ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ህጋዊ ባልሆነ ወይም ሙያ በጎደለው መልኩ ሥራ አካሂዷል ብለው ካሰቡ ህጋዊ የሆነ ቅሬታ ለማካሄድ ግምት ውስጥ ማስገባት አለብዎ።

ይህ ገጽ

ህጉ ምን እንደሚል
በባለንብረቶችና በተወካዮች ህግ መጣስ ወንጀል
እንዴት ቅሬታ እንደሚቀርብ
በጽሁፍ አድርጎ ቅሬታን ስለማቅረብ
የቅሬታ/ክስ ናሙና ደብዳቤ
ቅሬታዎን ለማቅረብ የሚችሉበት ሌላ ቦታ የት ነው?

ህጉ ምን እንደሚል

በቪክቶሪያ ውስጥ ለተከራዮችና ለባለንብረቶች ስለሚኖሩ መብቶችና ግዴታዎች በ Residential Tenancies Act 1997 ዝርዝሩ ተገልጿል። በአንቀጽ ህጉ መሰረት ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ወንጀል ከፈጸመ በቪክቶሪያ ደንበኛ ጉዳይ በኩል ተደርጎ በወረዳ ፍርድ ቤት ሊከሰሱ ይችላሉ፡ እንዲሁም ጥፋተኛ ሁነው ከተገኙ ሊቀጡ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ቅሬታ ለማቅረብና የደንበኛ ጉዳይ ደግሞ ክስ እንዲመሰርት መጠየቁ የርስዎ ሀላፊነት ነው።

ክስ ለመመስረት የሚወስደው ጊዜ ገደብ፤ ወንጀሉ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ12 ወራት ወይም 3 ዓመት ውስጥ ባለው ጊዜ ይሆናል (የጊዜ ገደቡ እንደ ወንጀሉ ይለያያል)። ስለዚህ ወዲያውኑ እርምጃ እንዲወስዱ እናሳስባለን።

በባለንብረቶችና በተወካዮች ህግ መጣስ ወንጀል

ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ስለሚከተሉት ያካተተ የተከራይና አከራይ ውል ሲጀምር አስፈላጊ የሆኑትን ሰነዶች ካልሰጥዎ ወንጀል ፈጽሟል ማለት ነው:
[list type=”square_list”]

 • የመብቶችንና ግዴታዎችን ጽሁፋዊ መግለጫ (ከ Consumer Affairs Victoria ትንሽ መጽሐፍ)
 • የርስዎን የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል የተፈረመበትን ቅጂ
 • የተፈረመበትን ንብረት መግለጫ ሪፖርት 2 ቅጂዎች(የማስያዣ ገንዘብ ተከፍሎ ከሆነ)
 • የባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ተለፎንና የፋክስ ቁጥሮች
 • ከሥራ ሰዓታት ውጭ ለአስቸኳይ ጥገና የሚጠቅም ለድንገተኛ ችግር መጥሪያ ቁጥር
 • የንብረት ተወካይ ከተጠቀሙ ለአስቸኳይ ጥገና ለማካሄድ ስልጣን ማግኘት አለማግኘት ጽሁፋዊ መግለጫ (አስቸኳይ ጥገና ለማካሄድ ስልጣን ከሰጡም የሚፈቀድላቸው ከፍተኛ ወጪና የነሱን ስልክ ቁጥር ወይም ፋክስ ቁጥር)

[/list]

ሊካተቱ የሚችሉ ሌላ ወንጀሎች:
[list type=”square_list”]

 • ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ከቤት ለማስወጣት መሞከር (ይህም ፖሊስ ያለ ህጋዊ ማዘዣ ሳይዝ)
 • የቤት ኪራይ ለከፈሉበት ደረሰኝ አለመስጠት
 • የቤት ኪራይ ውዝፍ እዳ ስላለብዎ በሚል ሳቢያ ማንኛውንም እቃዎን መያዝና መሸጥ
 • የርስዎን ማስያዣ ገንዘብ እንደከፈሉ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ Residential Tenancies Bond Authority ካላስገቡት
 • ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ለማይፈቀድለት ነገሮች ለማስከፈል መሞከር (ለምሳሌ፡ ንብረት ፍተሻ፣ የተከራይና አከራይ ውል፤ የመጀመሪያ የቤት ኪራይ የተከፈለበት ካርድ ወይም በቀጥታ ካለዎት ተቀማጭ ገንዘብ ለመጠቀም ማቀናጀት)
 • ተገቢ የሆነ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጡና ለመግባት ቅድመ ሁኔታን ሳያሟሉ ወይም በቂ ምክንያት ሳይኖር ወደ ተከራዩበት ቤት መግባት
 • በVictorian Civil and Administrative Tribunal የቀረበውን ትእዛዝ አለመከተል

[/list]

በባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ስለ ህግ መጣስ ወንጀል የበለጠ መረጃ ለማግኘት የ Tenants Union/Tenants Victoria ማነጋገር።

እንዴት ቅሬታ እንደሚቀርብ

የንብረት ተወካይ መፍትሄ አገልግሎት

በቪክቶሪያ ውስጥ ስለ ንብረት ተወካዮች/ real estate agents ክሶች/ቅሬታዎች በተዛመደ የ Consumer Affairs Victoria’s Estate Agent Resolution Service (EARS) ድርድር ያካሂዳል። ይህ አገልግሎት የተመሰረተው ደንበኞችን ለመርዳት ሲሆን ይህም ከተወካዩ ጋር ክርክር ያላቸውን ተከራዮች ያካትታል።
ለ EARS በስልክ 1800 500 509 ማነጋገር ይችላሉ።

በ EARS በኩል መረጃ፣ ምክርና ለክርክር መፍትሄ ማቅረብ ይችላል። ወደ ስምምነት መድረስ ካልተቻለ፣ EARS ክርክሩን ወደ Compliance and Enforcement at Consumer Affairs Victoria ይመራው ይሆናል።

በጽሁፍ አድርጎ ቅሬታን ስለማቅረብ

ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ወንጀል ፈጽሟል ብለው ካመኑበት ለቪክቶሪያ የደንበኛ ጉዳይ ቢሮ መጻፍ ይችላሉ (በዚህ ወረቀት ጀርባ ላይ ናሙና ደብዳቤን ማየት)። ጠቃሚ ለሆኑ ማንኛውም ሰነዶች ቅጂውን ከማያያዝ አለመርሳት። እንዲሁም በጽሁፍ አድርጎ ቅሬታን በመስመር ላይ በድረገጽ www.consumer.vic.gov.au በኩል ማስገባት ይችላሉ።

የርስዎ ደብዳቤ እንደደረሳቸው በሁለት ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ የደንበኛ ጉዳይ ደብዳቤ መልሰው ለርስዎ መላክ አለባቸው። ጉዳዩን አናጣራም ብለው ከነገርዎትና እርስዎም በበለጠ አንዳንድ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ የተከራይ ማሕበርን ያነጋግሩ። ጉዳዩን ለማጣራት ከወሰኑ ህጋዊ የሆነ ጽሁፋዊ መግለጫ ስለማግኘት ያነጋግሩዎታል።

የደንበኛ ጉዳይ ክስ ለመመስረት ከወሰነ እርስዎ እንደ ምስክር ሆነው ወደ ፍርድ ቤቱ መሄድ እንዳለብዎና በችሎት ላይ ቀርበው ማስረጃ ይሰጣሉ።

የቅሬታ/ክስ ናሙና ደብዳቤ

ከዚህ የሚከተለው ለቪክቶሪያ ደንበኛ ጉዳይ የሚቀርብ የቅሬታ ናሙና ደብዳቤ ነው።

Consumer Affairs Victoria
GPO Box 123
Melbourne VIC 3001

(የርስዎ ስም)

(የርስዎ ወቅታዊ አድራሻ)

(ቀን)

ክቡር ጌታየ ወይም እመቤት,

ስለ (lባለንብረቱ/የንብረት ተወካዩ) የቀረበ ቅሬታ

ባለንብረቱ: (ወንጀል የፈጸመ ባለንብረት (ካለ) ስምና አድራሻ)

የንብረት ተወካይ (ወንጀል የፈጸመ ንብረት ተወካይ (ካለ) ስምና አድራሻ)

ንብረት (የሚከራየው ቤት አድራሻ)

ከዚህ በላይ ባለው ንብረት ላይ እንደ (ተከራይ/የበፊት ተከራይ) መጠን ስለተፈጸመ ድርጊት (በባለንብረቱ እና/ ወይም ንብረት ተወካይ) ቅሬታ/ክስ ማስገባት እፈልጋለሁ። የ Residential Tenancies Act 1997 ደንብ እንደተጣሰ አምናለሁ (አንቀጽ ህጉን ካወቁት የክፍል ቁጥሩን መመዝገብ)።

(የተፈጸመውን ድርጊትና ለርስዎ ወደ ክስ የመራዎትን መግለጽ ይህም ስሞች፣ አድራሻዎች፣ ሰዓታት፣ ቀናት ወዘተ. ያካተተ)

እባክዎ ከዚህ ጋር የተያያዘ ስለሚከተሉት ሰነዶች ቅጂ ይድረስዎ (ከደብዳቤዎ ጋር የተያያዘን ማንኛውም ጠቃሚ ሰነዶች መመዝገብ).

ይህን ጉዳይ በሚገባ አጣርተው በወንጀል ክስ እንዲታይ እጠይቃለሁ። ፈጥነው ምላሽ እንደሚሰጡኝ እጠብቃለሁ። ከዚህ በበለጠ መረጃ ካስፈለግዎ እባክዎ (አሁን ባለዎ ተለፎን ቁጥር አድርገው) ያነጋግሩኝ።

የርስዎ ታማኝ

(የርስዎ ፊርማ)

ቅሬታዎን ለማቅረብ የሚችሉበት ሌላ ቦታ የት ነው?

ወደ EARS ከመደወልዎ እና/ወይም ወደ Consumer Affairs Victoria ከመጻፍዎ በተጨማሪ ስለባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ቅሬታዎን ወደሚከተለው ለማቅረብ መብትዎ ይሆናል:
[list type=”square_list”]

 • Victorian Equal Opportunity & Human Rights Commission of Victoria 1300 292 153 (ለማበሳጨት ወይም አድልዎ መፍጠር)
 • Federal Privacy Commissioner 1300 363 992 (ሚስጢራዊ የሆኑ መረጃዎችን አላግባብ በመጠቀም)
 • ለቪክቶሪያ ፖሊስ (ለወንጀል ድርጊት ወይም ባህሪ)

[/list]

[box type=”warning”] ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም። [/box]

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

ለብቻነት

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Complaints about landlords and real estate agents | Amharic | September 2011

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept