና ማቆምያ ክፍያ)
 • ማስረጃ የማዘጋጃ ወጪዎች (ምሳ፤ የፎቶ ማዘጋጃ ክፍያ፣ የፎቶኮፒ)
 • በሸንጎው ለመገኘት በባከነ ጊዜ የጠፋ ገቢ
 • የጠበቃ ክፍያ

 

እንዴት እንደሚጠይቁ

ኣከራዩ የርስዎን ክፍያዎች እና ወጪዎች መክፈል ኣለበት ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ኣከራዩ እንዲከፍልቪሲኤቲው ትእዛዝ እንዲሰጥ መጠየቅ ኣለብዎት። ይህንን በማመልከቻዎ ቅጽ ላይ መጠየቅ የተሻለ ነው (ቪሲኤቱው እንዲያደርግ የሚፈልፈልጉዋቸው ትእዛዛት በሚለው ክፍል ላይ)። ካልሆነም በሸንጎው ወቅት መጠየቅ ይችላሉ። እንዲሁም የህጉን ክፍል በቅጹ ላይ ይጻፉ ወይም ይህንን ትእዛዝ ሲጠይቁ በችሎቱ ወቅት ሊጠቅሱት ይገባል። ኣከራይዎ ወጪዎችዎን እንዲከፍል የፈለጉ እንደሆነ፣ ክፍል 109፣ ቪሲኤቲ ደንብ (VCAT Act)፣ ይጻፉ። ኣከራይዎ  ክፍያዎችዎን እንዲከፍል የፈለጉ እንደሆነ፣ ክፍል 115B ቪሲኤቲ ደንብ (VCAT Act)ይጻፉ።

የሚያስፈልግዎት

ጥያቄዎን ለማገዝ፣ እርስዎ፤

 • ወደሸንጎው ለመሄድ ያወጡትን (ወይም ያጡትን)መጠን የሚያሳይ (ለምሳሌ፤ ከደሞዝዎ ያጡትን መጠን የሚገልጽ ደብዳቤ ከኣሰሪዎ፤ የባቡር/ትራም/ኣውቶቡስ ክፍያ፣ የመኪና ማቆምያ፣የፎቶኮፒ ደረሰኞች ወዘተ) ማስረጃ ይኑርዎት
 • ማንኛውም ምክንያቶች እርስዎተገቢ ናቸው የሚሉዋቸው ኣከራዩ ወጪዎችዎን ሊከፍል ይገባል የሚሉበትን ይጠቁሙ (ለምሳሌ፤ ለሸንጎው ምንም ጥሩ የሆነ ምክንያት የለም፣ ወይም ሸንጎው እንዲተላለፍ ኣድርገዎል)
 • ኣከራይዎ እንዴትኣላስፈላጊ መዘግየት እንዳስከተለ ይጠቁሙ (ለምሳሌ፤ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት የነሱን ጥያቄ ግልባጭ እንዳልሰጡዎት እናም ችሎቱ ማተላለፍ እንዳልፈለገው)
 • ኣከራይዎ በችሎቱ እንዴት እንደጎዳዎ ይጠቁሙ (ለምሳሌ፤ የነሱን ማስረጃ ቅጂዎች እስከ ችሎቱ እለት ድረስ እንዳልሰጡዎት እናም ምላሽዎን ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ እንዳልነበርዎት)
 • ኣከራይዎ  እንዴት እርስዎን ወይም ቪሴኤቲን ሊያታል እንደሞከረይጠቁሙ።

ኣከራዩ የጠየቀ እንደሆነ

ኣከራዩ እርስዎ ክፍያዎቹን እና ወጪዎቹን እንዲከፍሉት ቪሲኤቲን ትእዛዝ የጠየቀ  እንደሆነ እናም እርስዎ ተገቢ ኣይደለም ብለው ካሰቡ፣ ሊያስረዱ ይችላሉ፤

 • እርስዎ የኣከራዩን ክፍያዎች እና ወጪዎች መክፈል ተገቢኣይደለም ብለው ለምን እንደሚያስቡ
 • እርስዎ ለምን የተጠየቀው መጠን ኣግባባነት የሌለው መጠን ነው ብለው እንደሚያስቡ
 • እንዴት ኣከራዩ ኣላስፈላጊ መዘግየት በችሎቱ ላይ እንዳደረሰ
 • እንዴት ኣከራዩ እርስዎን እንደጎዳዎ
 • እንዴት ኣከራዩ እርስዎን ወይም ቪሲኤቲን ለማታለልእንደሞከረ።

 

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የታተመ; ነሐሴ 2016

Fees and costs for a VCAT hearing | Amharic | August 2016


Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept