ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የመያዣ ገንዘብ ክፍያዎችን እና የክፍያዎቹ ኣመላለስ

የመያዣ ገንዘብ ኣብዛኛውን ጊዜ በኪራይ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ለ ኣከራይ ወይም ለነሱንብረት ወኪል የሚከፈል የገንዘብ መጠን ነው። ይህ በ የኪራይ መያዣ ባለስልጣን   Residential Tenancies የውል ባለስልጣን , የሚያዝ ሲሆን አሁንም በእርስዎ ገንዘብ ነው እና የ ኣከራይ ወይም ወኪሉ አይደለም ማለት ነው.

በኪራዩ  ወቅት መጨረሻ ኣከራዩ የመያዣውን ገንዘብ በጥቂቱ ወይም በሙሉ በቤቱ ለደረሰ ብልሽት፣ ለማፅጃ ወይም ላልተከፈለ ኪራይ ማካካሻ ሊጠይቅ ሊሞክር ይችላል።

 ውል መያዣዎን መልሰው ለማግኘት ምርጥ ጠቃሚ ፍንጮች

ፎቶዎች፣ የውል መያዣዎን መልሰው ሲያገኙ ኣለምስማማትን ለመከላከል የኪራዩ ቤት ምን እንደሚመስል የሚያሳዩ ፎቶዎች ሲገቡና ለቀው ሲዎጡ ያንሱ።

የሁኔታ ሪፖርት፣ የሁኔታ ረፖርቱን በኪራዩ ወቅት መጀመርያና መጨረሻ ላይ በጥንቃቄ  መሙላት የኪራይ መያዣዎን ማግኘት ወይም በሙሉ ወይም በከፊል የማጣት ልዩነት ሊሆን ይችላል።

ያለቀ እና የተቀደደ፣ ተከራዮች በኣግባቡ ለደረሰ ማለቅ እና መቀደድ ሃላፊ ኣይደሉም። በተለመደው ሁኔታ ለተጠቀሙበት ነገር ምክንያቶች ሊከፍሉ ኣይገባም፣ እንደ የፀሃይብርሃን የመጋረጃ መደብዘዝ ወይም በላያቸው ላይ በመረማመድ የተነሳ የምንጣፎች ማለቅ ያሉ።

ሙሉ ክፍያ  ወይስ ግማሽ ክፍያ? ተከራዮች ያረጁ፣ የተጎዱ እቃዎችን በኣዲስ እቃዎች የመተክያ ሙሉ ዋጋ ሁልጊዜ  ሃላፊ ኣይደሉም፣ ጉዳቱን በከፊሉ ቢያደርሱም እንኳን። ለምሳሌ፣ እርስዎ  የተዉትን ብልሽት ከምንጣፉ ላይ የማንሻ ዋጋን ሊሸፍኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ለኣዲስ ምንጣፍ ለመክፈል ላይኖርብዎ  ይችላል።

ማስረጃ፣ ባጠቃላይ ለውል መያዣ የከፈሉት ገንዘብ ለምን ሊመላስልዎት እንደማይገባ  ማስረጃ  ማቅረብ የኣከራይዎ  ሃላፊነት ነው።  ስለጉዳቱ ለምን እርስዎ ሃላፊ እንዳልሆኑ የሚያሳይ የራስዎ ማስረጃ  ቢኖርዎ  ደግሞ  የርስዎ ኣቋም የበለጠ የጠነከረ ይሆናል።
ውለታ: የ ቼክኣውት እና ሬድፈርን (Checkout and  Redfern) የህግ ማዕከል ተከራዮች ተሟጋች (Advocate) ቶም ማክዶናልድ (5 ጁን 2014 ታተመ)

የእርስዎን የመያዣ ውል መክፈል

የመኖርያ  ቤቶች ኣለቃ (Director of Housing) (ዲኦኤች) በ የውል መያዣዎን የሚከፍል ከሆነ  የውል ብድር እቅድ (Bond Loan Scheme) ስር , አንድ የተጠናቀቀ ዲኦኤች የውል መመዝገብያ ቅጽ (Bond Lodgement form) መፈረም ያስፈልግዎታል. ዲኦኤች የ ውል መያዣዎን በከፊል የሚከፍል ከሆነ, እነሱ የከፈሉትን መጠን አንድ ዲኦኤች የውል መመዝገቢያ ቅጽ (Bond Lodgement form), እንዲሁም ለተቀረው ገንዘብ የውል ባለስልጣን (Bond Authority) የውል መመዝገቢያ ቅጽ (Bond Lodgement form) መጠቀም አለቦት።

ኣከራዩ  ወይም ወኪሉ የ ቅጽ / ዎችን ቅጂ ለርስዎ መስጠት አለባቸው፣ እርስዎም የውል መያዣውን ለመክፈሎ ማረጋገጫ ሊይዙት ይገባል።

እርስዎ የውል መያዣ የሚከፍሉ ከሆነ፣ ኣከራዩ ወይም ወኪሉ በ ኣከራዩ የተፈረመ 2 ቅጂ የሁኔታ ሪፖርት (Condition Report) መስጠት አለባቸው.

ኣከራዩ ወይም ወኪሉ የርስዎን የውል መያዣ ገንዘብ መመዝገብ እና እንዲሁም የውል መመዝገብያ ቅጽ/ዎች (Bond Lodgement form) በ የውል ባለስልጣን ጋር እርስዎ ከከፈሉ በ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።  ኣከራዩ ወይም ወኪሉ የ ውል መያዣዎን እንደመዘገቡ ከ የውል ባለስልጣን ማረጋገጫ ማግኘት አለብዎት። እርስዎ በ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ደረሰኝ ያላገኙ ከሆነ፣  በስልክ ☎ 1300 137 164
(በአካባቢ ጥሪ ሂሳብ) ላይ የውል ባለስልጣን ማነጋገር አለብዎት።

የ ውል መያዣዎ ያልተመዘገበ ከሆነ ወንጀል ነው. እርስዎ ለ ተጠቃሚ ጉዳዮች ቪክቶሪያ (Consumer Affairs Victoria) ይህን ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፣ እና ደግሞ እርስዎ ኣከራይዎ የ ውል መያዣዎን እንዲመዘግብ የሚጠይቅ  ትእዛዝ ለ ቪሲኤቲ ማመልከት ይችላሉ.

ባጠቃላይ፣ የኪራዩን ወል እስኪፈርሙ ድረስ የገንዘብ መያዣውን ኣለመክፈል የሚመረጥ ልምምድ ነው። ሁል ጊዜ የገንዘብ መያዣውን ሲከፍሉ ማስረጃ ማግኘቶን ያረጋግጡ፣ በተለይ በጥሬ ገንዘብ ከከፈሉ።

የእርስዎን ውል መያዣ ማስተላለፍ

ከክራዩ ቦታ ከወጡና ኣከራዩ ወይም ሌሎች ተከራዮች ሌላ ሰው የርስዎን ክራይ እንዲወስድ ከተስማሙ፣ ለ የገንዘብ መያዣ ባለስልጣን(Bond Authority) በ 5 ቀናት ውስጥ የገንዘብ መያዣው ወለድዎ ለኣዲስ ተከራይ እንደተላለፈ ማሳወቅ ኣለቦት። የተከራይ ማስተላለፍ(Tenant  Transfer) ቅፅ በመሙላት(ይህም በ እርስዎ፣ ሌሎች ተከራዮች (ካሉ)፣ ኣዲሱ ተከራይ እና ኣከራዩ  ወይም ወኪሉ መፈረም ኣለበት)እና ለ የውል ገንዘብ መያዣ ባለስልጣን(Bond Authority) በመላክ ይህንን ሊያደርጉ ይችላሉ። የውል ገንዘብ መያዣ ባለስልጣኑ(Bond Authority) የኪራዩ ጊዜ እስከሚያልቅ ድረስ የ ውል መያዣ ገንዘቡን ኣይለቅም ስላዚህም ክፍያውን ከ አዲሱ ተከራይ ለማግኘት ማመቻቸት የእርስዎ  ሃላፊነት ነው። የ ተከራይ የዝውውር ቅጽ ከመፈረምዎ በፊት ክፍያውን ከመጭው ተከራይ መቀበል  ይገባዎታል።

የኪራይ ጊዜ ሲያበቃ

እርስዎ የ ውል መያዣዎን ለሌላ ሰው ካላስተላለፉ፣ የኪራይ ወቅት እስከሚጠናቀቅ ድረስ መያዣው በየውል ባለስልጣን (Bond Authority)ይያዛል፣ከዚያም የለለያዩ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ:

  • ከ ኣከራይዎ ጋር ከየ ውል መያዣ ላይ ምን ያህልእንደሚከፈላቸው ስምምነት ያደርጋሉ
  •  እርስዎ ኣከራይዎ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ እናም እነሱ ከ የ ውል መያዣው ላይ ጥቂት ወይም ሁሉንም እንዲከፈላቸው ትእዛዝ ለ የቪክቶሪያ ሲቪል እና ማስተዳደርያ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከት ይችላሉ
  • የ ውል መያዣዎ እንዲመለስለዎ ለልዩ ፍርድ ቤቱ (Tribunal) ያመለክታሉ

 

የርስዎ ኣከራይ ምንም መጠየቅ ኣይችልም

የእርስዎ ኣከራይ የ ውል መያዣዎን ላለመጠየቅ ከተስማማ፣ እርስዎ እና ኣከራዩ የ ውል መያዣ ገንዘቡ ለርስዎ እንዲመለስ ማመልከት ይገባችኋል። እርስዎ፣ ሌሎች ተከራዮች (ካለ) እና ኣከራይ ወይም ወኪል አንድ የመያዣ መጠየቅያ ቅጽ (Bond Claim form) መፈረም አለባችሁ፣ እንዲሁም በቅፁላይ ገንዘቡ እንዲገባ የሚፈልጉትን የባንክ ሂሳብ ዝርዝር ማቅረብ አለቦት። ኣንዴ ቅፁ  በ የውል ባለስልጣን (Bond Authority)ዘንድ ከተመዘገበ፣ የእርስዎ የ ውል መያዣ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ በተጠቀሰው የባንክ ሂሳብ ውስጥ መከፈል አለበት።

ኣከራይዎ ለርስዎ  ያልተሟላ የመያዣ መጠየቅያ ቅጽ (Bond Claim form) እንዲፈርሙ መስጠት  ወንጀል ነው። የ ውል መያዣው ሙሉውን ለእርስዎ መከፈል ያለበት ከሆነ፣ የ ውል መያዣው ሙሉ መጠን ‘ተከራይ የክፍያ ዝርዝር’ ክፍል ውስጥ መመዝገቡብ ያረጋግጡ። አንድ ቅጂ ማስቀመጥዎን እርግጠኛ ይሁኑ.

የርስዎ የ ውል መያዣ በ የመያዣ የብድር እቅድ (Bond Loan Scheme) መሰረት በ የቤቶች ጉዳይ ሃላፊ (Director of Housing)  የተከፈለ ከነበረ እና ኣከራይ በእርሱ ላይ ማንኛውም ማወጅ ካላደረገ፣ እርስዎ እና አከራይዎ ወይም ወኪሉ አንድ የመያዣ መጠየቅያ ቅጽ (Bond Claim form) መሙላት አለብዎት እና የ ውል መያዣ ገንዘብ ወደ የቤቶች ቢሮ (Office of Housing) በቀጥታ ተመልሶ ይከፈላል።

በእርስዎ ከኣከራይዎ ጋር ይስማማሉ

እርስዎ ኣከራይ ከ የ የ ውል መያዣ ገንዘቡ ጥቂት ወይም ሁሉም ይገባዋል ብለው ከተስማሙ፣ ያ መጠን እንዲከፈለው መስማማት ይችላሉ። እርስዎ፣ ሌሎች ተከራዮች (ካለ) እና ኣከራይ ለ ኣከራዩ   ከ የ ውል መያዣ ውስት ምን ያህል እንደሚከፈለው እና ለርስዎ ምን ያህል እንደሚክፈል በመግለፅ የመያዣ መጠየቅያ ቅጽ (Bond Claim form) መሙላት አለባችሁ።

 የ ውል መያዣው በእርስዎእና በኣከራይ መካከል የሚከፋፈል ከሆነ፣ ትክክለኛውን መጠን በ   የ ‘ተከራይ የክፍያ ዝርዝር’ ክፍል እና የሚመለከት ከሆነም ለ ኣከራይ / ወኪል የሚከፈለው ጠቅላላ መጠን ‘ውስጥ ተገቢውን መጠን መጻፍዎን እርግጠኛ ይሁኑ። የነዚህ መጠኖች ድምር ከ የ ውል መያዣ ጠቅላላ መጠን ጋር  ልክ መሆናቸውን ያረጋግጡ።

ተውል የመያዣ መጠየቅያ ቅጽ (Bond Claim form) ከ የኪራይ ወቅት የመጨረሻ ሳምንት በፊት ሊጠናቀቅ ይገባል።  ቅፁ ላይ የተፃፈው ቀን ​ የኪራይ ወቅት ከመጠናቀቁ ከ 7 ቀናት ላይ ከሆነ፣  የ የውል ባለስልጣኑ (Bond Authority) ኣይቀበለውም። የእርስዎ የ ውል መያዣ በ የመያዣ የብድር እቅድ (Bond Loan Scheme) መሰረት የቤቶች ቢሮ (Office of Housing) በኩል የሚከፈል ከሆነ፣ እርስዎ ከሱ ላእ የተወሰነ ለኣከራዩ  እንዲከፈል ስምምነትለማድረግ አይችሉም። ኣከራዩ ወይም ወኪሉ  የ ውል መያዣውን በሙሉ ወይም በከፊል  ለመቀበል  ትእዛዝ  ለልዩ ፍርድ ቤቱ ማመልከት ይኖርባቸዋል። ፍርድ ቤቱ ማንኛቅም በ የመያዣ ብድር እቅድ (Bona Loan Scheme) መሰረት በተመለከ ያደረጉትን የውል መያዣ ክፍያ ውሳኔ ለ የቤቶች ቢሮ ያሳውቃሉ።

የእርስዎ ኣከራይ የእርስዎን ውል ለመውሰድ ያመለክታል

የ ውል መያዣ ገንዘቡ የርስዎ ነው ተብሎ ነውየሚታሰበው፣ ኣከራይዎ ከየውል መያዣ ከገንዘቡ ሙሉውን ይሁን ጥቂቱን ማወጅ የፈለገ  ከሆነና  እርስዎ ካልተስማሙ፣ ወደ የቪክቶሪያ ሲቪል እና ማስተዳደርያ ፍርድ ቤት (Victorian Civil and Administrative Tribunal) ማመልከት ይኖርባቸዋል። ኣከራዩ ለፍርድቤቱ ያወጀው ምክንያታዊ እና ተገቢ ነው ማሳመን የርሱ ኃላፊነት ነው። ኣከራዩ  ወይም ወኪሉ የይገባኛል ጥያቄያቸውን የርስዎ  የኪራይ ወቅት ባበቃ  በ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ማድረግ ይገባቸዋል። ኣከራዩም ሆነ ወኪሉ ለእርስዎ ወደፊት የሚልኩበት ኣድራሻ እንዲኖራቸው ኣስፈላጊ ነው። ይህንን ካላደረጉ፣ ኣከራዩ እና ፍርድ ቤቱ ማስታወቂያዎች እና ሰነዶችን ኣስቀድመው ተከራይተውት ወደ ነበረ ቤት ይልኩ ይሆናል። ኣከራይ ወይም ወኪሉ ወደፊት የሚልኩበት ኣድራሻ ካላቸው እርስዎ የማመልከቻቸው ቅጂ ሊላክልዎ  ይገባል፣ ፍርድ ቤቱም የገንዘብ መያዣዎን እወጃ ለመከላከል ሸንጎው የት እና መቼ እንደሆነ ይልክልዎታል የቀጠሮ ማስታወቂያ ። እርስዎ መገኘት ኣለቦት ያለበለዚያ ኣከራይዎ ቅዋሜ የሌለው ማስረጃ  ኣቅርቦ  የጠየቁትን ሁሉ ሊያገኙ ይችላሉ ምክንያቱም ትእዛዛት ያለርስዎ  መገኘት ሊደረጉ ይችላሉና።

የ ውል መያዣዎ እንዲመለስለዎ ለልዩ ፍርድ ቤቱ (Tribunal) ማመልከት

የ ውል መያዣ ማመልከት ነፃ ነው እንዲሁም በልዩ  ፍርድቤቱ ችሎት በሚቀርቡበት ወቅት ምንም የህጋዊ ክፍያ ስጋት የለም በእርስዎ ኣከራይ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ካለቻሉ፣  ወይም ኣከራዩ  በቀላሉ በጣም ረጅም ጊዜ እየወሰደ ከሆነ፣ ከወጡ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ለፍርድ ቤቱ ማመልከት ይችላሉ። እርስዎ  ማድረግ ያለብዎት ነገር የውል መያዣ ገንዘብዎ እንዲመለስለዎ ጠቅላላ የ ቪሲኤቲ ማመልከቻ በመሙላት መጠየቅ እና ከውል መያዣ ከደረሰኙ ጋር ማያያዝ ነው።

በተጨማሪም ተከራዮች የውል መያዣ ጥያቄ ባቀረቡበት ጊዜ የካሳ ጥያቄም ማድረግ ይችላሉ።

በልዩ ፍርድ ቤት ችሎት

ለፍርድ ቤቱ ያመለከተው እርስዎም ይሁኑ ኣከራዩ፣ የሚከተለውን መረጃ በቀጠሮው ይዘው መሄድ ኣለብዎ፤

  • የተከፈለው የ ውል መያዣ መጠን
  •   የኪራይ ወቅት ለማቆም የተሰጠ ማስታወቂያ መጠን፣  በርስዎ ወይም ኣከራይ

 

ኣከራይ የ የ ውል መያዣ ላይ እወጃ የሚያደርግ ከሆነ፥ እነሱ የማመለከቻውንቅጽ ቅጂ እና ለመጠቀም የሚፈልጉትን ማንኛውንም ማስረጃ ሊሰጥዎ ይገባል። እነርሱይህንን ከየፍርድቤት ጉዳይ ቀን በፊት ለርስዎ መስጠት አለባቸው። እርስዎ ይህንን ወደ የፍርድቤት ጉዳይ ይዘውት ሊሄዱ ይገባል።

የ ውል መያዣዎ በ የመያዣ የብድር እቅድ (Bond Loan Scheme) መሰረት የተከፈለ ከነበረ እናም ኣከራዩ በሱ ላይ ጠያቄው የተሳካለት ከሆነ፣ እርስዎ አሁንም ቢሆን ለየቤቶች ጉዳይ ሃላፊ (Director of Housing) የ ውል መያዣ ብድሩን መክፈል ይኖርብዎታል። ለ የቤቶች ጉዳይ ሃላፊ (Director of Housing)  ያልተከፈለ ዕዳ ማንኛውም ለወደፊት የህዝብ መኖሪያ ቤት ወይም የ ውል መያዣ ብድር ለማግኘት መሚያደርጉት ማመልከቻዎች ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል።

በልዩ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከወሰነ በኋላ፣ ትእዛዝ (Order) ተብሎ የሚጠራው ውሳኔ ግልባጭ ይሰጥዎታል። ከዚያም እርስዎ ያለ ኣከራይ ወይም ወኪሎች ፊርማ የመያዣ መጠየቅያ ቅጽ (Bond Claim form) መሙላት ይችላሉ። እርስዎ የፍርድቤቱን ትእዛዝ (Tribunal Order) ከ የውል መያዣ መጠየቅያ ቅፅ (bond Claim form) ጋር ያያይዙና በ የውል ባለስልጣኑ (Bond Authority) ያስመዘግባሉ። ገንዘቡ በ ትእዛዙ መመርያ መሰረት ይለቀቃል። ከአንድ በላይ ተከራይ (ለምሳሌ ደባል ቤት ውስጥ) በ የ ውል መያዣ ደረሰኝ ላይ ከተጠቅሰ እርስዎ እና ሌሎቹ ተከራዮች ለያንዳንዱ ሰው የውል መያዣው እንዴት እንደሚከፈል መስማማት ይኖርባችኋል።.

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የታተመ: ሜይ2017

Bond payments and refunds | Amharic | May 2017


Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept