ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

የግል መኖሪያ ቤት ኪራይ ስለማመልከት

ለመኖሪያ ቤት ኪራይ ሲያፈላልጉ፤ ለሚቀጥለው ቤትዎ ሲፈላልጉና ከዚያ በፊት ግምት ውስጥ ማስገባት ያለብዎ የተለያዩ ነገሮች አሉ።

ይህ ገጽ

ስለ የቤት ኪራይ ወጪ
የት እንደሚፈለግ
ለንብረት ፍተሻ ስለማቀናጀት
የሚከራይ መኖሪያ ቤት ፍተሻ
የኪራይ ቤት ስለማመልከት
የብድር እዳ መረጃ ፍተሻ
ስለተከራይ የተቀመጠ መረጃ
ያቀረቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ካገኘ
ለመገልገያ አገልግሎቶች ማስቀጠል

ስለ የቤት ኪራይ ወጪ

የሚከራይ ቤት ከመፈለግዎ በፊት የገንዘብ ባጀት ማዘጋጀት። በነዚህ ወጪዎች የሚካተቱት:

 • ማስያዣ ገንዘብ
 • በቅድሚያ የቤት ኪራይ
 • ለጋዝ፣ ኤሌትሪክ፣ ተለፎን ማስቀጠያ ክፍያ
 • ለእቃ ማጓጓዣ ወጪ
 • የቤት እቃና ለቤተሰቡ መገልገያ እቃዎች

 

የገንዘብ እርዳታ ማግኘት ስለመቻልዎ ለሚከተሉት ማጣራት:

 • Rent Assistance (ለበለጠ መረጃ Centrelink ማነጋገር)
 • የቅድሚያ ኪራይ ክፍያ (የአካባቢዎን መንግሥት የመኖሪያ ቤት አገልግሎት ማነጋገርና ስለ Housing Establishment Fund ወይም HEF) መጠየቅ
 • ለማስያዣ ገንዘብ ብድር (ተጨማሪ መረጃ ከአካባቢዎ Housing Office ስለ Bond Loan Scheme ማግኘት ይችላሉ)

 

በተከታታይ የሚከፈል ወጪ ማለት የቤት ኪራይ፣ የፍጆታ ክፍያ እና ለቤት እቃ ተስማሚ ዋስትና ኢንሹራንስን ያካትታል። እንዲሁም ሁልጊዜ የሚጓዙበትን ወጪም ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልግ ይሆናል። ወደ ሥራዎ፣ ትምህርት ቤት ወይም ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ቦታ/ቤት ካላገኙ ወይም ለመከራየት አቅም ከሌለዎት፤ ታዲያ ለመጓጓዣ የሚሆን የገንዘብ በጀት መመደብ ይኖርብዎታል።

ከተቻለ ለቤት ኪራይ የሚያወጡት ከሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ መጠን ላይ ከመቶ 25 እጅ መብለጥ የለበትም።

የት እንደሚፈለግ

የመኖሪያ ቤት ማየት የሚችሉበት ብዛት ያላቸው ቦታዎች እንዳሉና በንብረት አከራይ ድርጅቶች በኩል የሚከራዩ ቤቶች ዝርዝር ይቀርባል።

ለመጀመር ጥሩ ቦታዎች:

 • በንብረት አከራይ ድርጅቶች የሚከራዩ ቤቶችን ዝርዝር ያቀርባሉ
 • በኢንተርኔት (በንብረት አከራይ ኩባንያ ድረገጾች እና በመኖሪያ ቤት ማፈላለጊያ ድረገጾች ላይ እንደ domain.com.au እና realestate.com.au) ባሉ

 

የግል ቤት አከራዮች ወይም በጋራ የሚኖሩባቸው ቤቶች አማካኝነት ብዙ ጊዜ ማስታወቂያ የሚያወጡት:

 • በጋዜጣዎች: The Age (ቅዳሜ), Herald Sun (ቅዳሜ), የአካባቢ ጋዜጣዎች
 • በማህበረሰብ የማስታወቂያ ቦርድ ላይ፣ በአካባቢ ካፊቴሪያ፣ በቤተ መጻሕፍት፣ ዩኒቨርሲቲ ወይም ቴፍ/ TAFEs

 

ለንብረት ፍተሻ ስለማቀናጀት

በንብረት አከራይ ድርጅቶች በኩል በማስታወቂያ የወጣን ንብረት ለማየት ለቁልፍ ማስያዣ ገንዘብ መክፈል ይኖርብዎታል። ይህም በአብዛኛው $50 ዶላር ሲሆን ነገር ግን አንዳንዴ $100 ዶላር ይሆናል (ደረሰኝ መጠየቁን አይዘንጉ)። ቁልፍ በሚመልሱበት ጊዜ ገንዘብዎ ይመለሳል።

እንዲሁም ቁልፍ ሲሰጥዎ ፎቶ ያለበት መታወቂያ ሊያስፈልግዎ ስለሚችል አንዳንድ ፎቶግራፍ ያለበትን መታወቂያ መውሰዱ ጥሩ ነው። ንብረቱን በሚያዩበት ጊዜ ድርጅቱ ፎቶግራፍ ያለበትን መታወቂያዎን ፎቶኮፒ አድርጎ ማስቀመጥ ይፈልግ ይሆናል። መታወቂያዎ ፎቶኮፒ ተደርጎ ከሆነ ቁልፉን ሲመልሱ ፎቶኮፒ የተደረገውን መታወቂያዎ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ።

አንዳንዴ የአከራይ ድርጅቱ ወይም ባለንብረቱ “ክፍት የሆነ ፍተሻ” እንዲካሄድ ይመርጣል፣ ታዲያ ሌሎች ሰዎች ንብረቱን በሚያዩበት ጊዜ እርስዎም ማየት ይችላሉ። ብዙጊዜ ክፍት የሆነ ፍተሻ ለ30 ደቂቃ ብቻ ስለሆነ ታዲያ በታቀደው ሰዓት ላይ በንብረቱ ላይ መድረሱ አስፈላጊ ነው። በዚህን ጊዜ ቤቱን ለማየት አይከፍሉም እንዲሁም ለቁልፍ ማስያዣ አይከፍሉም።

የአከራይ ድርጅቱ ተወካይ ወይም ባለንብረቱ ቤቱን ለማየት የሚመጡትን ሰዎች በበሩ ሲገቡ እንደሚያዩ ማወቅ ይገባል፤ ታዲያ ለንብረቱ ኪራይ ለማመልከት ምናልባት ከወሰኑ አከራዮቹ ስለ እርስዎ ጥሩ አመለካከት እንዲኖራቸው ለማድረግ መሞከር አለብዎ።

የሚከራይ መኖሪያ ቤት ፍተሻ

የንብረቱን ውስጥና ውጭ በሚገባ መፈተሽ። የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት ከመፈረምዎ ወይም የሆነ ገንዘብ ከመክፈልዎ በፊት በንብረቱ ላይ ደስተኛ ስለመሆንዎ ያረጋግጡ። ያስተውሉ፤ የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት አንዴ ከፈረሙ፣ ንብረቱ ባለበት ሁኔታ ላይ ተስማምተው እንደተቀበሉ ነው። ለምሳሌ፡ የተከራይና አከራይ ውል ስምምነት በሚፈርሙበት ጊዜ በንብረቱ ላይ ሂተር ማሞቂያ ከሌለው ባለንብረቱ ለማቅረብ አይገደድም።

(ይሁን እንጂ ባለንብረቱ በንብረቱ ውስጥ ያሉና ተበላሽቶ ለማይሠራ ወይም ለተሰበረ ማንኛውም ነገር ማስጠገን ይኖርበታል።)

ለቤት መገልገያ እቃ ዋስትና የቤቱ መስኮቶችና በሮች የሚቆለፉ ካልሆኑ በስተቀር በአብዛኛው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ዋስትና አይሰጡም።

የኪራይ ቤት ስለማመልከት

ፈትሸው ካዩ በኋላ እና ቤቱን እንደፈለጉት ከወሰኑ የማመልከቻ ቅጹን መሙላት ይኖርብዎታል።

ስለራስዎ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቁ ይችላሉ:

 • የገቢ ምንጭ
 • የባንክ አካውንት ዝርዝር
 • ቀደም ሲል የነበረ የተከራይ ታሪክ
 • የሥራና ቀጣሪ ዝርዝርና ታሪክ
 • ምስክርነት የሚሰጥ (ቢያንስ ሁለት ሊጠየቁ ይችላሉ)

 

ለአውስትራሊያ አዲስ ከሆኑ የተጠየቁትን ሰነዶች በሙሉ ለማቅረብ አይችሉ ይሆናል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ14 ቋንቋዎች የተዘጋጀውን በቪክቶሪያ ውስጥ ቤት ስለመከራየት፡ በቅርቡ ለመጡ መጤዎችና ስደተኞች መመሪያ የሚለው ጽሁፍ በTenants Union of Victoria/Tenants Victoria ወይም በ Consumer Affairs Victoria ማግኘት ይችላሉ።

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካይ ድርጅት በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ ተመርኩዞ ልዩነት መፍጠር ህገ-ወጥነት ነው:

 • ዘር
 • የጋብቻ ሁኔታ
 • የአካል ጉዳት ወይም ጎደሎ
 • ወሲባዊ አገላለጽ ወይም በጾታ መለየት
 • ሃይማኖት ወይም የፖለቲካ እምነቶች

 

ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካይ ድርጅት ተከራዮች ህጻናት ስላላቸው ልዩነት መፍጠር ህገ-ወጥነት ቢሆንም ባለንብረቱ ወይም የአከራይ ድርጅት ተወካይ በResidential Tenancies Act 1997 መሰረት የሚከተሉትን ካሟላ በሚከራይ ንብረት ላይ ህጻናት እንዳይኖሩ ለማድረግ ይፈቅድለታል:

 • ባለንብረቱ በተመሳሳይ ንብረት ላይ የሚኖር ከሆነ
 • ንብረቱ ለህጻናት የማይስማማ ከሆነ
 • በንብረቱ ላይ ብቸኛ የሆኑ ሰዎች ወይም ህጻን የሌላቸው ባልና ሚስት እንዲኖሩ በመንግሥት የታገደ ከሆነ

 

በርስዎ ላይ ልዩነት ተፈጥሯል ብለው ካመኑበት በ Victorian Equal Opportunity & Human Rights Commission ቅሬታዎን ማቅረብ ይቻላል። ስልክ 1300 891 848።

የብድር እዳ መረጃ ፍተሻ

ስለርስዎ ብድር መረጃ ታሪክ የንብረት ተወካይ ድርጅት ለማወቅ ይፈልግ ይሆናል። ህጉ በደንበኛ እዳ ያሉትን መረጃዎች ማየት አይፈቅድላቸውም፤ ነገር ግን ህዝባዊ በሆነ ምዝገባ ላይ ያሉትን ማየት ይፈቀድላቸዋል። የንብረት ተወካይ ድርጅት የእዳ መረጃን ለማየት ከገፋፋ ምክር ለማግኘት Tenants Union/Tenants Victoria ማነጋገር።

ስለተከራይ የተቀመጠ መረጃ

የንብረት ተወካይ ድርጅቱ ጥሩ ያልሆነ የተከራይ ታሪክ እንዳለዎት ለማጣራት አንዳንድ ጊዜ ስለ ተከራዮች የተቀመጡ መረጃዎችን ይጠቀማሉ። ባለንብረቱ ወይም አከራይ ድርጅቱ ብዙጊዜ የተከራይ ማመልከቻዎችን ለማጣራት የተከራይ መረጃን ሊጠቀሙ ይችላሉ ታዲያ በሚያመለክቱበት ጊዜ በጽሁፍ ይህንን እንደሚያደርጉ ሊያሳውቁዎት ይገባል — ይህም ማመልከቻዎን ለመገምገም የተቀመጠ መረጃን ለመጠቀም መፈለግ አለመፈለግ ይሆናል። ይህ የጽሁፍ ማሳሰቢያ የትኛውን የተከራዮች የተቀመጠ መረጃዎችን እንደሚጠቀሙ፤ ለምን መረጃዎችን ለመጠቀም እንደወሰኑ እና መረጃዎችን የያዘው ኩባንያ ዝርዝር አድራሻን ያካተተ መሆን አለበት።

ዝርዝር መረጃው ከተገኘ ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ስለተመዘገበው ሁኔታ ለማሳሰብና እንዴት ከዝርዝሩ እንደሚሰረዝ ወይም እንደሚታረም ገላጻ ለማካሄድ የ7 ቀናት ጊዜ ይኖረዋል።

ያቀረቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ካገኘ

ቤቱን ለርስዎ ለማከራየት ባለንብረቱ ከተስማማ Residential Tenancy Agreement (ኮንትራት) እንዲፈርሙበት ይሰጥዎታል። ይህ ህጋዊ ኮንትራት ስለሆነ በጥንቃቄ ማንበብ እንዳለብዎትና ከመፈረምዎ በፊት በዚህ ኮንትራት ላይ ደስተኛ ስለመሆንዎ ያረጋግጡ።

ለመገልገያ አገልግሎቶች ማስቀጠል

አንዳንድ የንብረት ተወካይ ድርጅቶች የመገልገያ አገልግሎቶች በራስዎ ስም እንዲያስቀጥሉ ይጋብዛሉ ይህም ለጋዝ፣ ለኤሌትሪክ፣ ለውሀ፣ ለተለፎን ወዘተ. አገልግሎት። ስለ መገልገያ ማንኛውም ስምምነት ሲፈርሙ ጥንቃቄ ያድርጉ። ስለቅድመ ሁኔታ ማጣራትና ሊከሰት ለሚችል ማንኛውም ተጨማሪ ክፍያ ማጣራት። ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም ግዴታ የለብዎትም። በራስዎ አፈላልገው የመገልገያ አገልግሎት ካስቀጠሉ ተደራድረው የተሻለ ዋጋ ማግኘት ይችሉ ይሆናል።

ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ስለመጀመር
ስለ ተከራይ የተቀመጡ መረጃዎች ወይም “በጥፋተኝነት የተመዘገበ/blacklists”
ለፍጆታ ክፍያዎች
የንብርት ፍተሻ ማረጋገጫ ዝርዝር: ለተማሪ የመኖሪያ ቤት

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Applying for a private rental property | Amharic | September 2011

Was this page helpful?

Cookies and Privacy:This site uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

Find out more Accept